Author name: hanael

Article

ዓላማ

አንዳንድ ጊዜ፥ የሰው ልጆችን ህይወት ቆም ብላችሁ ብታስቡት፥ በተመሳሳይ ነገሮች የተሞላ ነው:: ሰው ይወለዳል፣ ያድጋል፣ ይማራል፣ ያገባል፣ ይወልዳል፣ ለኑሮው የሚያስፈልጉትን ነገሮች ለማሟላት ይሞክራል፣ እድሜ ከሰጠው ኖሮ፥ ካልሰጠውም ደግሞ በጊዜ ወደ አምላኩ ይሄዳል። ይሄ፥ የአብዛኛው ሰው ህይወት የሚያልፍበት ስርአት ነው። የየትኛውም ሰው ህይወቱ፥ ከዚህ ተመሳሳይ ድግግሞሽ አያመልጥም:: እግዚአብሄር የጥበብን መንፈስ የሞላበት ሰው ጠቢቡ ሰለሞን ህይወትንና የሰው ልጆችን እንቅስቃሴ ሁሉ አስተውሎ ከተመለከተ በኋላ ያለው ነገር ይገርመኛል:: “… ከንቱ ከንቱ የከንቱ ከንቱ ሁሉ ከንቱ ነው…” (መክብብ 1፡2)

Article

የተፈጠርኩበትን ዓላማ የማውቀው እንዴት ነው?

Home Blog Book About Contact X Order Book የተፈጠርኩበትን ዓላማ የማውቀው እንዴት ነው? Audio ብዙ ሰው በህይወቱ መጨረሻ ቁጭቶች ይኖሩታል። ማድረግ ነበረብኝ ወይንም አልነበረብኝም የሚላቸው ነገሮች ይበዛሉ። በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ፥ በእድሜው መጨረሻ ህይወቱን ዞር ብሎ አይቶ የእርካታና የደስታ ንግግር ከተናገሩ ሰዎች መካከል አንዱ ጳውሎስ ነው።  “መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፥ ሩጫውን ጨርሻለሁ፥ ሀይማኖትን ጠብቄያለሁ፥ ወደ ፊት የፅድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል ይህንም ፃድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል“ (2ኛ ጢሞ 4፡7) ጳውሎስ በነበረበት ዘመን የተማረ እና ብዙ ሊመካባቸው የሚችላቸው የህይወት ስኬቶች የነበሩት ሰው ቢሆንም፥ በህይወቱ መጨረሻ  ያገኘው ይሄ እርካታ ግን ከምድራዊ ስኬቶቹ ጋር የተያያዙ አልነበሩም። ይልቁንም ከእናቱ ማህፀን ጀምሮ እግዚአብሄር በህይወቱ ላለው አላማ እሱን መለየቱ፥ በፀጋው ውስጥ የደረሰው የአገልግሎት ጥሪ እና በህይወቱ ውስጥ እግዚአብሄር ልጁን ኢየሱስን ለሌሎች ሊገልጥ የወደደበትን አላማ በመረዳት ይሄን የተሰጠውን አላማ በመስዋእትነት በማገልገሉ ነው።   የምንኖርባት ምድር ስኬትን ከብዙ አቅጣጫ ትርጉም ብትሰጠውም፥ በእግዚአብሄር እይታ ስኬታማነት ማለት እግዚአብሄር የፈጠረንን አላማ መረዳት እና ያንን አላማ በሚመጥን የህይወት አካሄድ እና በሙሉ ትጋት አገልግሎ ማለፍ ነው። ሰው ይሄንን ሲረዳና በህይወቱ ተግባራዊ ሲያደርገው ነው ትክክለኛ የሆነውን የህይወት ትርጉምና እርካታ ማግኘት የሚጀምረው።  በባለፈው ክፍል ፅሁፋችን ውስጥ የዓላማን ምንነት ለማየት ሞክረን ነበር። ዓላማ ማለት እግዚአብሄር እኛን ከመፍጠሩ በፊት ስለ እያንዳንዳችን ህይወት ልቡ ውስጥ የነበረ ሀሳብ ማለት ነው። እግዚአብሄር እንደ ልቤ ያለው ሰው ዳዊት የዚህ ምድር ቆይታውን ስኬታማ ያስባለው፥ በራሱ ዘመን የእግዚአብሄርን ሀሳብ አገልግሎ ማለፉ ነው። እንግዲህ የእግዚአብሄር ቃል እንደሚናገረው፥ የስራ ድርሻችን ይለያይ እንጂ፥ እያንዳንዳችን በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ አብረን ሰራተኞች ልንሆንና የክርስቶስ አካል ልንሆን ነው የተጠራነው። አካልን ዝም ብላችሁ ስታዩት አገልግሎት የማይሰጥ ክፍል የለውም። እያንዳንዱ የአካል ክፍል አገልግሎት የሚሰጥ ብቻ ሳይሆን ለሚያገለግልበት የአገልግሎት ክፍል ተስማሚ ቦታና ቅርፅ  እንዲኖረው ተደርጎ ነው የተሰራው። እጅን ስታዩት ዓላማው መስራት ስለሆነ ልክ አንደ አፍንጫ እና ጆሮ አጭር ተደርጎ አልተሰራም። አይን ፊት ለፊት ስለሆነ ነገሮችን ቶሎ ማየት ይችላል። ሌላው ቀርቶ፥ ቅንድብ እራሱ እኛ እህቶች በርካታ ለሆኑ አገልግሎቶች እናውለው እንጂ ዋና አላማው አይንን ከአቧራ እና ከላብ መጠበቅ ነው። አፍንጫ በመተንፈስ ስለሚያገለግል ለአካሉ የጎላ ጠቀሜታ አለው። ጆሮ ይሰማልናል። እጅ ሰራተኛ ነው፥ እግርም እንዲሁ ወደሚያስፈልገው ስፍራ በመሄድ አካሉን ያገለግላል። የእግዚአብሄር ቃል በአካል የመሰለን፥ የአካል ክፍል  ቅርፅ እና ስራ እንደሚለያይ ሁሉ የተለያየ የተፈጥሮ ባህሪ እና የስራ ድርሻ ቢኖረንም፥ በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ሁላችንም ሰራተኞች እና አገልጋዮች እንደሆንን ለማስገንዘብ ነው።  “እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።” (ኤፌሶን 2፡10) አላማን ማወቅ ማለት ባለንበት የክርስቶስ አካል ውስጥ የትኛውን የአካል ክፍል ሆነን ለማገልገል እንደተጠራን ማወቅና መረዳት ነው። ለምሳሌ ብንወስድ፥ በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ አንደበት የሆኑ ሰዎች አሉ። ቦታቸው መድረክ ነው። እነዚህ በእግዚአብሄር አደባባዮች ላይ የሚቆሙ የእግዚአብሄር አንደበቶች ናቸው። አስተማሪዎች፥ ሰባኪዎች፥ ወንጌላውያን፥ እንዲሁም የቤተክርስቲያን መሪዎች ናቸው። ያስተምራሉ፥ ይገስፃሉ የእግዚአብሄርን ህዝብ ያገለግላሉ። ጳውሎስ እና አብዛኞቹ ሀዋሪያት በዚህ አገልግሎት ውስጥ አገልግለው አልፈዋል። በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ አይን ወይንም ጆሮ ሆነው የሚያዩና የሚሰሙ ሰዎች ደግሞ አሉ። ሊመጣ ያለው ነገው ይታያቸዋል ህልምን ወይንም ራእይን አይተው በመናገር የእግዚአብሄርን ህዝብ ያፅናናሉ ወይንም ሊመጣ ካለው ክፉ ነገር ህዝቡን/ልጆቹን ለማስመለጥ እግዚአብሄር ይጠቀምባቸዋል። እነዚህ፥ የጊዜውን የእግዚአብሄርን ሀሳብ የሚያመጡ ነቢያቶች ናቸው። ሙሴ፥ ሳሙኤል፥እምባቆም፥ ኤርምያስ እና ሌሎችም ብዙ የነቢያት ምሳሌዎች በቃሉ ውስጥ ተጠቅሰውልናል።  እንደ እጅ በመሆን የማገልገል ጥሪ ያላቸው ሰዎች ደግሞ አሉ። ብዙ ጊዜ መድረኮች ላይ ባናያቸውም ግን የትጋት መንፈስ ያለባቸው ለእግዚአብሄር መንግስት ይሄ ነው የማይባል ሚና የሚጫወቱ ሰራተኞች ናቸው። ይሄ በ1ኛ ቆሮ 12፡28 ላይ ከተዘረዘሩት የፀጋ ስጦታዎች ውስጥ “እርዳታ” በማለት አንድ ራሱን የቻለ የፀጋ ስጦታ እንደሆነ መፅሀፍ ቅዱስ ፅፎልናል። እነዚህ ሰዎች ቁጭ ብሎ ከመስተናገድ ይልቅ ማስተናገድ የሚያስደስታቸው፥ በእግዚአብሄር ቤት ውስጥ ለብዙ ሰው የማይታየው የጎደለ ነገር የሚታያቸውና የጎደሉ ቦታዎችን በመሙላት የሚያገለግሉ ናቸው። ይሄ ስጦታ ያላቸው ሰዎች፥ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ካላቸው የጠበቀ ህብረት የተነሳ፥ በመንፈስ በመመራትና ሰዎች ቤት ድረስ በመሄድ የሚያፈልጋቸውን ነገር ሲያደርጉ አይቼ አውቃለሁ።   “….እያንዳንዳችሁ የጸጋን ስጦታ እንደ ተቀበላችሁ መጠን በዚያው ጸጋ እርስ በርሳችሁ አገልግሉ። “ (1ኛ ጴጥ 4፡10)  ከላይ የተጠቀሱትን ጥቂት አገልግሎቶች ለምሳሌነት አየን እንጂ፥ በውስጣችን  እንደ ልብ፥ ኩላሊት እና ሌሎችም የማናያቸው፥ ነገር ግን አካል ቆሞ ለመሄዱ ወሳኝ የሆኑ የአካል ክፍሎች እንዳሉት ሁሉ፥ ፊት ለፊት የማናያቸው ነገር ግን በጣም አስፈላጊ የሆነ አገልግሎት ያላቸው ሰዎች በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ አሉ። ማስተዋል ያለብን ግን፥ አገልግሎት ቤተክርስቲያን ውስጥ ወይንም መድረክ ላይ ብቻ አለመሆኑን ነው። አገልግሎት በጣም ልዩ ልዩ ነው። መፅሀፍ ቅዱሳችንን ስናጠና፥ የእግዚአብሄርን ቤት ለመስራትና ለመገንባት እግዚአብሄር የጥበብ፥ የእውቀትና የማስተዋልን መንፈስ ያፈሰሰባቸው ሰዎች ነበሩ። (ዘፀ 31፡1-11) ሰዎችን የመምከር ስጦታ የነበራቸው ሰዎች ነበሩ፥  በመስጠት ያገለገሉ ሰዎች ነበሩ፥ እግዚአብሄር የጥበብንና የእውቀትን ስጦታ የሰጣቸው እንዲሁም በሌሎች የተለያየ አገልግሎቶች ውስጥ አገልግለው ያለፉ ሰዎች ነበሩ። “የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው፤ አገልግሎትም ልዩ ልዩ ነው ጌታም አንድ ነው፤ አሠራርም ልዩ ልዩ ነው፥ ሁሉን በሁሉ የሚያደርግ እግዚአብሔር ግን አንድ ነው።” (1ኛ ቆሮ 12፡4) የተሰጠን የፀጋ ስጦታ ወይንም መክሊት አስር ሊሆን ይችላል። ደግሞም አንድ ሊሆን ይችላል። የተጠራነው ለጥቂት ሰው ሊሆን ይችላል፥ ደግሞም ለብዙ ህዝብ ሊሆን ይችላል። ዋናው ግን የተጠራንበትን ትክክለኛ ቦታ ማወቅ እና በዛ ቦታ ላይ በታማኝነትና በትጋት ማገልገል ነው። የግል አላማዬን የማውቅባቸው መንገዶች ምንድናቸው?  1፥ አላማችንን ብዙ ጊዜ ግርግርና ጫጫታ ውስጥ አናገኘውም።  እኛን ወደ ትክክለኛው የህይወት አቅጣጫ ለመምራት፥ በፀጥታ ውስጥ የሚፈሰውን የእግዚአብሄርን ድምፅ ለመስማት ወደ ፀጥታ ቦታዎቻችን መግባትን መለማመድ ይኖርብናል። ያ የፀጥታ ቦታችን የመኝታ ክፍላችን ሊሆን ይችላል፣ መኪናችን ሊሆን ይችላል፣ ለብቻችን የምናደርገው የእግር መንገድ ጉዞ ሊሆን ይችላል፣ ወደ ተፈጥሮአዊ ቦታዎች መሄድ ሊሆን ይችላል፥ ለእኛ የሚመቸንን ቦታ መርጠን ያንን ከእግዚአብሄር ጋር ጊዜ የማሳለፊያ ቦታ ልናረገው እንችላለን። ስህተቶቻችንን ለማስተዋል፣ ትክክለኛ የሆኑ የህይወት ውሳኔዎችን ለመወሰን እንዲሁም ወደ አላማችን የሚመራንን የእግዚአብሄርን ድምፅ ለመስማት እድል የሚሰጡን የፀጥታ ቦታዎቻችን ናቸው። የፈጠረን ከአላማ ጋር ከሆነ እኛን ከመፍጠሩ በፊት ልቡ ውስጥ የነበረውን ትክክለኛ ሀሳብ ሊነግረን የሚችለው እግዚአብሄር እራሱ ነው። ይሄ ደግሞ ለእኛ የሚታወቀው ከእሱ ጋር በምናሳልፋቸው ጊዜያቶች ውስጥ ነው። ድምፁን ወደ እኛ በመላክ ወይንም ልባችንን ወደ ፍቃዱ በመምራት አላማችንን ያስታውቀናል።  2፥ ሁልጊዜ ልባችንን የሚሞላው ስራ ወይም አገልግሎት ምንድነው? ዙሪያችን ባሉ ድምፆች ወይም ግርግሮች ተሸፍኖብን ይሆናል እንጂ፥ የሆነ ጠንካራ መሻት ልባችን ውስጥ አለ። በጎ ፈቃዱን በህይወታችን ለማድረግ ሲል እግዚአብሄር በውስጣችን ያስቀመጠው ፍላጎት አለ። ወይንም ደግሞ፥ በሆነ ነገር ዙሪያ ከሌሎች የተሻለ አቅም ውስጣችን አለ። ያንን ለማወቅ ጊዜ ሰጥቶ ራስን መስማት በጣም አስፈላጊ ነው። የምንኖረው ህይወት ወይንም የምንሰራቸው ስራዎች ደስታንና እርካታን እየሰጡን ካልሆነ፥ ቆም ብለን “እግዚአብሄር የጠራኝን ነገር ነው ወይ እያደረኩ ያለሁት?” ብለን ራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል። ምክኒያቱም  አንዳንድ ጊዜ ለምናገኛቸው ጊዜያዊ ጥቅሞች ብለን የእኛ ያልሆኑና ለህይወታችን የእግዚአብሄር ሀሳብ የሌለባቸው ቦታዎች ውስጥ ዘመናችንን ልንጨርስ እንችላለን።  3፥ ስናደርገው ሰዎች የሚጠቀሙበት ነገር ምንድነው? በተደጋጋሚ ሰዎች የሚሰጡንን አስተያየቶች ማስተዋል የአገልግሎት ቦታችንን ለማወቅ ከሚያግዙን ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው። እግዚአብሄር ፀጋዎችን በውስጣችን የሚያስቀምጥበት ዋነኛ አላማ ሌሎችን ለማገልገል ስለሆነ እኛ ስናደርገው ሰዎች እንደተጠቀሙ የነገሩን ተደጋጋሚ አስተያየቶች ካሉ፥ ያንን ማስተዋል፥ ስለዚያ ነገር መፀለይና የእግዚአብሄርን ምሪት መፈለግ መልካም ነው።  በመጨረሻ እኔም እራሴ የተጠቀምኩበት እንዲሁም

Article

ፍጹም መውደድ 

Home Blog Book About Contact X Order Book ፍጹም መውደድ  Audio የሰው ልጅ የመብላት፣ የመጠጣት፣ የመልበስና መጠለያ የማግኘት መሰረታዊ ፍላጎቶች አሉት። እነዚህ መሰረታዊ ፍላጎቶቹ ለመኖር ብቻ ሳይሆን፥ የየቀን ኑሮውን በትክክልና በጤንነት ለማከናወን የሚያስችሉት አስፈላጊ ነገሮች ናቸው። መሰረታዊ ፍላጎቶቹ ግን በእነዚህ ከላይ በዘረዘርናቸው ነገሮች ብቻ የሚያበቁ አይደሉም። ሰው በጤንነት ለመኖር መብላትና መጠጣት እንደሚያስፈልገው ሁሉ፥ ስሜቱ ጤናማ እንዲሆን ደግሞ፥ ከእድገቱ ጀምሮ የቤተሰብና አካባቢው ያሉ ሰዎች ፍቅር ያስፈልገዋል። ከወላጆቹ እንዲሁም ከቤተሰቦቹ ጋር ፍቅርን መለዋወጥ ያስፈልገዋል። ለዚህ ነው በትክክል የቤተሰብና የወላጅ ፍቅር ያላገኙ ልጆች፥ ውስጣቸው በጣም የተጎዳ በመሆኑ፥ ወደ ከባባድ ህይወት ውስጥ ሲገቡ የምናየው። እንዲያውም የሆነ ችግር ገጥሞን የስነ ልቦና አማካሪዎች ጋር ስንሄድ፥ ሊያማክረን የተቀመጠው ሰው፥ ችግሮቻችንን ከመስማቱ በፊት፥ መጀመሪያ መስማት የሚፈልገው፥ የአስተዳደጋችንን ሁኔታ፣ በአስተዳደጋችን ውስጥ ከቤተሰብ ያገኘነውን ትኩረት፣ ከቤተሰብ ያገኘነውን ፍቅር ሆኖ የምናገኘው ለዚሁ ነው። አንድ ህጻን ገና ከእናቱ ሆድ ሲወጣ፥ ከባድ በሆነ ለቅሶ ነው የዚህች ምድር ህይወቱን የሚጀምረው። ከዚያ ግን ገና ልብስ እንኳን ሳይለብስ፥ እናቱ ደረት ላይ አምጥተው ሲያስቀምጡት፥ የእናቱን ፍቅርና እንክብካቤ ማግኘት ሲጀምር፥ ለቅሶውን ቀስ እያለ ይተወዋል። ሰው ካደገም በኋላ፥ በእድሜውና ባለፈባቸው የህይወት መንገዶች ውስጥ የተለያዩ የህይወት ልምዶችና እውቀቶችን ቢያገኝም፥ ውስጡ ያለው የመውደድና የመወደድ ፍላጎት ግን እድሜ ልኩን የሚቀጥል ነው። ታዲያ ግን ልብ ማለት ያለብን፥ እንደ መልካችን ልዩነት፥ ሁላችንም መወደድ የምንፈልግበት መንገድ ልዩ ልዩ መሆኑን ነው። እያንዳንዳችን ፍቅርን በበለጠ መንገድ የምንረዳበት፥ ከተፈጥሮአችን ጋር የተያያዘ መንገድ አለ። እንዲያውም Grey Chapman የተባለ አንድ የመጽሀፍ ጸሀፊ፥ አምስቱ የፍቅር ቋንቋዎች በሚል ርእስ በጻፈው መጽሀፉ ላይ እንዳስቀመጠው ከሆነ፥ ለብዙ አመታቶች ባደረገው ጥናት መሰረት፥ አምስት የፍቅር ቋንቋዎች እንዳሉ፥ የሁላችንም አንድ አይነት ባይሆንም፥ ከእነዚህ አምስት ቋንቋዎች ውስጥ፥ አንድ ወይንም ሁለት ፍቅርን የበለጠ የምንረዳበትና የሰዎች ፍቅር በትክክል ልባችን ጋር ሊደርስ የሚችልባቸው መንገዶች እንዳሉ ይናገራል። አካባቢያችን ያሉ ሰዎችን የፍቅር ቋንቋ ማወቅ፥ እነሱ መወደድ በሚፈልጉበት መንገድ እንድንወዳቸው በመርዳት፥ ከሰዎች ጋር ጥሩ የሆነ ግንኙነት እንዲኖረን እንደሚረዳ፥ በጻፈው መጽሀፍ ላይ አስቀምጦልናል። መጽሀፉ ለህይወቴ እጅግ በጣም የጠቀመኝና፥ ከቤተሰቦቼ እንዲሁም አካባቢዬ ካሉ ሰዎች ጋር ያለኝን ግንኙነቶች በብዙ የረዳልኝ መጽሀፍ ሆኖ ስላገኘሁት፥ ያላነበባችሁት ሁሉ እንድታነቡት እመክራለሁ። ከማንኛውም ሰው ጋር ጥቂት ጊዜ ካሳለፋችሁና ያንን ሰው ጆሮ ሰጥታችሁ ከሰማችሁት፥ መወደድ የሚፈልግበትን መንገድ ይናገራል። ባይናገር እንኳን ጥቂት ጊዜ ይፍጅብን እንጂ፥ እግዚአብሄር ማስተዋል ከሰጠን፥ የዚያን ሰው ስሜቶች አይተን መረዳት የምንችለው ነገር ነው። ዋናው ትልቁ አላማ ግን፥ በህይወታችን ላሉ ሰዎች ያለንን ፍቅር፥ እኛ ልብ ውስጥ ባለው የፍቅር መጠን ልክ መረዳት ይችሉ ዘንድ፥ የእነርሱን የፍቅር ቋንቋ ማወቅና ያንን ቋንቋ መናገር ነው። ይሄ ብዙ ድካማችንን ያቀለዋል። ለምሳሌ አንድ ሰው መውደዳችንን ሊረዳ የሚችለው ጊዜ ስንሰጠው ከሆነ፥ በጣም ብዙ ስጦታዎች በመግዛት መድከም ላይጠበቅብን ይችላል። ስጦታውን ቀነስ አርገን፥ ከዚያ ሰው ጋር ልናሳልፍና quality time ልንሰጠው የምንችልባቸውን ነገሮች እያመቻቸን፥ ለዚያ ሰው ያለን ቦታ እንዲገባው ማድረግና ከዚያ ሰው ጋር ያለንን ግንኙነት ጥሩ በሆነ መንገድ መቀጠል እንችላለን። ወደ ትልቁ ወደ እግዚአብሄርም ስንመጣ፥ እግዚአብሄር የእኛን ፍቅር በትክክል መረዳት የሚችልበትን መንገድ ሳይደብቅ በግልጽ ተናግሯል። በዮሀንስ ወንጌል ምእራፍ 14:15 ላይ “ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ” በማለት መወደድ የሚፈልግበትንና የእኛን ፍቅር በደምብ የሚረዳበትን ቀጥተኛ መንገድ ተናገረ። ኢየሱስዬ ብለን በቁልምጫ ቃል ብንጠራው፥ እምባችንን እያፈሰስን እንዴት እንደምንወደው ብንነግረው፥ እጆቻችንን ዘርግተን አመልክሀለሁ እያልን ብንጮህ፥ አርጉ የሚለንንና  የሚያዘንን ትእዛዞች ካላደረግን፥ የምናደርገው ነገር በሙሉ ስሜት ሊሰጠው አይችልም። እርሱ መወደድ የሚፈልግበትን መንገድ፥ ፍቅራችንን በትክክል የሚረዳበትን መንገድ ተናግሯል። እንዲያውም ያእቆብ በመልእክቱ ላይ እንደጻፈልን ከሆነ፥ “ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ፥ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ። ቃሉን የሚሰማ የማያደርገውም ቢኖር፥ የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት የሚያይን ሰው ይመስላል። ራሱን አይቶ ይሄዳልና ወዲያውም እንደ ምን እንደሆነ ይረሳል። ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ህግ ተመልክቶ የሚጸናበት፥ ስራንም የሚሰራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው፥ በስራው የተባረከ ይሆናል። አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ፥ እግዚአብሄርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር፥ የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው::” በማለት የእግዚአብሄርን ትእዛዝ ባለመጠበቅ ውስጥ የሆነ አምልኮ ሁሉ ከንቱ መሆኑን ይነግረናል።  እግዚአብሄር የሚወደድ አምላክ በመሆኑ፥ እግዚአብሄርን የማይወድ ሰው መቼም የለም። ቢያንስ ከእኛ ውስጥ የለም። እግዚአብሄርም እንድንወደው ይፈልጋል። እንዲያውም እግዚአብሄር እራሱ ለእስራኤል ህዝብ ከሰጣቸው ዋና ዋና ትእዛዞች ውስጥ አንዱ፥ እርሱን እግዚአብሄር አምላካቸውን በፍጹም ልባቸው፣ በፍጹም ነፍሳቸው፣ በፍጹም ሀሳባቸውና ሀይላቸው እንዲወዱት ነው። ኢየሱስም ይሄ ከትእዛዝ ሁሉ የበለጠው ትልቁ ትእዛዝ እንደሆነ አረጋግጧል። ታዲያ እግዚአብሄርን በፍጹም ነፍሳችን፣ በፍጹም ልባችን፣ በፍጹም ሀሳባችንና ሀይላችን መውደድ ማለት ምን ማለት ነው? እግዚአብሄርን መውደድ ማለት፥ ሙሉ ነፍሳችንን ተጠቅመን፣ ልባችንና ሀሳቦቻችን ውስጥ ያሉትን ቦታዎች በሙሉ ተጠቅመን፣ የሀይላችንን የመጨረሻ ጥጉን ተጠቅመን እግዚአብሄርን ደስ የሚያሰኘውን ነገር ማድረግ ማለት ነው። ደስ የሚያሰኘውን ነገሮች ለማድረግ፥ መክፈል እስከምንችለው ዋጋ ድረስ መሄድ ማለት ነው። መክፈል እስከምንችለው የሀይላችን ጥግ ድረስ መሄድ ማለት ነው። በነገራችን ላይ እግዚአብሄር ውስጣችን ያለውን የመውደድ አቅም ያውቀዋል። ውስጣችን ያለውን የማፍቀር አቅም ያውቀዋል። ስንወድ ምን ያህል ርቀት እንደምንጓዝ፣ አንድን ነገር በጣም ስናፈቅር፥ ምን ያህል ዋጋ እንደምንከፍል፥ አንድን ነገር በጣም ስንወድ፥ የት ድረስ እንደምንሄድ ያውቃል። ኢየሱስ እኛን ሲወደን የሄደው ርቀት ይሄ ነው። ርቀቱ ከሰማይ እስከምድር ነው። ከሰማይ ተነስቶ ያንን ሁሉ ርቀት ተጉዞ ወደ ምድር መጣ። ይሄ ነው ተብሎ በቃላት የማይነገረውን ሰማያዊ ክብር ወደ ጎን ቁጭ አርጎ፥ አምላክ መሆኑን ወደ ጎን አስቀምጦ መጣና ሰው ሆነ። እኛን ሆነ። እኔና እናንተን ሆነ። እራሱ ከምድር አፈር የሰራውን ሰው ሆነ። በሰው ምስል ተገኝቶ ራሱን አዋረደ። ራሱን ከመጠን በላይ ዝቅ ዝቅ አደረገ። ሰው መሆኑ ብቻ በቂ አልሆን ብሎት፥ በዚህች ክፉ አለም መከራ ሁሉ ውስጥ አለፈ። ፍቅርን ሊገልጸው የመጣበት ይሄ ሁሉ ርቀት አልበቃ ቢለው፥ መርገማችንን ሁሉ ተሸክሞ መስቀል ላይ ተገኘ። ይሄ ሁሉ ፍቅር ይገባን ይሆን? ፍቅር ይገባን ይሆን? ይሄንን ሁሉ ፍቅር፥ አይምሮአችን መሸከም ይችል ይሆን? የፍቅሩን ከፍታ ስፋትና ጥልቀት ለመረዳት፥ ከመታወቅ የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ እንደሚለው፥ ይሄንን ፍቅር በጥቂቱ እንኳን ለማወቅ፥ ብርታት ያስፈልገናል። ይሄንን ፍቅር ለመረዳት፥ የመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ያስፈልገናል። እግዚአብሄር ሲወድ የሄደበት ርቀት፥ ልጁን እስከመስጠት ነው። ኢየሱስ ሲወድ የሄደበት ርቀት፥ ከሰማይ ወደ ምድር በመውረድ ራሱን እስከመስጠት ነው። ሲወድ ከልቡ ነው። ለወደደው ነገር ደግሞ፥ ራሱን መስዋእት በማድረግ ማንም የማይከፍለውን ዋጋ ከፍሏል። ከእኛም የሚጠብቀው፥ የእውነታችንን እንድንወደው ነው። መስዋእትነት የተሞላበትን ፍቅር ነው ህይወታችን ውስጥ ማየት የሚፈልገው። ዋጋ እየከፈልን እንድንወደው። ራሳችንን ለእርሱ እንድናኖር። በሰጠን እስትንፋስ ሁሉ እርሱን እንድናከብረው። ያኔ እኛን ሲፈጥረን በውስጣችን ባስቀመጠው አቅም ሁሉ እንድንወደው፥ በአቅማችን ውስጥ ያለውን ነገር ብቻ ነው የጠየቀን። ትዝ ይላችሁ ከሆነ ነግደው አንዲያተርፉበት መክሊትን የሰጣቸው ባለቤት ሲመጣ፣ አምስት መክሊት ለሰጠው፥ ሌላ አምስት እንዲያተርፍበት ብቻ ነው የጠየቀው። ሁለት መክሊት ለሰጠውም እንዲሁ፥ ሌላ ሁለት እንዲያተርፍበት ብቻ ነው የጠበቀበት። ሁለት ሰጥቶት አምስት እንዲያተርፍ አልጠበቀበትም። አምስት ሰጥቶት ሌላ አምስት ያተረፈውንም፥ ሁለት ሰጥቶት ሌላ ሁለት ያተረፈውንም ሁለቱንም፥ አንተ በጎ ታማኝ ባሪያ ብሏቸዋል። ከሰጣቸው ቁጥር በላይ እንዲያተርፉ በፍጹም አልጠበቀባቸውም።  ምክኒያቱ ደግሞ፥ የሰጣቸው መክሊት እንደየአቅማቸው ስለሆነ ነው። እዛው ቃሉ ላይ ስታነቡ፥ መክሊቱን ሳይሰጣቸው በፊት “ለእያንዳንዱ እንደ አቅሙ” የሚል ቃል ታገኛላችሁ። ለእያንዳንዱ እንደ አቅሙ፥ ለአንዱ አምስት ለአንዱ ሁለት ለአንዱ ደግሞ አንድ ሰጣቸው ይላል። ሁላችንም ውስጥ እግዚአብሄር ያስቀመጠው አቅም፣ ጸጋ እና ስጦታ የተለያየ መሆኑን ማወቃችን፥ እራሳችንን ከማንም ሰው ጋር compair ሳናደርግ፥ በተሰጠን ነገር ውስጥ ብቻ እንድንሰራ ይረዳናል።

Article

ፍለጋ

Home Blog Book About Contact X Order Book ፍለጋ Audio የዘጸአትን መጽሀፍ ሳነብ፥ አንድ እስከዛሬ ያላስተዋልኩትን ነገር አነበብኩ። በመጽሀፉ 33ተኛ ምእራፍ ላይ እንደሚናገረው፥ ሙሴ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር የሚገናኝበትን የመገናኛ ድንኳን የተከለው፥ ሰፈር ውስጥ አልነበረም። የተከለው ከሰፈር ውጪ፣ ከመንደር ውጪ፣ አብዛኛው ሰው ከሚኖርበት ሰፈር ውጪ ነበር። ታዲያ እዚያው ምእራፉ ላይ እንደሚናገረው፥ እግዚአብሄርን እፈልገዋለሁ የሚል ሰው ሁሉ ከሰፈሩና ከመንደሩ እየወጣ፥ የመገናኛው ድንኳን ወዳለበት ቦታ በመሄድ እግዚአብሄርን ያገኝ ነበር። ቃሉ ለትምህርታችን እንደመጻፉ፥ ለህይወቴ የምማረውን ነገር ለማስተዋል ጥቂት ዝም አልኩ። ህዝቡ ከእግዚአብሄር ጋር ሊገናኝ የሚችልበትን የመገናኛ ድንኳን ለምንድነው ሙሴ ከሰፈር ራቅ አርጎ የተከለው? ለምንድነው እዚያው ለህዝቡ ቅርብ የሆነ ሰፈር ያልተከለው? እግዚአብሄር እርሱን ፍለጋ የምንሄደውን ርቀት ማየት ስለሚፈልግ ነው። መፈለግ ማለት ያንን የምንፈልገውን ነገር ለማግኘት የምናደርገው ብርቱ ጥረት ማለት ነው። እግዚአብሄርን ለማግኘት የምናደርገው ብርቱ ጥረት እግዚአብሄርን ያስደስተዋል። ብዙ ጊዜ ፍለጋ ውስጥ የምንገባው፥ ማግኘት ያቃተን ነገር ሲሆን ነው። እግዚአብሄር እኔን ፈልጉ ፊቴን ፈልጉ ብሎ ሲያዘን ግን ፊቱ ተፈልጎ ስለማይገኝ አይደለም። የፍላጎታችንን ብርቱ ጥረት ካሳ በመስጠት የሚደሰት አምላክ ስለሆነ ነው። እንኳንና እግዚአብሄርን ለማግኘት ቀርቶ፥ ሌሎችንም ነገሮች እኮ በህይወታችን ለማግኘት ኢየሱስ እንደነገረን “ለምኑ ይሰጣችሁዋል። ፈልጉ ታገኙማላችሁ” በማለት፥ መፈለግ ነገሮችን የምናገኝበት ዋና መንገድ መሆኑን ተናግሯል። እግዚአብሄርም በህይወታችን አንድን ነገር ሊያደርግ ሲፈልግ፥ መጀመሪያ በልባችን የሚያስቀምጠው ፍላጎትን ነው። መጀመሪያ በልባችን የሚያስቀምጠው መፈለግን ነው። የእስራኤል ህዝብ እግዚአብሄርን ለማግኘት፥ ከሰፈራቸው ውጪ ወደተተከለው የመገናኛ ድንኳን መሄድ ነበረባቸው። እግዚአብሄርን ለማግኘት ካሉበት ሰፈር መውጣት ነበረባቸው። ካሉበት መንደር፣ ከሚኖሩበት፣ ሰዎች ከበዙበት፣ ግርግርና ጫጫታ ከሞላበት ሰፈር ወጥተው፥ ከሰፈርና ከመንደራቸው ውጪ ወደተተከለው ወደ እግዚአብሄር ድንኳን መሄድ ነበረባቸው። የእግዚአብሄርን ህልውና በሙላት የምናገኘው፥ ከጫጫታና ከግርግር ተለይተን ለብቻችን በምሆንበት የጸጥታ ቦታችን ነው። ከብዙሀኑ ድምጽና ካለንበት ሰፈር ወጥተን ወደ መገናኛው ድንኳን መሄድን እራሳችንን ማስለመድ አለብን። መውጣት፣ ብቻችንን መሆን መልመድ። ዝም ባለ ቦታ ሆነን ልባችንን ወደ እግዚአብሄር ማንሳት። የምንወደውን ሰው ለማግኘት ህይወታችን ላይ ያሉትን ነገሮች እንደምናመቻች ሁሉ፥ እስትንፋሳችንን በእጁ ይዞ ከምንም ነገር በላይ ለእኛ አስፈላጊ የሆነውን እግዚአብሄርን ለማግኘት ካለንበት ሰፈርና መንደር መውጣት። ወደ መገናኛው ድንኳን መሄድ። እግዚአብሄርን ፍለጋ። ህልውናውን ፍለጋ። ድምጹን ፍለጋ። መገኘቱን ፍለጋ። ከእርሱ ጋር መሆንን ፍለጋ። አንድ በፍቅር የተያዘች ነፍስ፥ ያፈቀረችውን ሰው ለማግኘት መሄድ ያለባትን ርቀት ሁሉ እንደምትሄድ፥ ልክ እንደዚያ እግዚአብሄርን ፍለጋ መሄድ።  የእስራኤል ህዝብ እግዚአብሄርን ለማግኘት ከሚኖሩበት ሰፈር ወጥተው የመገናኛው ድንኳን ወደ ተተከለበት ቦታ መሄድ ነበረባቸው። ሙሴ ደግሞ ከእግዚአብሄር ጋር ጊዜ ለማሳለፍና ለመነጋገር ወደ ሲና ተራራ መውጣት ነበር። ተራራ መውጣት አድካሚ ነው። ቀጥ ያለ መንገድ እንደመሄድ ወይንም ቁልቁለት እንደመውረድ ቀላል አይደለም። ምናልባት አንዳንድ ጊዜ ለመዝናናት hiking ስንሄድ ድካሙን እናውቀዋለን። እኛ ለመዝናናትና ተራራው ጫፍ ላይ ወጥተን ፎቶ ለመነሳት ነው የምንሄደው። ሙሴ ግን የሲናን ተራራ ብቻውን የሚወጣው፥ 40 ቀንና 40 ሌሊት እዚያው ተራራው ላይ ምንም ምግብ ሳይበላ ለመቆየት ነው። መንገዱ ታዲያ ምንም አድካሚ ቢሆንም፥ ተራራው ጫፍ ላይ በእግዚአብሄር ህልውና ውስጥ የሚያሳልፈው ጊዜ አለመብላትና አለመጠጣቱን ሁሉ እንደሚያስረሳው እርግጠኛ ነኝ። ተራራው ጫፍ ላይ ከወጣ በኋላ የሚጠብቀው የእግዚአብሄር ክብር ያለበትን ዓለም እንደሚያስረሳው ምንም አልጠራጠርም። እኛ እንኳን አብረን ስናመልክ ወይንም በቤታችን ለጥቂት ሰአታቶች ስንጸልይ፥ በሩቅ የሚሰማን የእግዚአብሄር ህልውናና ክብር ሁሉን ነገር አይደል እንዴ የሚያስረሳን! ሙሴ እኮ ሰው ከባልንጀራው ጋር እንደሚነጋገር እግዚአብሄር ፊት ለፊት በግርማ ሞገሱ እየወረደ የሚያናግረው ሰው ነበር። ሙሴ ወደ ተራራው ሲወጣ እኮ፥ የእግዚአብሄር ደመና ተራራውን ይሸፍነው ነበር። የእግዚአብሄር ክብር በተራራው ላይ ይቀመጥ ነበር። በዘጸአት 24 ላይ እንደሚናገረው፥ የእግዚአብሄር ደመና ስድስት ቀን ተራራውን ከሸፈነው በኋላ፥ በሰባተኛው ቀን ሙሴ ወደ ደመናው ውስጥ እንዲገባ ተጠርቶ ነበር። በተራራው ራስ ላይ የሚወርደው የእግዚአብሄር ክብር፥ ልክ እንደሚያቃጥል እሳት እንደነበር የእግዚአብሄር ቃል ይናገራል። ምን አይነት ነገር ነው? ሙሴ እኮ በእግዚአብሄር ፊት ሆኖ ጊዜ ሲያሳልፍ፥ ልክ እንደ እኛ ለአንድ ወይንም ለሁለት ሰአት ጸልዮ መነሳት ሳይሆን፥ ለ6 ቀናቶች በተራራው ላይ ቆሞ መጠበቅ፥ ከዚያ ወደ  ደመናው ውስጥ ሲጠራ በመግባት፥ በእግዚአብሄር ክብርና ህልውና ውስጥ ሆኖ 40 ቀንና 40 ሌሊት ሙሉ እዚያው መሆን። እዚያው ቦታ መቆየት። የጸሎት ስነ ስርአት አከናውኖ ጨርሶ ወደ ሌላ ጉዳይ ውስጥ መግባት ሳይሆን፥ በቃ እዚያው መሆን። እዚያው መቆየት እዚያው መዋልና ማደር።   ታዲያ ግን የእግዚአብሄር መገኘትና ህልውና እንደማይጠገብ የምታውቁት፥ ሙሴ እግዚአብሄር ፊት ለፊት ወርዶ የሚያናግረው ሰው ቢሆንም፥ “ክብርህን አሳየኝ” እያለ መጠየቁ ነው። በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ ከተጻፉት ትልልቅ የእግዚአብሄር ሰዎች መካከል፥ እንደ ሙሴ የእግዚአብሄርን ክብር ያየ ሰው ያለ አይመስለኝም። የእግዚአብሄር መገኘትና ህልውና እንደማይጠገብ የሚያስተምረኝ ደግሞ የሙሴ “ክብርህን አሳየኝ” ጥያቄ ነው። እግዚአብሄር ክብሩን ያሳያችሁ። እግዚአብሄር በህልውናው ያረስርሳችሁ። ሙሴ ታዲያ ወደ ሲና ተራራ ላይ እየወጣ ከእግዚአብሄር ጋር ካሳለፋቸው ጊዜያቶች በኋላ ሁልጊዜ ከእግዚአብሄር ዘንድ ወደ ህዝቡ ይዞ የሚመጣው መልእክት ነበረው። አንድም ጊዜ ወደ ተራራ ላይ ወጥቶ ከእግዚአብሄር ጋር ቆይቶ ሲመጣ ያለ መልእክት ወደ ህዝቡ ተመልሶ አያውቅም። በእግዚአብሄር ህልውና ውስጥ የሚቆይ ሰው፥ ሁልጊዜ መልእክት አለው። የሚለው ነገር አለው። ሙሴ ከተራራው ሲወርድ ይዞ የመጣው፥ የእግዚአብሄር ህጎች የተጻፉበትን ጽላቶች ነበር። እግዚአብሄር ለህዝቡ እንዲሰጥ የሰጠው ትእዛዝ ነበር። መልእክት ነበረው። አሁንም በዘመናችን ላይ ትክክለኛ የሆነውን የእግዚአብሄርን ሀሳብ ወደ ህዝቡ የሚያመጡት፥ ከእግዚአብሄር ጋር ትክክለኛ ጊዜ የሚያሳልፉ ሰዎች ናቸው። ከእግዚአብሄር ጋር ጊዜ ስታሳልፉ፥ ለሰዎች የምትሉት ነገር ይኖራችኋል። መልእክት ይኖራችኋል። ለዚህ ትውልድ የምታስተላልፉት መልእክት ይኖራችኋል። ላገኛችሁት ሰው ሁሉ የምትሉት ነገር አላችሁ። መንገድ ለጠፋበት ሰው መንገድ ታሳያላችሁ። ግራ ለገባው ሰው መፍትሄ ትሆናላችሁ። ጥያቄ ላለው ሰው መልስ ትሆናላችሁ። እንዲያውም ትዝ አይላችሁም ሳኦል የአባቱ አህዮች ሲጠፉበትና ግራ ሲገባው ወዴት ነበር የሄደው? ትልቅ የእግዚአብሄር ሰው ወደሆነውና ከልጅነቱ ጀምሮ በመቅደስ በእግዚአብሄር ማደሪያ እየዋለና እያደረ የእግዚአብሄርን ድምጽ ወደተለማመደው ወደ ሳሙኤል ነበር የሄደው። እንደገና ደግሞ በ2ኛ ነገስት ምእራፍ 3 ላይ፥ የእስራኤል፣ የይሁዳና የኤዶም ያስ ንጉስ ተጋግዘው ለሰልፍ ወደ ምድረበዳ ሲወጡና በውሀ ጥም ሲጨነቁ ወደ ማን ነበር የሄዱት? ተቀብቶ የእግዚአብሄር መንፈስ ወዳረፈበት ወደ ነቢዩ ወደ ኤልሳእ ነበር። ያቺ ደግሞ በ2ኛ ነገስት ላይ ያለችውና ልጇ የሞተባትን ሱናማዊት ሴት ስትመለከቱ፥ የልጇን መሞት እጅግ በጣም በቅርቧ ላለው ለባሏ እንኳን ሳትናገር፥ መፍትሄ ፍለጋ ሩቅ መንገድ የሄደችው ወደ ነቢዩ ኤልሳእ ነበር። እነዚህ ሰዎች የሰዎች ጥያቄ መልስ ሊሆኑ የቻሉት፣ ለሰዎች ጭንቀትና ሀዘን መፍትሄ ሊሆኑ የቻሉት፣ በእግዚአብሄር ስለተመረጡና በእግዚአብሄር ህልውና ውስጥ ስለሚቆዩ ነው።  መቼም እያንዳንዳችን ብንጠየቅ፥ ሳናደርግ መሞት የማንፈልጋቸው ህልሞች በልባችን ውስጥ ይኖራሉ። እነዚህ ህልሞች ታዲያ፥ ለራሳችን የሚጠቅመንን ነገሮች ከማግኘት ባለፈ፥ የእግዚአብሄርን ሀሳብ በዘመናችን ከማገልገልና ውስጣችን በተቀመጠው ሸክም አቅጣጫ ሌሎችን ማገልገል፣ ለሆነ ሰው መፍትሄ መሆን፣ የሆነን ሰው መርዳት፣ ለሆነ ሰው መልስ መሆን እንደሚሆን እገምታለሁ። እነዚህ ህልሞቻችን እውን የሚሆኑት ታዲያ፥ ከእግዚአብሄር ጋር ባሳለፍነው ጊዜ ልክ ነው። በእኛ ውስጥ ለሰዎች መልስ የሚሆነው እግዚአብሄር እራሱ ነው። በእኛ ውስጥ ለሰዎች መፍትሄና የልብ እረፍት የሚሆነው እግዚአብሄር እራሱ ነው። የጥያቄዎች ሁሉ መልስ ከሆነው ከእርሱ ጋር ጊዜን ባሳለፍንና በህልውናው በተሞላን መጠን፥ አካባቢያችን ላይ ላሉት ሰዎች አልፎም ለዚህ ትውልድ እረፍትና መፍትሄ አለመሆን አንችልም። የምንሞላው መልስ የሆነውን የእግዚአብሄርን ህልውና ነው። የምንሞላው መንገድ የሆነውን እግዚአብሄርን ነው። የእግዚአብሄርን ቃል ስናነብ፥ በቃሉ ውስጥ ትልልቅ ተጽእኖን በማምጣት የእግዚአብሄርን ሀሳብ ያገለገሉ ሰዎች በሙሉ እግዚአብሄርን በብርቱ የሚፈልጉ ሰዎች ነበሩ። ከእነዚህ ሰዎች ውስጥ መቼም ሳናነሳ የማናልፈው ንጉስ ዳዊትን ነው። ዳዊት ዘማሪ ነው ደግሞም ንጉስ ነው። መቼም

Article

ጸሎት

Home Blog Book About Contact X Order Book ጸሎት Audio መቼም ስለ ጸሎት የማያውቅ ሰው በዚህች ምድር ላይ አለ ብዬ አላስብም። ማለትም ሰው የክርስቶስ ተከታይ ባይሆን እራሱ የሆነ ነገር ተከታይ ነው። ወደ እግዚአብሔር ባይጸልይ እንኳን አምላክ የለም ብሎ ከሚያምን ሰው በስተቀር ወደሚያምንበት እና አምላክ ብሎ ወዳሰበው አካል ይጸልያል። ጸሎት አብዛኛው ሰው የሚያደርገው ነገር መሆኑ፥ ሰው ሁሉ በዚህች ምድር በሚኖረው በዚህ ሕይወት ውስጥ እርዳታ ፈላጊ መሆኑን እንድንረዳ ያደርገናል። አብዛኛው የዓለማችን ሕዝብ እንዲያውም ጸሎትን አማራጭ አድርጎ የሚያስበው፥ ጭንቀት እና ፍርሀት ውስጥ በገባ ሰአት ከእርሱ አቅም በላይ የሆነ አጣብቂኝ ውስጥ በገባ ሰአት ነው።  ለእኛ በክርስቶስ አምነን የእግዚአብሔር ልጆች ለሆንን ሰዎች ግን ጸሎት ሲጨንቀን የምንሮጥበት ቦታ ብቻ ሳይሆን፥ ሁሉ ሰላም በሆነ ጊዜ፣ ሁሉ ደህና በሆነ ጊዜ ከአምላካችን ጋር የምናወራበት፣ እግዚአብሔርን ፍለጋ የምንሄድበት እና በየእለቱ ከምንወደው አምላካችን ጋር የምናደርገው የፍቅር ሕብረት ነው። ወደ ፊቱ እየመጣን የፍቅር መስዋእታችንን እና አምልኳችንን የምንሰጥበት የከበረ ስፍራ ነው።  ጸሎትን ትርጉም ስጡት ከተባልን አብዛኞቻችን የምንሰጠው ትርጉም ይሄ ነው። ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር የሚደረግ ንግግር ነው። ልክ ከሰው ጋር ንግግር እንደምናደርገው ሁሉ፥ አምላክ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሰጠን የልጅነት መንፈስ ውስጥ ሆነን፥ አንድ ልጅ ከአባቱ ጋር በሚነጋገርበት ነጻነት ከአምላካችን ጋር እንነጋገራለን። ታዲያ ንግግር የምትለውን ቃል አስምሩልኝ። ንግግር በሁለት አካል መካከል በሚለዋወጡ ቃላቶች ውስጥ የሚደረግ የሀሳብ ልውውጥ ነው። አንደኛው አካል ብቻ ተናግሮ ጨርሶ የሚሄድበት አይደለም። ከተናገረ በኋላ የግዴታ እያናገረው ያለውን አካል ምላሽ እና ሀሳብ ይጠብቃል። እንደዚያ ሲሆን ንግግሩ ሙሉ ይሆናል። ጸሎት እኛ የምንናገርበት ብቻ አይደለም። እድል ከሰጠነው እና በትጋት ከፈለግነው እግዚአብሔርም ለእኛ የሚናገርበት ቦታ ነው።  ይህም ደግሞ አምላካችን እግዚአብሔር ልክ በኤልያስ ዘመን የአህዛብ አማልክቶች እንደማይሰሙ እንደማይመልሱ እና እንደማይናገሩ በማሳየት ሕያውነቱን እንደገለጠው፥ ጆሮን የሰራ የሚሰማ፣ አንደበትን የፈጠረ የሚናገር አምላክ ስለሆነ ነው። ታዲያ ይሄ አምላክ እዛ የእነ ኤልያስ ዘመን ላይ ንግግሩን አልጨረሰም፥ ዛሬም ልክ ኤልያስን በኮራት ፈፋ ውስጥ ተሸሸግ ብሎ በወቅቱ ማድረግ ያለበትን እንደነገረው፥ ልክ ጊዜው ሲደርስ ደግሞ “አሁን ሂድና ለአክዓብ ተገለጥ” በማለት ኤልያስን እንደመራው፥ ዛሬም በፍጹም ልባቸው ለተከተሉት እና ለፈለጉት ሰዎች ይናገራል፣ ይመራል፣ በእያንዳንዱ የሕይወት ምእራፎች ውስጥ ያለውን ፈቃዱን በዝርዝር ይናገራል።  የእግዚአብሔርን ምሪት፣ የእግዚአብሔርን ድምጽ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ሀይል መለማመድ የምንጀምረው ታዲያ እግዚአብሔር እራሱ ጸልዩ ባለን መንገድ ወይንም እርሱ እንዳዘዘን ስንጸልይ ብቻ ነው። አንድንድ ጊዜ ጸሎት የሚመስሉ ነገር ግን ዝም ብለን እንደ ልማድ ብቻ የምናረጋቸው ካላረግናቸው ደስ የማይለን የእግዚአብሔርን ሀይል የማይገለጥባቸው ስጋዊ ልምምዶች አሉ።  ጸሎት በየቀኑ የለመድናቸውን ቃላቶች መደጋገም አይደለም፣ ያማሩ ቃላቶች ስብስብ አይደለም፣ ጸሎት ችሎታ ወይንም የረጅም ጊዜ ልምድ አይደለም፣ ድምጽን ጮክ ማድረግም አይደለም፣  ሀይማኖታዊ ልምምድ እና ስርዓትም አይደለም። ይልቁንም ሕይወት ያለበት፣ እውነተኞች በመሆን ድካም ውስጥ ካለን፣ ድካማችንን በፊቱ አምነን በመቀበል ሀይልን የምንቀበልበት፥ ራሳችንን የምንሆንበት እና ልባችንን ከፈቃዱ ጋር በማስማማት ከአምላካችን ጋር ፍጹም የሆነውን ሕብረት የምናረግበት፣ ፈቃዱን የምናውቅበት፣ ፍቅራችንን የምንሰዋበት የከበረ ቦታ ነው።  ስለ ጸሎት ስናስብ በመጀመሪያ ማሰብ ያለብን፥ እግዚአብሔር መንፈስ መሆኑን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በዮሐንስ ወንጌል  ምእራፍ 4 ላይ ሲናገር “እግዚአብሔር መንፈስ ነው” ይላል:: ወዲያው ታዲያ ቀጠል አርጎ “የሚሰግዱለትም በእውነት እና በመንፈስ ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል” በማለት ይናገራል። ከእግዚአብሔር ጋር ለማውራትም ሆነ እግዚአብሔርን ለማምለክ ስንቆም፥ መጀመሪያ መረዳት ያለብን እግዚአብሔር መንፈስ መሆኑን ነው። በመሆኑም ከእርሱ ጋር ማውራት፣ ሕብረት ማድረግም ሆነ ልዩ ልዩ መንፈሳዊ መገለጦች ጋር በመድረስ እርሱን ማምለክ የምንችለው በእውነት እና በመንፈስ መሆንን ስንማር ብቻ ነው። የዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ ምእራፍ 1፡10 ላይ ዮሐንስ ሲነግረን እንደዚህ ይላል “በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፥ በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ..” ይላል።  እግዚአብሔር እየተናገረ ያለውን የእግዚአብሔርን ድምጽ መስማት የምንጀምረው፣  በመንፈስ መሆንን መለማመድ ስንጀምር ብቻ ነው። ሌላ ተጨማሪ ቃል ደግሞ በ1ኛ ቆሮንቶስ ምእራፍ 1 ከቁጥር 10 ጀምሮ እንዲህ በማለት ይናገራል።  “መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው። በእርሱ ውስጥ ካለው ከሰው መንፈስ በቀር ለሰው ያለውን የሚያውቅ ሰው ማን ነው? እንዲሁም ደግሞ ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር ለእግዚአብሔር ያለውን ማንም አያውቅም። እኛ ግን ከእግዚአብሔር እንዲያው የተሰጠንን እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም። መንፈሳዊውን ነገር ከመንፈሳዊው ነገር ጋር አስተያይተን መንፈስ በሚያስተምረን ቃል ይህን ደግሞ እንናገራለን እንጂ የሰው ጥበብ በሚያስተምረን ቃል አይደለም። ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም። መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል ራሱ ግን በማንም አይመረመርም።”  በጸሎት ውስጥ እውነተኛ የሆነውን ሕብረት ከእግዚአብሔር ጋር ለማድረግ፥ ድምጹን ለመለማመድ እና ምሪት በምንፈልግባቸው የሕይወታችን ዝርዝር ጉዳዮች ውስጥ ምሪትን ለማግኘት፥ በመንፈስ መሆንን እራሳችንን ማስለመድ ያስፈልገናል። እንዴት ነው በመንፈስ መሆንን የምንማረው ብለን ከጠየቅን፥ የሚረዱንን ጥቂት ነጥቦች እስኪ እንመልከታቸው።  ልባችንን መመርመር፡- መቼም እግዚአብሔር እራሱ በቃሉ ከነገረን ዋና ዋና ነገሮች አንዱ ከመጸለያችን በፊት ውስጣችንን መመርመር እንዳለብን ነው። ከሰዎች ጋር ቅሬታ፣ ቂም እና ጥላቻ ካለብን፥ ያንን መጀመሪያ መፍታት እንዳለብን ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን ይቅር ማለት እንዳለብን፥ ጉዳያችንን መጨረስ ካለብን ሰዎች ጋር መጨረስ እንዳለብን፣ በእርሱ ፊት ለጸሎትም ሆነ ለአምልኮ ከመቆማችን በፊት ልባችን በፍጹም ፍቅር እና ይቅርታ ውስጥ መሆን እንዳለበት በቃሉ ነግሮናል። እንዲያውም ሰዎችን ይቅር አለማለታችን እግዚአብሔር የእኛን በደል ይቅር እንዳይለን ሊያደርግ የሚችል ከባድ ነገር መሆኑን ከእግዚአብሔር ቃል ያስተምረናል። ስለዚህ ለጸሎት ከምንዘጋጅባቸው ዋና ዋና ነገሮች ውስጥ አንዱ ከእነዚህ እግዚአብሔር ከሚጠላቸው ነገሮች ሁሉ ልባችንን ማጽዳት ነው። እግዚአብሔርን በሙሉ ትኩረት ማሰብ:- በመንፈስ ለመሆን ከሚረዱን ዋና ዋና ነገሮች ውስጥ አንዱ፥ በትኩረት ወይንም ባልተከፈፋፈለ ሀሳብ እግዚአብሔርን ማሰብ ነው። ይሄ የታወቀ የሚመስለን ግን ጥቅሙ ያን ያህል ስላልገባን፥ የሚገባውን ቦታ ያልሰጠነው እጅግ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። እስኪ አንድ ጥያቄ ራሳችንን እንጠይቅ፥ ከሰዎች ጋር ስንጸልይ፥ መቼ ነው የሰዎቹን የጸሎት ችሎታ መገምገም ትተን እግዚአብሔር ላይ ትኩረት በመስጠት የጸለይነው? መቼ ነው በህብረት ዝማሬዎቻችን ላይ የአዘማሪዎቹን የዝማሬ ችሎታ ወይንም ብቃት መገምገም ትተን ዝማሬው ውስጥ ያሉትን እያንዳንዱን ቃላቶች በማስተዋል፥ አምላካችንን ብቻ እያሰብን የዘመርነው? መቼ ነው ስብከት ለማቅረብ ፊታችን የቆመውን ሰው የአሰባበክ ችሎታ መገምገም ትተን፥ በሰባኪው ውስጥ እግዚአብሔር ሊናገረን የወደደውን ለማስተዋል ልባችንን አምላካችን ላይ ብቻ ያደረግነው? አብዛኛውን ጊዜ እንዲያውም ቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀምጠን ሀሳባችን ሌላ ሌላ ቦታ ላይ ስለሆነ አሜን በማይባልበት የተሳሳተ ቦታ እራሱ አሜን ስንል ወይንም ሰዎች ሲሉ አጋጥሞን አያውቅም?  ብዙ የምናረጋቸውን ነገሮች በማስተዋል ከተመለከታችሁ፥ ለምናረጋቸው ነገሮች ምንም ትኩረት አንሰጥም። አንድ ቀለል ያለ ምሳሌ ብንመለከት፥ አንድ በጣም ከምናከብረው ሰው ጋር ምሳ ወይንም እራት ለመብላት ብንቀጣጠር፥ ያንን ሰው ካገኘነው በሁዋላ ለዚያ ሰው ክብር ስንል ከምንሰጠው ቀዳሚ እና ዋና ነገሮች ውስጥ አንዱ ሙሉ ትኩረታችንን ነው። ያንን ሰው አስቀምጠን በስልካችን ድራማ አናይም። ወይንም ሲጮህ የሚውለውን ስልካችንን አንስተን ከሌላ ሰው ጋር ሌላ ጨዋታ አንይዝም። ወይንም ሌላ ሌላ ነገር እየሰራን ለዚያ ፊታችን ለተቀመጠው ለምናከብረው ሰው የተከፋፈለ ትኩረት አንሰጠውም። ይልቁንም ያ የምናከብረውን ሰው አይን አይኑን እያየን ሙሉ ትኩረታችንን ወደዚያ ሰው አርገን በአክብሮት እናወራለን። ለአንድ ለምናከብረው ሰው ይገባዋል ብለን የምንሰጠውን ነገር፥ እንዴት ለእግዚአብሔር አንሰጠውም? አንድ የምናከብረው ሰው ይገባዋል ብለን የምናስበው ነገር፥ እንዴት እግዚአብሔርን አይገባውም? እግዚአብሔር በሚልክያስ መጽሐፍ ላይ ስለ መስዋእት ሲናገር እንዲህ አለ “እስኪ ይሄን ያመጣኸውን አንካሳ እና እውር መስዋእት ለአለቃህ አቅርበው። ለአለቃህ ታቀርበዋለህ?” በማለት ለእርሱ የምንሰጠውን ነገር፥

Article

ጥንቃቄ

Home Blog Book About Contact X Order Book ጥንቃቄ Audio ከህይወታቸው እንማረባቸው ዘንድ በመጽሀፍ ቅዱሳችን ላይ ከተጻፉልን ሰዎች መካከል ነው። ብዙ ጊዜም በየመድረኮቻችን ላይ ታሪኩ ለትምህርታችን ሲሰበክ እናውቀዋለን። ሳምሶን። የተቀባ በጣም ትልቅ የእግዚአብሄር አላማ ያለበት ሰው። ይህ ትልቅ የእግዚአብሄር ሀይል የተገለጠበት ሰው ታዲያ ታሪኩን ብዙዎቻችን እንዳነበብነውና እንደተማርነው፣ ብዙም ሳይቀጥል በጠላቶቹ እጅ በመውደቅ፥ ሙሉውን የእግዚአብሄርን ሀሳብ አገልግሎ ሳይጨርስ አገልግሎቱ እንዳበቃ ብዙዎቻችን እናውቃለን። የሳምሶን ታሪክ በመሳፍንት ምእራፍ 13 ላይ ሲጀምር፥ ከሳምሶን ታሪክ አይጀምርም። ይልቁንም የእስራኤል ልጆች በእግዚአብሄር ፊት እንደ ገና ክፉ ስራ እንደሰሩ፥ እግዚአብሄርም በፍልስጥኤማውያን እጅ አርባ አመት አሳልፎ እንደሰጣቸው በመናገር ነው የሚጀምረው። ሳምሶን የተወለደበት ወቅት፥ እግዚአብሄር የእስራኤልን ህዝብ በፍልስጥኤም ግዛት ስር የጣለበት፥ እስራኤላውያን በጠላቶቻቸው እጅ ተላልፈው የተሰጡበት ከባድ ወቅት ነበር። ታዲያ ሳምሶን ከመጸነሱ በፊት፥ የእግዚአብሄር መልአክ ማኑሄ ለሚባል ሰውና መካን ለነበረችው ሚስቱ ተገልጦ፥ ይህቺ መካን ሴት ወንድ ልጅ እንደምትወልድ፥ ይሄ ልጅም፥ በየጊዜው ከሚወለዱት ልጆች ለየት ያለ እንደሆነ፥ ከእናቱ ማህጸን ጀምሮ ለእግዚአብሄር የተለየ ናዝራዊ እንደሚሆን፥ በራሱ ላይ ምላጭ እንደማይደርስበት፥ ይሄንን ለእግዚአብሄር የተለየ ልጅ ለመውለድ ደግሞ መብላትና መጠጣት ስለሌለባት ነገር ጭምር ነው የነገራት። ሳምሶን እኮ እናቱ እንኳን ስለ እርሱ የተቀደሰችለት አስደናቂ የእግዚአብሄር አላማ ያለበት ሰው ነበር። መልአኩ ታዲያ ቀጠል አረገና “ይሄ ከአንቺ የሚወለደው ልጅ፥ የእስራኤልን ህዝብ ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን የሚጀምር ነው” በማለት እግዚአብሄር በዚህ ልጅ ህይወት ላይ ያለውን ዋናና ትልቁን አላማ ሳይነግራት አልሄድም። አይገርማችሁም? እግዚአብሄር እኮ እኛ እንኳን በእናታችን ማህጸን ከመጸነሳችን በፊት ነው በህይወታችን ሊሰራ ያሰበውን አላማ ያቀደው። ሁላችንም ከመወለዳችን በፊት፥ እግዚአብሄር በህይወታችን ሊሰራ ያሰበውን አላማ በሙሉ ጽፎታል። አላማን ማወቅ ማለት፥ ይሄ እግዚአብሄር ሳይፈጥረን በፊት በህይወታችን ሊሰራ ያሰበውን ሀሳቡን ማግኘት ማለት ነው። ህይወታችን ትክክለኛውን እርካታ የሚያገኘው፥ ይሄንን አላማ አግኝቶ፣ በዚህ አላማ መመራት ሲጀምር ነው። በዚሁ አጋጣሚ፥ እዚሁ ዌብ ሳይቴ ላይ “አላማ” በሚል ርእስ የጻፍኩትን ጽሁፍ፥ ፈልጋችሁ እንድታነቡት እጋብዛችኋላሁ። ታዲያ ከላይ እንደተነጋገርነው፥ እግዚአብሄር የእስራኤልን ህዝብ አሳልፎ ከሰጣቸው ከፍልስጥኤማውያን ግዛት ለማዳን ሲያስብ፥  ይሄንን ሀሳቡን ለመፈጸም የፈጠረው ሰው ሳምሶን ነበር። የሳምሶን ትልቁ የህይወት አላማ፥ ለእግዚአብሄር ራሱን ለይቶ ናዝራዊነቱን በመጠበቅ፥ የእስራኤልን ህዝብ፥ ተላልፈው ከተሰጡበት ከፍልስጥኤም ህዝብ ባርነት ነጻ ማውጣት ነው። ሳምሶን ናዝራዊ ነው። ናዝራዊ ማለት ለእግዚአብሄር የተለየ ማለት ሲሆን፥ በዘሁልቁ ምእራፍ 6 ላይ፥ እግዚአብሄር ለእስራኤል ህዝብ በሰጣቸው ህግና ስርአት መሰረት፥ ናዝራዊ የሆነ ሰው፥ በጸጉሩ ላይ ምላጭ የማይደርስበት፣ ወይን ጠጅና የሚያሰክር ነገር የማይጠጣ፣ በፍጹም የሞተ ነገር ጋር የማይቀርብ፥ እንዲሁም ብዙ ከናዝራዊነት ጋር እግዚአብሄር ለእስራኤል ህዝብ የሰጣቸውን ትእዛዛት የሚጠብቅ ሰው መሆን አለበት። እነዚህ እንግዲህ ከአንድ ናዝራዊ ከሆነ ሰው የሚጠበቁ የህይወት ስርዓቶች ናቸው። እኛ የህይወት ዘመን ናዝራውያኖች ነን። ለእግዚአብሄር የተለየን ህዝቦች ነን። ልክ እግዚአብሄር በዘሁልቁ መጽሀፍ ላይ ናዝራዊ ለሆኑ ሰዎች እንደሰጠው ስርአትና ህግ፥ ለእኛ ደግሞ፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ከሰጠን ህይወት ጋር የምንተዳደርባቸው ህጎች አሉን። ሳምሶን ናዝራዊ ነህ የተባለው፥ ላዩ ላይ ከነበረው ትልቅ የእግዚአብሄር መንፈስና ሀይል የተነሳ ነው። ዛሬ ልክ እንደ ሳምሶን ዘመን የእግዚአብሄር መንፈስ በላያችን እየመጣ የሚሄድ ሳይሆን፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ስራ፥ በውስጣችን ሊኖር የዘላለም መኖሪያዎቹ አርጎናል። በየቀኑ በውስጣችን ተሸክመን የምንንቀሳቀሰው፥ ቅዱስ የሆነውን የእግዚአብሄርን መንፈስ እንደሆነ በማወቅ፥  በውስጣችን ላለው ለዚህ የከበረ መንፈስ ክብር እየሰጠን፥ በዚህች ምድር እንድንመላለስ ፍጹም የሆነው የእግዚአብሄር ሀሳብና ፈቃድ ነው። ሀያ አራት ሰአት በውስጣችን የሚኖር፣ የእግዚአብሄርን ቃል የሚተረጉምልን፣ የሚያስተምረን፣ ወደ እውነት ሁሉ የሚመራን፣ የሚቀድሰን፣ ከስህተት መንገድ ሁሉ የሚመልሰን፣ ከሀዘናችን የሚያጽናናን፣ በነገር ሁሉ የሚረዳን የእግዚአብሄር መንፈስ በውስጣችን አለ። በላያችን የተሸከምነው የእግዚአብሄርን ስም ነው። በውስጣችን የተሸከምነው ደግሞ፥ የእግዚአብሄርን መንፈስ ነው። በጣም ውድ ውድ ነገሮችን ተሽክመን፥ ርካሽ ቦታዎች ራሳችንን ማስገኘት አያዋጣንም። እግዚአብሄር፥ በተለያዩ ሰዎች ልዩ ልዩ ባህሪውን የገለጠ ሲሆን፥ በሳምሶን ውስጥ፥ ብርታቱንና ሀይሉን እንዲሁም ማስፈራቱን ገልጦአል። መጽሀፍ ቅዱሳችን ላይ ስናነብ፥ አንዳንድ ሰዎች፥ የእግዚአብሄር መንፈስ ሲወርድባቸው ትንቢትን ይናገራሉ። አንዳንዶች ደግሞ መገለጥና ራእይን ያያሉ:: ሌሎች ደግሞ ልዩ ልዩ በሆነ ልሳንና ሰማያዊ ቋንቋዎች ያወራሉ። ሳምሶን ግን የእግዚአብሄር መንፈስ ሲወርድበት፥ ሀይለኛ ነበር የሚሆነው። በእግዚአብሄር መንፈስ ውስጥ ወደ ሳምሶን ይወርድ የነበረው መለኮታዊ የሆነ የእግዚአብሄር ሀይል ነበር። አይታችሁት ከሆነ፥ ልክ የእግዚአብሄር መንፈስ በላዩ ላይ ሲወርድ፥ ይነሳና ሰው ጠቦትን እንደሚቆራርጥ፥ ያለ ምንም መሳሪያ በእጁ ብቻ አንበሳውን ይቆራርጠው ነበር። ይሄድና የእግዚአብሄር ህዝብ ጠላቶች የሆኑትን ፍልስጥኤማውያንን ይጨርሳቸው ነበር። የእግዚአብሄር መንፈስ ወደ እኛ በሀይልና በሙላት የሚመጣው፥ የተፈጠርንበትን አላማ እንድናገለግል ሀይል ሊሰጠን ነው። የእግዚአብሄር መንፈስ በሀይልና በሙላት ወደ እኛ የሚመጣው የእግዚአብሄርን ሀሳብ በእኛ ውስጥ ለመፈጸም ነው። መንፈስ ቅዱስ በእኛ ላይ በሀይልና በተለየ መንገድ ሲመጣ የምናረጋቸው ነገሮች፥ አላማዎቻችንን የሚያመለክቱ ናቸው። ይሄ የእግዚአብሄር መንፈስ በሀይል ወደ እኔ ሲመጣ ወዴት ነው የሚወስደኝ? በዝማሬ ነው የሚሞላኝ? አይኖቼን ከፍቶ መንፈሳዊ ሚስጥራትን ነው የሚያሳየኝ? የቃሉን መገለጥ ነው የሚሰጠኝ? ምን ሳረግ ነው ራሴን የማገኘው? ብለን መጠየቃችን እግዚአብሄር በህይወታችን ሊሰራ ያሰበውን ነገር፥  ከሚያመለክቱን ትልልቅ ምልክቶች ውስጥ አንዱ ነው። “እግዚአብሄርም የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በሀይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያቢሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፣ እግዚአብሄር ከእርሱ ጋር ነበረና።” ሀዋ ስራ 10:38 ሳምሶን በህይወቱ ላይ እግዚአብሄር ካለው አላማ አንጻር፥ በህይወቱ ላይ የተገለጠው የእግዚአብሄር ሀይል፥ በዙሪያው ያሉትን በሺዎች የሚቆጠሩ የፍልስጤም ህዝቦች ያንቀጠቅጥ ነበር። አይገርማችሁም?  እግዚአብሄር እኮ ለመስራት አንድ ሰው ነው የሚበቃው። አንድ የእስራኤልን ህዝብ ወክሎ በቆመ ሰው ውስጥ፥ አንድ ሙሉ ሀገርን ያናውጣል። እግዚአብሄር ጠላቶቹን ለመበቀል ሲነሳ፥ የሚፈልገው አንድ ሰው ነው። ብዙ ሆነን ሀይልና ብርታት እንድናዋጣለት አይፈልግም። ይልቁንም አንድ በእርሱ ትእዛዝና ፈቃድ ውስጥ ለመኖር በቆረጠ ሰው ህይወት፥ ሀገር የሚያንቀጠቅጠውን ሀይሉን ይገልጣል። ከዚያ ሙሉ ክብሩን እራሱ ይወስዳል። ሳምሶንን እንደምታውቁት፥ ላዩ ላይ ከነበረው የእግዚአብሄር ሀይል የተነሳ፥ የከተማን በር ገንጥሎ ከተሸከመ በኋላ፥ ቁልቁለት ሳይሆን ተራራ ላይ በመውጣት የከተማውን በር ተራራው ጫፍ ላይ ወስዶ የሚጥል፥  አስረነዋል ሲሉ ያሰሩበትን ጠንካራ ገመድ፥ እሳት እንደ ሸተተው የተልባ እግር ማሰሪያቸውን በጣጥሶ የሚነሳ፥ የእግዚአብሄርን ህዝብ ጠላቶች ግራ አጋብቶ፥ ራስ ምታት የሆነባቸው ሰው ነበር።  ይሄ ህዝብ ተሰብስቦ ያልቻለው እግዚአብሄር  ሀያል አርጎ ሀይሉን የገለጠበት እልፍ ገዳይ፥ በአንዲት ሴት እጅ መውደቁና ታሪኩ እንዲህ ማብቃቱ አይገርማችሁም?  የሳምሶን ህይወት መጨረሻው በደሊላ እጅ ይለቅ እንጂ፣ የሳምሶን ውድቀት ግን  የጀመረው ደሊላ ጋር አይደለም። ታሪኩ የተጻፈልን ለትምህርታችን እንደመሆኑ መጠን፥ ከሳምሶን ህይወት የምንማረው ትልቁ ትምህርት ጥንቃቄና ማስተዋል ምን ያህል ህይወታችንን እንደሚጠብቅ ነው። ሳምሶን፥ የህይወቱን አካሄድ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በደምብ ስታዩት፥ የተጠራበት ናዝራዊ የመሆን ህይወት የሚጠይቀውን ስርዓት፥ በአግባቡ እየተከተለ የሚሄድ ሰው አልነበረም። ከላይ በዘሁልቁ መጽሀፍ ላይ እንዳነበብነው፥ እግዚአብሄር ለህዝቡ ከሰጣቸው የናዝራዊነት ህጎች አንዱ፥ የሞተ ነገር ጋር ወይንም ሬሳ ጋር አለመቅረብ ነው። ታሪኩን ካስታወሳችሁት፥ ሳምሶን የእግዚአብሄር መንፈስ ወርዶበት የቆራረጠውን የአንበሳ ሬሳ ለማየት ፈቀቅ በማለትና፥ የሞተው የአንበሳ ሬሳ ውስጥ ያየውን ማር በእጁ በመውሰድ፥ መንገድ ለመንገድ እየበላ እንደሄደ መጽሀፍ ቅዱስ ጽፎልናል። እቤቱ ሲደርስ ደግሞ፥ ማሩን ለእናትና ለአባቱ ቢሰጣቸውም፣ ማሩን ከሞተ የአንበሳ ሬሳ ውስጥ እንዳመጣው ግን አልነገራቸውም በማለት መጽሀፍ ቅዱስ በግልጽ ጽፎልናል። ብዙ ጊዜ ስናወራ “ከሞተ አንበሳ ውስጥ ማርን የሚያወጣ አምላክ” እያልን እናወራለን እንዘምራለን። እውነት ነው፥ እግዚአብሄር ምንም የማይሳነው አምላክ ነው። ከዚህ ነገር ውስጥ የምንማረው ትልቁ ነገር ግን፥ ሰይጣን እኛን ወደ ተሳሳተ ቦታ ለመሳብ፥ ትክክል ያልሆኑ ነገሮች ውስጥ፥ ሊስቡን የሚችሉ ነገሮችን ሊያስቀምጥ መቻሉ ነው። ሳምሶን ወደ ሬሳው ጋር ባይቀርብ ማሩን ባላየው፣ ለመብላትም ባልተመኘው ነበር። ትልቁ ስህተቱ አትቅረብ

Article

ጠቢብ

Home Blog Book About Contact X Order Book ጊዜ Audio መስራት የምፈልጋቸው ብዙ ነገሮች አሉ። ጊዜዬንና ሰአቴን የሚፈልጉ ብዙ ነገሮች ህይወቴ ላይ አሉ። በአንዱ ነገር ውስድ እልና ሌሎቹን ህይወቴ ላይ ያሉ አስፈላጊ ነገሮች ችላ ስላቸው እራሴን አገኘዋለሁ። ከዚያ ደግሞ ሀላፊነቶቼን በትክክል እየተወጣሁ እንዳልሆነ አስቤ አዝናለሁ። በዚህ የህይወት ጎዳና ውስጥ እያለሁ ነው አንድ ቀን ወረቀትና እስክሪፕቶ አውጥቼ በህይወቴ ላይ በጣም አስፈላጊና ጊዜዬ ይገባቸዋል የምላቸውን ነገሮች በዝርዝር ለመጻፍ ውስጤ የተመራው። አንደኛ ሁለተኛ ሶስተኛ እያልኩ ዝርዝሮቹን በሙሉ ጻፍኩ። ከዚያ ደግሞ ለዘረዘርኳቸው ነገሮች በሙሉ በሳምንቴ ውስጥ ምን ያህል ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው ዘርዝሬ ጻፍኩ። ከዚያ እነዚህን ነገሮች በቀናቶቼ ውስጥ በምን በምን ሰአት ውስጥ እንደማደርጋቸው ውሳኔ ከሰጠሁ በኋላ እግዚአብሄር በረዳኝ መጠን ውሳኔዬን ተከትዬ ለነገሮቹ በሰጠኋቸው ጊዜያቶች ውስጥ መመራት ስጀምር፥ ውጤቱን በጣም ወደድኩት። ህይወቴ ሚዛናዊነቱን እየጠበቀ፣ ሀላፊነቶቼ በሙሉ የሚገባቸውን ጊዜና ትኩረት እያገኙ ስለመጡ በጊዜዬ አጠቃቀም ደስተኛ እየሆንኩኝ መጣሁ።  እግዚአብሄር የሰውን ፊት አይቶ እንደማያደላው ማንነቱ መጠን፥ ለሰዎች ሁሉ እኩል አርጎ ከሰጣቸው ስጦታዎች ውስጥ አንዱ ነው ጊዜ። ሀብታሙም ደሀውም፣ ወንዱም ሴቱም፣ ትልቁም ትንሹም፣ የተማረውም ያልተማረውም እግዚአብሄር በየቀኑ ከሰጠው የ24 ሰአት ስጦታ አልጎደለም። ለሁሉም እኩል የተሰጠ ስጦታ ይሁን እንጂ ግን ሰው ሁሉ ጊዜን የሚያይበት መንገድ የተለያየ ነው። ለአንዳንዱ በሰአትና በደቂቃ ከፋፍሎ ያሰበውን ሁሉ የሚያሳካበት፣ እቅድና ምኞቶቹን እውን የሚያረግበት የስኬት መንገዱ ነው። ለሌላው ደግሞ ወደ ጎን ጠጋ ብሎ ቆሞ፥ እለፍ እለፍ ጠጋ ልበልልህ እያለ ቆሞ የሚያሳልፈው ተራ ነገሩ ነው። ኸረ ቆይ እንደውም ጊዜው ትንሽ ቆየት ቢልም አንድ ቃለ ምልልስ እየሰማሁ እግዜር ማስተዋል የሰጠው ታዳጊ ወጣት ጊዜን ሲያብራራ ያለውን ልንገራችሁ። በዚህ ምድር ላይ ሶስት አይነት ሰዎች አሉ አለ። የመጀመሪያዎቹ ጊዜን የሚጠቀሙ ናቸው። እነዚህ ሰዎች ጊዜ ውስጥ ያለው ውድነት የገባቸው፣ እቅድና ፕሮግራም እያወጡ የሚሰሩ ናቸው። መነሻና መድረሻ ያላቸው እንዲሁም ምን ማድረግ እንደሚፈልጉ የሚያውቁ ሰዎች ናቸው። ሁለተኞቹ ደግሞ ጊዜ የሚጠቀምባቸው ሰዎች ናቸው። እነዚህ ምንም እቅድና ፕሮግራም ስለሌላቸው ጊዜው ካመጣው ነገር ሁሉ ጋር አብረው የሚሄዱ፣ ቀናቸው ላይ ኑ ካላቸው ነገር ሁሉ ጋር አብረው የሚሄዱ ናቸው። ሶስተኞቹ ሰዎች ደግሞ ጊዜን የሚያሳልፉ ናቸው። እነዚህ የነ ፌስ ቡክ ወዳጆች፣ ጊዜን በምን ልጠቀመው ብለው ጊዜን ስለመጠቀም ሳይሆን ጊዜን ስለማሳለፍ የሚጨነቁ ሰዎች ናቸው ብሎ የገለጸው ነገር ሁሌ ትዝ ይለኛል። እናንተ ጊዜን እንዴት ነው የምታዩት? እኔ ጊዜን ሳስብ ቶሎ ብሎ ወደ ሀሳቤ የሚመጣው ዘላለም ነው። ብዙ በህይወት አውቃቸው የነበሩ ዛሬ ግን የዚህች ምድር ጊዜያቸው አልቋል ተብለው ወደውም ሆነ ሳይወዱ ከዚህች ምድር የተሰናበቱ ሰዎችን አውቃለሁ። እነዚህ ሰዎች የሆነ ወቅት ላይ እዚህች ምድር ላይ የሚቆዩበት ጊዜ የሚባል እድል ተሰጥቷቸው የነበሩ ሰዎች ናቸው። አሁን ግን እድሉን መልሰው ቢፈልጉት እንኳን አያገኙትም። እነዚህ ሰዎች ታዲያ ተሰቷቸው በነበረው የምድር ጊዜ ያደረጓቸው ነገሮች፥ ዘላለማቸውን ላይ መልካም ወይንም መልካም ያልሆነ ተጽእኖን የሚፈጥር ነው። ሌላው ቀርቶ በኢየሱስ ክርስቶስ ድህነትን ቢያገኙም እንኳን፥ ክርስቶስን ካገኙ በኋላ ያላቸው የሕይወት አካሄድ እና በተሰጣቸው ጊዜ ያከናወኗቸው ነገሮች፥ በእግዚአብሔር ፊት የሚገመገም ነው።  በተሰጣቸው ምድራዊ ጊዜ በብዙ ዋጋ መክፈል የእግዚአብሄርን ሀሳብ ሲኖሩና ሲያገለግሉ የነበሩ እንደ እነ ጳውሎስ ያሉ ሰዎችና ከዳኑ በኋላ እንደፈለጉ የኖሩ ሰዎች በዘላለም ውስጥ አንድ አይነት ቦታ እንደሌላቸው መጽሀፍ ቅዱሳችንም ይናገራል። እንዲያውም በጭንቅ እንደሚድኑ ይሆናሉ የሚላቸው ሰዎችም አሉ። በአንጻሩ ደግሞ በተሰጣቸው ጊዜ የእግዚአብሔርን ሐሳብ በብዙ ትጋት እና ዋጋ መክፈል ያገለገሉ ሰዎች በክብርና በዘላለማዊ ሽልማት የዘላለም ብድራታቸውን ከራሱ ከጌታ እጅ እንደሚቀበሉ ቃሉ ይናገራል። እግዚአብሄር ለዚህ ክብር ያብቃችሁ። የሆነ ደህና ስራ ሰርተን እኮ መድረክ ላይ ወጥተን በሰው ፊት መሸለም እራሱ የሆነ ስሜት ካለው፣ በብዙ መላእክቶችና ቅዱሳን ፊት በብዙ ክብር ከዘላለም አምላክ ከእግዚአብሄር እጅ ሽልማት መቀበል ምን ይመስል ይሆን?  በምድር ላይ የተሰጠኝን ጊዜ ሳስብ፥ ዘላለምን አብሬ ስለማስብ እግዚአብሄር የሰጠኝን ውድ የጊዜ ስጦታ በአግባቡ እንድጠቀምበት ይረዳኛል። የእናንተን አላውቅም እኔ ግን የምሞትበት ቀን ላይ ምንም አይነት ቁጭት ውስጤ እንዲኖር አልፈልግም። የዛን ቀን በተሰጠኝ ጊዜ ውስጥ ስላልሰራኋቸው ነገሮች በማሰብ ጸጸት እንዲሰማኝ አልፈልግም። እንዲሰማኝ የምፈልገው ልክ ጳውሎስ ሊሞት ሲል ይሰማው የነበረው ደስታ እና እግዚአብሄርን ለማየት ያለ ጉጉት ነው። ይሄ አይነቱ ጸጸት የሌለበት መጨረሻ ሊኖረን የሚችለው ደግሞ በተሰጠን ጊዜ መስራት የሚገባንን ነገር ሰርተን ስንጨርስ ነው።  ለምሳሌ፥ በዚህች ምድር ላይ የቀራችሁ 6 ወራቶች ብቻ ናቸው ብንባል፥ ዛሬ የምንኖረውን አይነት ኑሮ የምንኖር ይመስላችኋል? ቅድሚያ መስጠት ስላለብንና ስለሌለብን ነገሮች ደግመን የምናስብ አይመስላችሁም? እያንዳንዱን ቀን እግዚአብሄርን ከ6 ወር በኋላ እንደምናየው እያሰብን በፊቱ መቆማችንን አውቀን እርሱ ዋጋ ለሚሰጣቸው ነገሮች ዋጋ እየሰጠን እያንዳንዱን ቀናቶቻችንን ከዘላለም አንጻር የምንጠቀምባቸው አይመስላችሁም? ታዲያ ግን ለመኖር 6 ወር ብቻ እንዳልቀረን እርግጠኛ የሚያረገን ነገር ምንድነው? ምንድነው ረጅም አመታቶች እንደምንኖር የሚያስመካን? ጤነኛ መሆናችን? ጤነኛ ሆነው ይኖሩ የነበሩ ወደ ጌታ የሄዱ ሰዎችን አናውቅም? ወጣትነታችን ነው? ወጣት ሆነው እንዲያውም ከእኛ በእድሜ ያነሱ ሰዎች በድንገት ሲሄዱ አላየንም? ያለን ገንዘብ ሀብት፣ አካባቢያችን ያሉ ብዙ ወዳጆች፥ እግዚአብሔር ይወስን እንጂ እነዚህ አንዳቸውም እግዚአብሔር ከወሰነልን ቀን ሊያሳልፉን አይችሉም። እሺ እኛ ሳንሄድ ደግሞ ኢየሱስስ ድንገት ቢመጣስ? የምመጣው እንደ ሌባ ድንገት ነው ማለቱ ሁልጊዜ የተዘጋጀ ህይወት እንዲኖረንና የሰጠንን ጊዜ በአግባቡ እንድንጠቀምበት ለማሳሰብ አይመስላችሁም?  መቼም ስለጊዜ አጠቃቀም ካነሳን፥ በዚህ ምድር ላይ የተሰጠውን ጊዜ በሙሉ በአግባቡ ተጠቅሞ እግዚአብሄርን ስላከበረው ትልቁ ምሳሌያችን ስለ ክርስቶስ ሳናነሳ ልናልፍ አንችልም። ወደ ምድር የመጣበትን አላማ ጠንቅቆ ማወቁ፣ የተሰጠውን ጊዜ በአግባቡ እንዲጠቀምበት አርጎታል። ምንም ያባከነው ጊዜ አልነበረም። ትርፍ ጊዜ አልነበረውም። መቼ ለጸሎት ጊዜ መውሰድ እንዳለበት ያውቃል፣ መቼ መስራት እንዳለበት ያውቃል፣ መቼ ወደ ምድረበዳ ሄዶ ማረፍ እንዳለበት ያውቃል፣ መቼ ማገልገል እንዳለበት ያውቃል፣ ሌላው ቢቀር መቼ ዝም ማለትና መቼ መልስ መስጠት እንዳለበት እራሱ ጠንቅቆ ያውቃል። ጊዜውን በሚገባ መጠቀሙ ብቻ ሳይሆን፣ ለሚያደርገው ለየትኛውም ነገር፥ ትክክለኛውን ጊዜ ጠንቅቆ ያውቃል። አለምን ሁሉ ከዘላለም ጥፋት የሚያድን ስራ ቢሰራም፥ ይሄንን የሰዎችን ሁሉ ዘላለም የሚቀይር ስራ ለመስራት ከ33 አመት ተኩል በላይ አልፈጀበትም። በእነዚህ አጭር አመታቶች ውስጥ የመጣበትን አላማ አሳክቶ እንዲያልፍ ከረዳው ነገሮች አንዱ፥ ጊዜውን በአግባቡ መጠቀሙና የእያንዳንዱን ነገር ጊዜ ጠንቅቆ ማወቁ ነው። ኢየሱስ በዚህች ምድር ላይ ሲመላለስ፥ የዚህች ምድር ቆይታው በጣም አጭር እንደሆነች በልቡ እያሰበ ነው። የተመላለሰው የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ የመጣበትን አላማ እያሰበ ነው። እኛስ ጊዜን እንዴት እየተጠቀምንበት ይሆን? እያንዳንዱ ቀን በእድሜያችን ላይ ሲደመር፥ በዚህች ምድር ላይ የተሰጠን የጊዜ ገድብ ለመጠናቀቅ አንድ ቀን እየቀረበ እንደሆነ ብዙ ጊዜ ማስታወስ አለብን። ጊዜን በአግባቡ ለመጠቀም ከሚረዳን ነገሮች ውስጥ ሁለት ዋና ዋና ነገሮችን በአጭሩ እናንሳ፦  1ኛ. በሕይወታችን ላይ ያለውን የእግዚአብሔር አላማ ማወቅ፦ መቼም ጊዜን ተጠቀምን የሚባለው በጊዜ ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ስናደርግ ነው። እኛ ዘርዝሩ ብንባል አስፈላጊ ብለን የምንላቸውን ነገሮች አንድ ሁለት ሶስት እያልን እንዘረዝር ይሆናል። ነገር ግን ከዘላለም አንጻር ስንመለከተው፥ በሕይወታችን አስፈላጊ የሚባለው አንደኛው ነገር እግዚአብሔር እኛን የፈጠረበት አላማ ነው። ኢየሱስ ጊዜውን በሙሉ የሰጠው፥ ወደ ምድር ለመጣበት ወይንም እግዚአብሔር እርሱን ለላከበት አላማ ነበር። እኛስ ለምንድነው የተፈጠርነው? ምን ለማድረግ ነው የተላክነው? በዚህች ምድር ላይ በተሰጠን በዚህች ውስን ጊዜ ውስጥ እግዚአብሔር በሕይወታችን ሊያከናውን የፈለገው ዋና አላማ ምንድነው? በየትኛው አገልግሎት ውስጥ ነው የጠራኝ? በግል ሕይወቴስ ምን አደርግ ዘንድ ይፈልጋል የሚሉትን ጥያቄዎች መልስ ከእግዚአብሔር ማግኘታችን፥ ጊዜ እና ትኩረታችንን እዚያ ዋና አላማ ላይ በማድረግ በተሰጠን ጊዜ ውስጥ እጅግ በጣም

Article

ጊዜ

Home Blog Book About Contact X Order Book ጊዜ Audio መስራት የምፈልጋቸው ብዙ ነገሮች አሉ። ጊዜዬንና ሰአቴን የሚፈልጉ ብዙ ነገሮች ህይወቴ ላይ አሉ። በአንዱ ነገር ውስድ እልና ሌሎቹን ህይወቴ ላይ ያሉ አስፈላጊ ነገሮች ችላ ስላቸው እራሴን አገኘዋለሁ። ከዚያ ደግሞ ሀላፊነቶቼን በትክክል እየተወጣሁ እንዳልሆነ አስቤ አዝናለሁ። በዚህ የህይወት ጎዳና ውስጥ እያለሁ ነው አንድ ቀን ወረቀትና እስክሪፕቶ አውጥቼ በህይወቴ ላይ በጣም አስፈላጊና ጊዜዬ ይገባቸዋል የምላቸውን ነገሮች በዝርዝር ለመጻፍ ውስጤ የተመራው። አንደኛ ሁለተኛ ሶስተኛ እያልኩ ዝርዝሮቹን በሙሉ ጻፍኩ። ከዚያ ደግሞ ለዘረዘርኳቸው ነገሮች በሙሉ በሳምንቴ ውስጥ ምን ያህል ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው ዘርዝሬ ጻፍኩ። ከዚያ እነዚህን ነገሮች በቀናቶቼ ውስጥ በምን በምን ሰአት ውስጥ እንደማደርጋቸው ውሳኔ ከሰጠሁ በኋላ እግዚአብሄር በረዳኝ መጠን ውሳኔዬን ተከትዬ ለነገሮቹ በሰጠኋቸው ጊዜያቶች ውስጥ መመራት ስጀምር፥ ውጤቱን በጣም ወደድኩት። ህይወቴ ሚዛናዊነቱን እየጠበቀ፣ ሀላፊነቶቼ በሙሉ የሚገባቸውን ጊዜና ትኩረት እያገኙ ስለመጡ በጊዜዬ አጠቃቀም ደስተኛ እየሆንኩኝ መጣሁ።  እግዚአብሄር የሰውን ፊት አይቶ እንደማያደላው ማንነቱ መጠን፥ ለሰዎች ሁሉ እኩል አርጎ ከሰጣቸው ስጦታዎች ውስጥ አንዱ ነው ጊዜ። ሀብታሙም ደሀውም፣ ወንዱም ሴቱም፣ ትልቁም ትንሹም፣ የተማረውም ያልተማረውም እግዚአብሄር በየቀኑ ከሰጠው የ24 ሰአት ስጦታ አልጎደለም። ለሁሉም እኩል የተሰጠ ስጦታ ይሁን እንጂ ግን ሰው ሁሉ ጊዜን የሚያይበት መንገድ የተለያየ ነው። ለአንዳንዱ በሰአትና በደቂቃ ከፋፍሎ ያሰበውን ሁሉ የሚያሳካበት፣ እቅድና ምኞቶቹን እውን የሚያረግበት የስኬት መንገዱ ነው። ለሌላው ደግሞ ወደ ጎን ጠጋ ብሎ ቆሞ፥ እለፍ እለፍ ጠጋ ልበልልህ እያለ ቆሞ የሚያሳልፈው ተራ ነገሩ ነው። ኸረ ቆይ እንደውም ጊዜው ትንሽ ቆየት ቢልም አንድ ቃለ ምልልስ እየሰማሁ እግዜር ማስተዋል የሰጠው ታዳጊ ወጣት ጊዜን ሲያብራራ ያለውን ልንገራችሁ። በዚህ ምድር ላይ ሶስት አይነት ሰዎች አሉ አለ። የመጀመሪያዎቹ ጊዜን የሚጠቀሙ ናቸው። እነዚህ ሰዎች ጊዜ ውስጥ ያለው ውድነት የገባቸው፣ እቅድና ፕሮግራም እያወጡ የሚሰሩ ናቸው። መነሻና መድረሻ ያላቸው እንዲሁም ምን ማድረግ እንደሚፈልጉ የሚያውቁ ሰዎች ናቸው። ሁለተኞቹ ደግሞ ጊዜ የሚጠቀምባቸው ሰዎች ናቸው። እነዚህ ምንም እቅድና ፕሮግራም ስለሌላቸው ጊዜው ካመጣው ነገር ሁሉ ጋር አብረው የሚሄዱ፣ ቀናቸው ላይ ኑ ካላቸው ነገር ሁሉ ጋር አብረው የሚሄዱ ናቸው። ሶስተኞቹ ሰዎች ደግሞ ጊዜን የሚያሳልፉ ናቸው። እነዚህ የነ ፌስ ቡክ ወዳጆች፣ ጊዜን በምን ልጠቀመው ብለው ጊዜን ስለመጠቀም ሳይሆን ጊዜን ስለማሳለፍ የሚጨነቁ ሰዎች ናቸው ብሎ የገለጸው ነገር ሁሌ ትዝ ይለኛል። እናንተ ጊዜን እንዴት ነው የምታዩት? እኔ ጊዜን ሳስብ ቶሎ ብሎ ወደ ሀሳቤ የሚመጣው ዘላለም ነው። ብዙ በህይወት አውቃቸው የነበሩ ዛሬ ግን የዚህች ምድር ጊዜያቸው አልቋል ተብለው ወደውም ሆነ ሳይወዱ ከዚህች ምድር የተሰናበቱ ሰዎችን አውቃለሁ። እነዚህ ሰዎች የሆነ ወቅት ላይ እዚህች ምድር ላይ የሚቆዩበት ጊዜ የሚባል እድል ተሰጥቷቸው የነበሩ ሰዎች ናቸው። አሁን ግን እድሉን መልሰው ቢፈልጉት እንኳን አያገኙትም። እነዚህ ሰዎች ታዲያ ተሰቷቸው በነበረው የምድር ጊዜ ያደረጓቸው ነገሮች፥ ዘላለማቸውን ላይ መልካም ወይንም መልካም ያልሆነ ተጽእኖን የሚፈጥር ነው። ሌላው ቀርቶ በኢየሱስ ክርስቶስ ድህነትን ቢያገኙም እንኳን፥ ክርስቶስን ካገኙ በኋላ ያላቸው የሕይወት አካሄድ እና በተሰጣቸው ጊዜ ያከናወኗቸው ነገሮች፥ በእግዚአብሔር ፊት የሚገመገም ነው።  በተሰጣቸው ምድራዊ ጊዜ በብዙ ዋጋ መክፈል የእግዚአብሄርን ሀሳብ ሲኖሩና ሲያገለግሉ የነበሩ እንደ እነ ጳውሎስ ያሉ ሰዎችና ከዳኑ በኋላ እንደፈለጉ የኖሩ ሰዎች በዘላለም ውስጥ አንድ አይነት ቦታ እንደሌላቸው መጽሀፍ ቅዱሳችንም ይናገራል። እንዲያውም በጭንቅ እንደሚድኑ ይሆናሉ የሚላቸው ሰዎችም አሉ። በአንጻሩ ደግሞ በተሰጣቸው ጊዜ የእግዚአብሔርን ሐሳብ በብዙ ትጋት እና ዋጋ መክፈል ያገለገሉ ሰዎች በክብርና በዘላለማዊ ሽልማት የዘላለም ብድራታቸውን ከራሱ ከጌታ እጅ እንደሚቀበሉ ቃሉ ይናገራል። እግዚአብሄር ለዚህ ክብር ያብቃችሁ። የሆነ ደህና ስራ ሰርተን እኮ መድረክ ላይ ወጥተን በሰው ፊት መሸለም እራሱ የሆነ ስሜት ካለው፣ በብዙ መላእክቶችና ቅዱሳን ፊት በብዙ ክብር ከዘላለም አምላክ ከእግዚአብሄር እጅ ሽልማት መቀበል ምን ይመስል ይሆን?  በምድር ላይ የተሰጠኝን ጊዜ ሳስብ፥ ዘላለምን አብሬ ስለማስብ እግዚአብሄር የሰጠኝን ውድ የጊዜ ስጦታ በአግባቡ እንድጠቀምበት ይረዳኛል። የእናንተን አላውቅም እኔ ግን የምሞትበት ቀን ላይ ምንም አይነት ቁጭት ውስጤ እንዲኖር አልፈልግም። የዛን ቀን በተሰጠኝ ጊዜ ውስጥ ስላልሰራኋቸው ነገሮች በማሰብ ጸጸት እንዲሰማኝ አልፈልግም። እንዲሰማኝ የምፈልገው ልክ ጳውሎስ ሊሞት ሲል ይሰማው የነበረው ደስታ እና እግዚአብሄርን ለማየት ያለ ጉጉት ነው። ይሄ አይነቱ ጸጸት የሌለበት መጨረሻ ሊኖረን የሚችለው ደግሞ በተሰጠን ጊዜ መስራት የሚገባንን ነገር ሰርተን ስንጨርስ ነው።  ለምሳሌ፥ በዚህች ምድር ላይ የቀራችሁ 6 ወራቶች ብቻ ናቸው ብንባል፥ ዛሬ የምንኖረውን አይነት ኑሮ የምንኖር ይመስላችኋል? ቅድሚያ መስጠት ስላለብንና ስለሌለብን ነገሮች ደግመን የምናስብ አይመስላችሁም? እያንዳንዱን ቀን እግዚአብሄርን ከ6 ወር በኋላ እንደምናየው እያሰብን በፊቱ መቆማችንን አውቀን እርሱ ዋጋ ለሚሰጣቸው ነገሮች ዋጋ እየሰጠን እያንዳንዱን ቀናቶቻችንን ከዘላለም አንጻር የምንጠቀምባቸው አይመስላችሁም? ታዲያ ግን ለመኖር 6 ወር ብቻ እንዳልቀረን እርግጠኛ የሚያረገን ነገር ምንድነው? ምንድነው ረጅም አመታቶች እንደምንኖር የሚያስመካን? ጤነኛ መሆናችን? ጤነኛ ሆነው ይኖሩ የነበሩ ወደ ጌታ የሄዱ ሰዎችን አናውቅም? ወጣትነታችን ነው? ወጣት ሆነው እንዲያውም ከእኛ በእድሜ ያነሱ ሰዎች በድንገት ሲሄዱ አላየንም? ያለን ገንዘብ ሀብት፣ አካባቢያችን ያሉ ብዙ ወዳጆች፥ እግዚአብሔር ይወስን እንጂ እነዚህ አንዳቸውም እግዚአብሔር ከወሰነልን ቀን ሊያሳልፉን አይችሉም። እሺ እኛ ሳንሄድ ደግሞ ኢየሱስስ ድንገት ቢመጣስ? የምመጣው እንደ ሌባ ድንገት ነው ማለቱ ሁልጊዜ የተዘጋጀ ህይወት እንዲኖረንና የሰጠንን ጊዜ በአግባቡ እንድንጠቀምበት ለማሳሰብ አይመስላችሁም?  መቼም ስለጊዜ አጠቃቀም ካነሳን፥ በዚህ ምድር ላይ የተሰጠውን ጊዜ በሙሉ በአግባቡ ተጠቅሞ እግዚአብሄርን ስላከበረው ትልቁ ምሳሌያችን ስለ ክርስቶስ ሳናነሳ ልናልፍ አንችልም። ወደ ምድር የመጣበትን አላማ ጠንቅቆ ማወቁ፣ የተሰጠውን ጊዜ በአግባቡ እንዲጠቀምበት አርጎታል። ምንም ያባከነው ጊዜ አልነበረም። ትርፍ ጊዜ አልነበረውም። መቼ ለጸሎት ጊዜ መውሰድ እንዳለበት ያውቃል፣ መቼ መስራት እንዳለበት ያውቃል፣ መቼ ወደ ምድረበዳ ሄዶ ማረፍ እንዳለበት ያውቃል፣ መቼ ማገልገል እንዳለበት ያውቃል፣ ሌላው ቢቀር መቼ ዝም ማለትና መቼ መልስ መስጠት እንዳለበት እራሱ ጠንቅቆ ያውቃል። ጊዜውን በሚገባ መጠቀሙ ብቻ ሳይሆን፣ ለሚያደርገው ለየትኛውም ነገር፥ ትክክለኛውን ጊዜ ጠንቅቆ ያውቃል። አለምን ሁሉ ከዘላለም ጥፋት የሚያድን ስራ ቢሰራም፥ ይሄንን የሰዎችን ሁሉ ዘላለም የሚቀይር ስራ ለመስራት ከ33 አመት ተኩል በላይ አልፈጀበትም። በእነዚህ አጭር አመታቶች ውስጥ የመጣበትን አላማ አሳክቶ እንዲያልፍ ከረዳው ነገሮች አንዱ፥ ጊዜውን በአግባቡ መጠቀሙና የእያንዳንዱን ነገር ጊዜ ጠንቅቆ ማወቁ ነው። ኢየሱስ በዚህች ምድር ላይ ሲመላለስ፥ የዚህች ምድር ቆይታው በጣም አጭር እንደሆነች በልቡ እያሰበ ነው። የተመላለሰው የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ የመጣበትን አላማ እያሰበ ነው። እኛስ ጊዜን እንዴት እየተጠቀምንበት ይሆን? እያንዳንዱ ቀን በእድሜያችን ላይ ሲደመር፥ በዚህች ምድር ላይ የተሰጠን የጊዜ ገድብ ለመጠናቀቅ አንድ ቀን እየቀረበ እንደሆነ ብዙ ጊዜ ማስታወስ አለብን። ጊዜን በአግባቡ ለመጠቀም ከሚረዳን ነገሮች ውስጥ ሁለት ዋና ዋና ነገሮችን በአጭሩ እናንሳ፦  1ኛ. በሕይወታችን ላይ ያለውን የእግዚአብሔር አላማ ማወቅ፦ መቼም ጊዜን ተጠቀምን የሚባለው በጊዜ ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ስናደርግ ነው። እኛ ዘርዝሩ ብንባል አስፈላጊ ብለን የምንላቸውን ነገሮች አንድ ሁለት ሶስት እያልን እንዘረዝር ይሆናል። ነገር ግን ከዘላለም አንጻር ስንመለከተው፥ በሕይወታችን አስፈላጊ የሚባለው አንደኛው ነገር እግዚአብሔር እኛን የፈጠረበት አላማ ነው። ኢየሱስ ጊዜውን በሙሉ የሰጠው፥ ወደ ምድር ለመጣበት ወይንም እግዚአብሔር እርሱን ለላከበት አላማ ነበር። እኛስ ለምንድነው የተፈጠርነው? ምን ለማድረግ ነው የተላክነው? በዚህች ምድር ላይ በተሰጠን በዚህች ውስን ጊዜ ውስጥ እግዚአብሔር በሕይወታችን ሊያከናውን የፈለገው ዋና አላማ ምንድነው? በየትኛው አገልግሎት ውስጥ ነው የጠራኝ? በግል ሕይወቴስ ምን አደርግ ዘንድ ይፈልጋል የሚሉትን ጥያቄዎች መልስ ከእግዚአብሔር ማግኘታችን፥ ጊዜ እና ትኩረታችንን እዚያ ዋና አላማ ላይ በማድረግ በተሰጠን ጊዜ ውስጥ እጅግ በጣም

Article

ደውል

Home Blog Book About Contact X Order Book ደውል Audio አንዳንድ ጊዜ ቤቴ ውስጥ ቡና ሳፈላ፥ ጣሪያ ላይ ያለችው የእሳት አደጋ ደውል የቡናውን ጭስ ሰምታ ጩኸትዋን  ታቀልጠዋለች። በሩን ከፍቼ የቡናውን ጭስ ካላስወጣሁትማ፥ እልህ ይይዛታል መሰለኝ ብሶባት ነው ቁጭ የሚለው። ለነገሩ እሷ ምን ታርግ? ስራዋን እኮ በአግባቡ እየሰራች ነው። ኸረ እንደውም እሳት የተነሳ መስሏት፥ እኔኑ ከአደጋ ለማትረፍ እኮ ነው የምትጮኸው። ጭሱን ያስነሳሁት እኔው እራሴ መሆኔን አላወቀችም እንጂ የእውነት እሳት አደጋ ቢነሳ፥ በዚህ ጩኸትዋ ህይወቴን በማትረፏ እንደው ሰው ሆና ግምባሯ ላይ አንድ መቶውን ዶላር ብለጥፍላት እራሱ አይቆጨኝም።  በክርስትና ህይወታችን ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ አንዱ ስራው ልክ እንደዚህች የማንቂያ ደውል ይመስለኛል። ህይወታችን አደጋ ላይ ሲሆን ልባችን ውስጥ የሚያሰማን የማንቂያ ደውል አለ። በተለይ በሀጢያት ጎዳናዎች መጓዝ ስንጀምር፥ ሀጢያት ከእግዚአብሄር እንደሚለየን ስለሚያውቅ ልባችን ውስጥ ጮክ ብሎ ይጮሀል። “አደጋ ላይ ናችሁ!” እያለ የአደጋ ምልክት ያሰማናል። እግዚአብሄር ህይወት ስለሆነ ከህይወት እንዳንርቅና እንዳንጎድል የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል። ፍቅሩ እኮ ነው! ርህራሄው እኮ ነው! ዛሬ ዝም ካልነው ነገም እኛን ለመመለስ ተስፋ አይቆርጥም። ትልቁ አደጋ ግን የሚፈጠረው ድምፁን እየሰማን በጀመርናቸው የስህተት መንገዶች የቀጠልን ጊዜ ነው።  በሰው ልጆች ፈቃድ ውስጥ ብቻ የሚሰራ አምላክ ስለሆነ ማንንም በማስገደድ አያምንም። በፈቀድነው መንገድ ለመሄድ ልባችን ውስጥ ፈቃድን አስቀምጧል። ከመረጥናቸው የስህተት መንገዶች ጋር ግን አብሮ መጓዝ አይችልም። እኛን ለማትረፍ የሚጮኸውን የአደጋ ላይ ናችሁ ድምፅ ሰምተን ካልተመለስን፥ ለፍቃዳችን ሊተወን ይገደዳል። ይሄ አንድ ክርስቲያን የሚገባበት በጣም አደገኛ የሆነ ቦታ ነው። በስህተት ጎዳና ውስጥ ስንሄድ በውስጣችን የሚሰማን ምንም የወቀሳ ድምፅ ከሌለ፥ የእግዚአብሄርን ቃል መተላለፋችን ምንም አይነት ስሜት ካልሰጠን፥ ሰላምና ምቾት ካልነሳን እንደውም ምንም እንዳልተፈጠረ አይነት ስሜት ኖሮን በሰላም ወደሚቀጥለው ጉዳያችን ከገባን፥ አደጋ ላይ ነን! ትልቅ አደጋ ላይ ነን! ህይወታችን ላይ ያሉትን እንቅስቃሴዎች ሁሉ አቁመን መንገዶቻችንን መመርመር ያለብን በዚህ ጊዜ ነው። ቶሎ ሳይረፍድ በንሰሀ መመለስና አካሄዳችንን ከእግዚአብሄር ጋር ማስተካከል ያለብን በዚህ ጊዜ ነው።  ክርስቲያን በሀጢያት ስህተት ውስጥ ሊወድቅ አይችልም ወይ? ኸረ በደምብ ሊሳሳት ይችላል! እንደውም መፅሀፍ ቅዱስ እኮ ሀጢያተኞችን በምህረቱ ያፀደቀበትና የእግዚአብሄርን የፀጋ ጉልበት ያየንባቸው ሰዎች ስብስብ ነው። እነ ዳዊት ቢሆኑ መቼ ፍፁምነታቸው ሆነና እንደ ልቤ ያስባላቸው! ድምፁን ሰምተው ቶሎ መመለሳቸው አይደል እንዴ የእግዚአብሄርን ምህረት በህይወታቸው ፍፁም ያደረገው! ምህረቱ እኮ ነው በተሰጣቸው ዘመን ሁሉ የእግዚአብሄርን ሀሳብ አገልግለው እንዲያልፉ አቅም የሰጣቸው። ኸረ እንኳንም ሳቱ! እንኳንም ደግሞ ስህተታቸው ከስኬትና ከድላቸው ጋር አብሮ ተፃፈልን! የስህተታቸው አስከፊነት እኮ ዛሬ ለእኛም ተስፋ እንዳለን ነገረን። እንደ እነ ጳውሎስ አይነቶቹ አሳዳጆች ላይ እግዚአብሄር ያበዛው ትእግስት አይደል እንዴ ከስህተት በመመለስ ሩጫን መጨረስ ይቻላል የሚል መልእክት ያደረሰን! ክርስቲያን ይሳሳታል። በደምብ ይሳሳታል።  ነገር ግን ክርስቲያን በሀጢያት ውስጥ መኖር አይችልም። ሀጢያትን መኖሪያ ቦታው ማድረግ ግን አይችልም። እንደ ማንኛውም በክርስቶስ መዳንን እንደማያውቅ ሰው በሀጢያት ውስጥ ሊዝናና ግን አይችልም። ከሀጢያት አርነት ያወጣውና ውስጡ ያለው የህይወት መንፈስ ህግ አይፈቅድለትም። ከእግዚአብሄር በመወለዱ ሀጢያትን የሚቃወም መንፈስ በውስጡ አለ። የእግዚአብሄርን ዘር ስለተሸከመ ሀጢያትንና ውስጡ ያለውን የእግዚአብሄር ዘር ጎን ለጎን ማስኬድ አይችልም። አንዱን ይመርጣል። ወይ ከዚህኛው ወይንም ከዚያኛው ይሆናል። አንድ ሰው ማገልገሉ፥ ክርስቲያን የሚያደርጋቸውን ነገሮች ሁሉ ማድረጉ ከእግዚአብሄር ዘር ነው ሊያስብለው አይችልም። ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ እንደተባለው ማስታወቂያው ፍሬው ነው እንጂ የመድረክ ላይ አገልግሎቱም አይደለም። በከፍተኛ መሰጠትና ሀይል አገልግሎ ብዙዎችን ወደ እግዚአብሄር መንግስት ያመጣው ሀዋሪያው ጳውሎስ “እኔ ከሰበኩ በሗላ የተጣልኩ እንዳልሆን ስጋዬን እየጎሰምኩ አስገዛዋለሁ” ብሎ የግል ህይወቱንና አገልግሎቱን ነጣጥሎ ያየው፥ እግዚአብሄር አገልግሎታችንንና የግል ህይወታችንን ለያይቶ እንደሚመዝናቸው ስለገባው ነው። ለካ ክርስቲያን ነኝ እያሉ ኖር ኖሮ፥ አገልጋይ ነኝ ብሎ አገልግሎ አገልግሎ ህይወትን በትክክል ካልኖሩ፥ መጨረሻ ላይ መጣል የሚባል አደጋም አለ።  መዳናችን፥ በፀጋ ድነናል ብሎ ብቻ አያበቃም። ይሄው እራሱ ያዳነን ፀጋ፥ መጀመሪያ አለማዊ ምኞትንና ሀጢያትን ካስካደን በሗላ የሚያስተምረን ከሀጢያት ጋር መጋደልን ነው። በፅድቅና በቅድስና መኖርን ነው። እግዚአብሄርን በመምሰል እየኖርን የክርስቶስን መምጣት መጠበቅን ነው። ክርስቲያን ታጋይ ነው!  በእግዚአብሄር መንፈስና ፀጋ እየታገዘ፥ በስጋው ውስጥ ከሚኖረው ሀጢያት ጋር እየተጋደለ የሚኖር ተዋጊ እንጂ፥ ፀጋውን እየሄደበት ላለው የስህተት መንገድ እንደ ፈቃድ ተጠቃሚ  አይደለም።  አንድ ሴት ለመፀነስና ልጅ ለመውለድ ቢያንስ 9 ወር እንደሚያስፈልጋት፥ ፀንሳ መውለድዋ በጊዜ ሂደት ውስጥ የሚከናወን እንደሆነ ሁሉ፥ የስጋ ምኞትና የድፍረት ሀጢያት በጊዜ ሂደት ውስጥ ፀንሰው የሚወልዱት አንድ ነገር አለ። ሞት። ቤተክርስቲያን ውስጥ እየተመላለስን፥ የሞተ ወይንም ከእግዚአብሄር የተለየ ህይወት ሊኖረን ይችላል። ይሄ ደግሞ በክርስቶስ ያገኘነውን የዘላለም መዳን ሊያሳጣን የሚችል ነገር ስለሆነ፥ የተሰጠንን አንድና ድጋሚ እድል የሌለበት ህይወት በጥንቃቄ መኖር ማስተዋል ነው።    “Our true success in this life is being able to fulfill the purpose we were created for!” Icon-facebook Youtube Instagram for the Kingdom through Christ ! Scroll to top Blog Book About Contact ©2026, Hana Elias. All Rights Reserved Blog Book About Contact

Article

ይሉኝታ

Home Blog Book About Contact X Order Book ያእቆብ Audio ሰሞኑን የህይወት ታሪኩን በማሰላሰል ልቤን በጣም የገዛው ሰው ነው። መቼም ታሪኩን ምንም የማናውቀው ብንሆን እንኳን፥ ወይ በሰዎች ንግግር ውስጥ፥ ወይንም ደግሞ በህብረት ጸሎቶቻችን ውስጥ፥ የአብርሀም የይስሀቅ የያእቆብ አምላክ ተብሎ ሲጸለይ እንሰማለን። ያእቆብ የአብርሀም ልጅ የሆነው ይስሀቅ ከወለዳቸው መንታ ልጆች ውስጥ፥ ሁለተኛ ልጅ ሆኖ የተወለደው ልጅ ነው። እነዚህ መንታ ወንድ ልጆች፥ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ፥ ገና በእናታቸው ማህጸን ውስጥ ሆነው ነው መገፋፋትና በታገል የጀመሩት። እናታቸው ርብቃም ምንም የመጀመሪያዋ እርግዝና ይሁን እንጂ፥ በውስጧ አንድ ያልተለመደ ነገር እየሆነ እንዳለ ተረድታ፥ ግራ ስለገባት እግዚአብሄርን ምን እየሆነ እንዳለ ለመጠየቅ ሄዳ ነበር። “ሁለት ወገኖች በማህጸንሽ ናቸው። ሁለቱም ህዝብ ከሆድሽ ይከፈላሉ። ህዝብም ከህዝብ ይበረታል። ታላቁም ለታናሹ ይገዛል” በማለት የገዛ ሆዷ ውስጥ እየተከናወነ ያለውን ነገር፥ እግዚአብሄር በግልጽ ነግሯት ነበር። ርብቃ እኮ ታዲያ የምታውቅ የነበረው፥ ሁሉም ሴት ልጅን ለመውለድ እርጉዝ እንደሚሆነው እሷም እንዳረገዘች እንጂ፥ ሁለት ትልልቅ ሰራዊት የሚሆኑና ከአብርሀም ጀምሮ እግዚአብሄር ለአመታት ሲገባ የነበረውን ኪዳን የሚፈጽምባቸው፥ እንዲሁም ሁለት ትልልቅ ህዝብ የሚሆኑ ሰዎች በውስጥዋ እንዳሉ አታውቅም ነበር። አይገርማችሁም፥ አንዳንድ ጊዜ እኮ እግዚአብሄር ውስጣችን ምን እንዳስቀመጠ አናውቅም። የሚገርመው ታዲያ፥ እነዚህ ገና በእናታቸው ማህጸን ውስጥ መገፋፋትና መታገል የጀመሩ አራስ ልጆች፥ በተወለዱበትም ጊዜ፥ ታናሹ የሆነው ያእቆብ የታላቁን ተረከዝ ይዞ ነው ከእናቱ ሆድ የወጣው። እናት ወይንም አባት የሆናችሁ መቼም፥ ልጆቻችሁ ሲወለዱ እንዴት ትንንሾችና ለማቀፍ እንኳን የሚያሳሱ፣ በጣም የሚያሳዝኑ፥ ልባቸው ፍጹም ንጹህ የሆነ፣ በሁሉ ነገራቸው የእናንተን እርዳታና ድጋፍ የሚፈልጉ እንደሆኑ ታውቃላችሁ። ከኤሳውና ከያእቆብ ውጪ ከማህጸን መገፋፋትና መታገል የጀመረ ጽንስ ከዚህ በፊት ታይቶ አይታወቅም። ነገሩ ግን ትንቢታዊ እንደሆነ እና ከፊታቸው ያለውን የትግል ዘመናቶች የሚያሳይ መሆኑን፥ ወላጆቻቸውም በጊዜው አልተረዱም። የታሪኩን አካሄድ እንደምናውቀው፥ እነዚህ ልጆች ካደጉ በኋላ፥ ኤሳው በውጪ በማደን የሚተዳደር ሰው ሲሆን፥ ያእቆብ ደግሞ በቤት ከእናቱ ጋር የሚውል ልጅ ነበር። ታዲያ ከእለታት አንድ ቀን ያእቆብ የምስር ወጥ በሰራበት ቀን ነው ኤሳው ተርቦ ከውጪ የገባው። በጣም ከመራቡ የተነሳ የሚያስበው ስለ ምግብ ብቻ ነበር። “ያእቆብ በጣም ደክሞኛል፥ ደግሞም ርቦኛል፥ በናትህ ከሰራኸው የምስር ወጥ፥ ትንሽ እንድበላ ፍቀድልኝ።” ያእቆብም መለሰ “ችግር የለውም ወንድሜ። አንድ ነገር ብቻ እንደራደር፥ እኔ ከሰራሁት ቆንጆ የምስር ወጥ የምትበላውን እሰጥሀለሁ። በመጀመሪያ ግን አንተ አንድ ነገር ታረግልኛለህ። ብኩርናህን ትሰጠኛለህ።” ኤሳውም አለ “እኔ ለራሴ በረሀብና በድካም ልሞት ነው፥ ብኩርናዬ ለምኔ ናት?” በማለት ነው በምስር ወጥ ለመለወጥ የተስማማው። ኤሳው በጊዜው በከፍተኛ ድካምና የረሀብ ስሜት ውስጥ ቢሆንም፥ በምስር ወጥ የለወጠው ግን፥ በህይወቱ ላይ የነበረውን የእግዚአብሄርን ዘላለማዊ ኪዳን ነበር። እጁ ላይ የነበረው፥ ትውልዶችን አልፎ ዘላለም የሚቀጥል ትልቅ የእግዚአብሄር ፕሮግራም ነበር። ሰፊ የሆነ የእግዚአብሄር ሀሳብ ነው ከእጁ ያመለጠው። የድካሙና የረሀቡ ስሜት ያልፋል። ተሰጥቶት የነበረው እድል ግን፥ የማያልፍና ዘላለም የሚኖር የእግዚአብሄር በረከት ነበረ። ከዚያ በኋላ ይላል መጽሀፍ ቅዱስ፥ ድካሙ ካለፈ በኋላ፥ ረሀቡ ካለፈ በኋላ፥ በምግብ የለወጠውን ብኩርና በእምባ ቢፈልጋት እንኳን መልሶ አላገኛትም። ለንሰሀም ቦታ አላገኘም” በማለት የእግዚአብሄር ቃል ይነግረናል። አያናድድም? በእጃችን ላይ ያለው የከበረ ነገር፥ ዋጋው የሚገባን ካጣነው በኋላ ሲሆን አያናድድም? ምን አይነት ውድ ነገር እጃችን ላይ እንደነበረ የምናስተውለው ካጣነው በኋላ ሲሆን አያናድድም? ኤሳው በጊዜው አይምሮውን ሁሉ የተቆጣጠረው የረሀብ ስሜት፥ እጁ ላይ ያለውን ነገር ዋጋ እንዳይረዳ አርጎት ነበር። ከዚህ የምንወስደው ትልቁ ትምህርት፥ ውስጣችን ያሉት የተለያዩ ስሜቶች፥ አይምሮአችንን ገዝተው የእግዚአብሄርን ነገር እንዳያቀሉብን በጣም መጠንቀቅ እንዳለብን ነው። ስሜት በባህሪው፥ አይምሮአችንን በሙሉ የመቆጣጠርና በትክክል ማሰብ እንዳንችል የማድረግ ዝንባሌ አለው። አንድ ሰው ስሜታዊ ሲሆን፥ አይምሮው ሌላ ነገር ማሰብ አይችልም። የሚያስበው ስለዛ ስሜታዊ ስለሆነበት ነገር ብቻ ነው። ኤሳው ብኩርናውን ያሸጠው፥ በጊዜው አይምሮውን ተቆጣጥሮት የነበረው የረሀብ ስሜት ነው። ኤሳው በጊዜው ይሰማው የነበረውና አይምሮውን በሙሉ የተቆጣጠረው የረሀብ ስሜት፥ በእጁ ላይ የነበረውን ኪዳን ውድነት ማሰብ እንዳይችል አርጎት ነበር። ሌላኛው የስሜት ባህሪ ደግሞ፥ እንድንወስድ የሚገፋፋን እርምጃ መኖሩ ነው። ሰዎች ስለሆንን ብዙ ስሜቶች በህይወታችን ውስጥ ያልፋሉ። ስሜታዊ በሆንበት ሰአት ግን፥ ምንም አይነት ውሳኔ መወሰን የለብንም። ያ አይምሮአችንን የተቆጣጠረው የትኛውም አይነት ስሜት እስኪያልፍና፥ በትክክል ማሰብ እስክንችል ድረስ ከዚያ ስሜት በቶሎ እንድንወጣ የሚረዱንን ነገሮች እያረግን፥ ዝም ብለን መጠበቅ አለብን። የደስታ ቢሆን የሀዘን፣ የንዴት ቢሆን የብስጭት የትኛውም አይነት ስሜት ያልፋል። የደስታ ስሜት እንኳን ያልፋል። ስሜቱ ውስጥ ሆነን የምንወስናቸው ውሳኔዎች ግን፥ በከፍተኛ ሁኔታ የሚጎዱንና፥ በህይወታችን ብዙ ዋጋ የሚያስከፍሉን ሊሆኑ ይችላሉ። ከዚህም በላይ እግዚአብሄር ካልረዳን፥ ስሜታዊ ሆነን የምንወስናቸው ውሳኔዎች፣ ከትልቁ ከእግዚአብሄር ሀሳብና ፕሮግራም ሊያስወጡን ይችላሉ። ነገ ላይ የምንጸጸትባቸው ሊሆኑ ይችላሉ። እግዚአብሄር በእጃችሁ ላይ ያለውን ውድ ነገር እንድታስተውሉ በምትችሉበት ማስተዋል ይባርካችሁ። “እንዲሁም ኤሳው ብኩርናውን አቃለላት” እንደሚለው፥ በእጃችሁ ያለውን ትልቅ የእግዚአብሄር ሀሳብና ፕሮግራም ከማቃለል እግዚአብሄር ይጠብቃችሁ። ህይወታችሁ ላይ ያለውን የከበረ ነገር ውድ መሆን እንድታዩ፥ እግዚአብሄር አይናችሁን ይክፈትላችሁ። የያእቆብ ታሪክ በዚሁ እንዳለ፥ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ደግሞ ፍጹም አምላክ ሲሆን ፍጹም ሰው ሆኖ ወዲህች ምድር የመጣ አንድ ሰው አለ። ምንም የረሀብ ስሜት ቢቆጣጠረውም፥ ይሄ ስሜት ከእግዚአብሄር ሀሳብ ውጪ ያላስወጣው፥ ፍጹም አምላክ ደግሞም ፍጹም ሰው የሆነው  ኢየሱስ። 40 ቀናቶች ሙሉ ከጾመ በኋላ ቢራብም፥ የረሀብ ስሜቱን ለማስታገስ የተሰጠውን ጥሩ የሚመስል ሀሳብ ተቀብሎ፥ ድንጋዩን ዳቦ አላረገውም። የእግዚአብሄር ልጅ ከሆንክ ይሄንን ድንጋይ ዳቦ እንዲሆን በል በተባለው መሰረት፥ የእግዚአብሄር ልጅ መሆኑን ለማረጋገጥና ለማሳየት፥ አንድም ተጨማሪ ነገር አላረገም። ሰዎች፥ በውስጣችን ያለውን እውነተኛ ማንነት ከተረዱት መልካም ነው። አለበለዚያ ግን፥ እውነተኛ ማንነታችንን ለማሳየት፥ ምንም አይነት ተጨማሪ ነገሮችን እያረግን እንዲረዱን በማድረግ፥ ጊዜ ማቃጠል የለብንም። ልባችን፥ ማንነታችንን ሁሉ በሚያውቀው አምላክ ማረፍ አለበት። ኢየሱስ ድንጋዩን ዳቦ አርጎ በመብላት ረሀቡን ለማስታገስም ሆነ፥ ይሄንን ተአምራት አርጎ የእግዚአብሄርን ልጅ መሆኑን ለማሳየት፥ ስሜት አልገፋፋውም።  ስሜት ከእግዚአብሄር ሀሳብና ፕሮግራም አላስወጣውም። በስሜት ላይ ነገሰ እንጂ ስሜት አልነገሰበትም።  እንግዲህ የያእቆብን ታሪክ እንደምታውቁት፥ ከኤሳው ብኩርናውን ከተቀበለ በኋላ፥ በተንኮል ገብቶ ኤሳው ነኝ በማለት፥ ከአባቱ ከይስሀቅ ለኤሳው የሚገባውን በረከት ሁሉ በማታለል ተቀብሏል። ለማታለል የሄደበትም መንገድ ሰርቶለት፥ ማግኘት የሚፈልገውን ነገር በሙሉ አግኝቷል። ያእቆብ “ብኩርና” ውስጥ ያለውን በረከት በሙሉ ከአባቱ ተቀብሏል። አሁን ይሄ ኪዳን ኤሳውን አልፎ በያእቆብ ህይወት ቀጥሏል። ያእቆብ በተንኮል በመግባት፥ አንድ በኩር ልጅ ከአባቱ የሚቀበለውን በረከት በሙሉ ተቀብሏል። አላማውን በሙሉ አሳክቷል። ኪዳኑ በህይወቱ ሰርቷል። የእግዚአብሄር ፕሮግራም በህይወቱ ቀጥሏል። እግዚአብሄርም በዘመኑ ሁሉ ከእርሱ ጋር ሆኗል። እግዚአብሄር ጠብቆታል። በተለያየ ጊዜያትም በድምጽና በራእይ አናግሮታል። ምንም የእግዚአብሄር ኪዳን በህይወቱ ቢሰራም ግን፥ መዝራትና ማጨድ የእግዚአብሄር ህግ በመሆኑ፥ ያእቆብ ወንድሙንም ሆነ አባቱን በማታለል የሄደባቸው የማታለል መንገዶች፥ ህይወቱ ላይ እጅግ በጣም ብዙ ዋጋ አስከፍለውታል። የያእቆብን ህይወት ጠቅለል አርገን ስናየው፥ ህይወት ትግል የሆነበት ሰው ነበር። ያእቆብ ታጋይ ነው። ትግል የጀመረው ከእናቱ ማህጸን ሲሆን፥ ይሄ ትግሉ ዘመኑን ሙሉ ቀጥሏል። ከወንድሙ ጋር ይታገላል። ከአጎቱ ከላባ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ይታገላል። ኸረ ያእቆብ ከእግዚአብሄርም ጋር ታግሏል። ወንድሙን ኤሳውን በመሸሽ ወደ አጎቱ ወደ ላባ ቤት ሲሄድ ታዲያ፥ ከላባ ጋር ያሳለፋቸው አመታቶች፥ ዘርቶ የመጣውን የማታለል ዘር ያጨደበት ቦታ ሆኖበታል። ላባ ያእቆብን አስር ጊዜ ደሞዙን እየቀያየረ አታሎታል። 20 አመታቶችን በሚስቶቹ ምክኒያት ገዝቶታል። ያእቆብ አንዴ በበጎቹ፥ አንዴ ደግሞ በፍየሎቹ፥ ከላባ ጋር ባለመስማማት፥ ብዙ ከተማረረ በኋላ፥ ከወንድሙ ከኤሳው እንደኮበለለ፥ እንዲሁ ደግሞ ከአጎቱም ከላባ ኮብልሎ ወደ ሀገሩ ተመልሷል። ከዘመናት በፊት አታሎ የተለየውን ወንድሙን ኤሳውን እንደገና ለመገናኘት፥ በጣም በብዙ ጭንቀት ውስጥ

Scroll to Top