Author name: hanael

Article

ያእቆብ

Home Blog Book About Contact X Order Book ያእቆብ Audio ሰሞኑን የህይወት ታሪኩን በማሰላሰል ልቤን በጣም የገዛው ሰው ነው። መቼም ታሪኩን ምንም የማናውቀው ብንሆን እንኳን፥ ወይ በሰዎች ንግግር ውስጥ፥ ወይንም ደግሞ በህብረት ጸሎቶቻችን ውስጥ፥ የአብርሀም የይስሀቅ የያእቆብ አምላክ ተብሎ ሲጸለይ እንሰማለን። ያእቆብ የአብርሀም ልጅ የሆነው ይስሀቅ ከወለዳቸው መንታ ልጆች ውስጥ፥ ሁለተኛ ልጅ ሆኖ የተወለደው ልጅ ነው። እነዚህ መንታ ወንድ ልጆች፥ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ፥ ገና በእናታቸው ማህጸን ውስጥ ሆነው ነው መገፋፋትና በታገል የጀመሩት። እናታቸው ርብቃም ምንም የመጀመሪያዋ እርግዝና ይሁን እንጂ፥ በውስጧ አንድ ያልተለመደ ነገር እየሆነ እንዳለ ተረድታ፥ ግራ ስለገባት እግዚአብሄርን ምን እየሆነ እንዳለ ለመጠየቅ ሄዳ ነበር። “ሁለት ወገኖች በማህጸንሽ ናቸው። ሁለቱም ህዝብ ከሆድሽ ይከፈላሉ። ህዝብም ከህዝብ ይበረታል። ታላቁም ለታናሹ ይገዛል” በማለት የገዛ ሆዷ ውስጥ እየተከናወነ ያለውን ነገር፥ እግዚአብሄር በግልጽ ነግሯት ነበር። ርብቃ እኮ ታዲያ የምታውቅ የነበረው፥ ሁሉም ሴት ልጅን ለመውለድ እርጉዝ እንደሚሆነው እሷም እንዳረገዘች እንጂ፥ ሁለት ትልልቅ ሰራዊት የሚሆኑና ከአብርሀም ጀምሮ እግዚአብሄር ለአመታት ሲገባ የነበረውን ኪዳን የሚፈጽምባቸው፥ እንዲሁም ሁለት ትልልቅ ህዝብ የሚሆኑ ሰዎች በውስጥዋ እንዳሉ አታውቅም ነበር። አይገርማችሁም፥ አንዳንድ ጊዜ እኮ እግዚአብሄር ውስጣችን ምን እንዳስቀመጠ አናውቅም። የሚገርመው ታዲያ፥ እነዚህ ገና በእናታቸው ማህጸን ውስጥ መገፋፋትና መታገል የጀመሩ አራስ ልጆች፥ በተወለዱበትም ጊዜ፥ ታናሹ የሆነው ያእቆብ የታላቁን ተረከዝ ይዞ ነው ከእናቱ ሆድ የወጣው። እናት ወይንም አባት የሆናችሁ መቼም፥ ልጆቻችሁ ሲወለዱ እንዴት ትንንሾችና ለማቀፍ እንኳን የሚያሳሱ፣ በጣም የሚያሳዝኑ፥ ልባቸው ፍጹም ንጹህ የሆነ፣ በሁሉ ነገራቸው የእናንተን እርዳታና ድጋፍ የሚፈልጉ እንደሆኑ ታውቃላችሁ። ከኤሳውና ከያእቆብ ውጪ ከማህጸን መገፋፋትና መታገል የጀመረ ጽንስ ከዚህ በፊት ታይቶ አይታወቅም። ነገሩ ግን ትንቢታዊ እንደሆነ እና ከፊታቸው ያለውን የትግል ዘመናቶች የሚያሳይ መሆኑን፥ ወላጆቻቸውም በጊዜው አልተረዱም። የታሪኩን አካሄድ እንደምናውቀው፥ እነዚህ ልጆች ካደጉ በኋላ፥ ኤሳው በውጪ በማደን የሚተዳደር ሰው ሲሆን፥ ያእቆብ ደግሞ በቤት ከእናቱ ጋር የሚውል ልጅ ነበር። ታዲያ ከእለታት አንድ ቀን ያእቆብ የምስር ወጥ በሰራበት ቀን ነው ኤሳው ተርቦ ከውጪ የገባው። በጣም ከመራቡ የተነሳ የሚያስበው ስለ ምግብ ብቻ ነበር። “ያእቆብ በጣም ደክሞኛል፥ ደግሞም ርቦኛል፥ በናትህ ከሰራኸው የምስር ወጥ፥ ትንሽ እንድበላ ፍቀድልኝ።” ያእቆብም መለሰ “ችግር የለውም ወንድሜ። አንድ ነገር ብቻ እንደራደር፥ እኔ ከሰራሁት ቆንጆ የምስር ወጥ የምትበላውን እሰጥሀለሁ። በመጀመሪያ ግን አንተ አንድ ነገር ታረግልኛለህ። ብኩርናህን ትሰጠኛለህ።” ኤሳውም አለ “እኔ ለራሴ በረሀብና በድካም ልሞት ነው፥ ብኩርናዬ ለምኔ ናት?” በማለት ነው በምስር ወጥ ለመለወጥ የተስማማው። ኤሳው በጊዜው በከፍተኛ ድካምና የረሀብ ስሜት ውስጥ ቢሆንም፥ በምስር ወጥ የለወጠው ግን፥ በህይወቱ ላይ የነበረውን የእግዚአብሄርን ዘላለማዊ ኪዳን ነበር። እጁ ላይ የነበረው፥ ትውልዶችን አልፎ ዘላለም የሚቀጥል ትልቅ የእግዚአብሄር ፕሮግራም ነበር። ሰፊ የሆነ የእግዚአብሄር ሀሳብ ነው ከእጁ ያመለጠው። የድካሙና የረሀቡ ስሜት ያልፋል። ተሰጥቶት የነበረው እድል ግን፥ የማያልፍና ዘላለም የሚኖር የእግዚአብሄር በረከት ነበረ። ከዚያ በኋላ ይላል መጽሀፍ ቅዱስ፥ ድካሙ ካለፈ በኋላ፥ ረሀቡ ካለፈ በኋላ፥ በምግብ የለወጠውን ብኩርና በእምባ ቢፈልጋት እንኳን መልሶ አላገኛትም። ለንሰሀም ቦታ አላገኘም” በማለት የእግዚአብሄር ቃል ይነግረናል። አያናድድም? በእጃችን ላይ ያለው የከበረ ነገር፥ ዋጋው የሚገባን ካጣነው በኋላ ሲሆን አያናድድም? ምን አይነት ውድ ነገር እጃችን ላይ እንደነበረ የምናስተውለው ካጣነው በኋላ ሲሆን አያናድድም? ኤሳው በጊዜው አይምሮውን ሁሉ የተቆጣጠረው የረሀብ ስሜት፥ እጁ ላይ ያለውን ነገር ዋጋ እንዳይረዳ አርጎት ነበር። ከዚህ የምንወስደው ትልቁ ትምህርት፥ ውስጣችን ያሉት የተለያዩ ስሜቶች፥ አይምሮአችንን ገዝተው የእግዚአብሄርን ነገር እንዳያቀሉብን በጣም መጠንቀቅ እንዳለብን ነው። ስሜት በባህሪው፥ አይምሮአችንን በሙሉ የመቆጣጠርና በትክክል ማሰብ እንዳንችል የማድረግ ዝንባሌ አለው። አንድ ሰው ስሜታዊ ሲሆን፥ አይምሮው ሌላ ነገር ማሰብ አይችልም። የሚያስበው ስለዛ ስሜታዊ ስለሆነበት ነገር ብቻ ነው። ኤሳው ብኩርናውን ያሸጠው፥ በጊዜው አይምሮውን ተቆጣጥሮት የነበረው የረሀብ ስሜት ነው። ኤሳው በጊዜው ይሰማው የነበረውና አይምሮውን በሙሉ የተቆጣጠረው የረሀብ ስሜት፥ በእጁ ላይ የነበረውን ኪዳን ውድነት ማሰብ እንዳይችል አርጎት ነበር። ሌላኛው የስሜት ባህሪ ደግሞ፥ እንድንወስድ የሚገፋፋን እርምጃ መኖሩ ነው። ሰዎች ስለሆንን ብዙ ስሜቶች በህይወታችን ውስጥ ያልፋሉ። ስሜታዊ በሆንበት ሰአት ግን፥ ምንም አይነት ውሳኔ መወሰን የለብንም። ያ አይምሮአችንን የተቆጣጠረው የትኛውም አይነት ስሜት እስኪያልፍና፥ በትክክል ማሰብ እስክንችል ድረስ ከዚያ ስሜት በቶሎ እንድንወጣ የሚረዱንን ነገሮች እያረግን፥ ዝም ብለን መጠበቅ አለብን። የደስታ ቢሆን የሀዘን፣ የንዴት ቢሆን የብስጭት የትኛውም አይነት ስሜት ያልፋል። የደስታ ስሜት እንኳን ያልፋል። ስሜቱ ውስጥ ሆነን የምንወስናቸው ውሳኔዎች ግን፥ በከፍተኛ ሁኔታ የሚጎዱንና፥ በህይወታችን ብዙ ዋጋ የሚያስከፍሉን ሊሆኑ ይችላሉ። ከዚህም በላይ እግዚአብሄር ካልረዳን፥ ስሜታዊ ሆነን የምንወስናቸው ውሳኔዎች፣ ከትልቁ ከእግዚአብሄር ሀሳብና ፕሮግራም ሊያስወጡን ይችላሉ። ነገ ላይ የምንጸጸትባቸው ሊሆኑ ይችላሉ። እግዚአብሄር በእጃችሁ ላይ ያለውን ውድ ነገር እንድታስተውሉ በምትችሉበት ማስተዋል ይባርካችሁ። “እንዲሁም ኤሳው ብኩርናውን አቃለላት” እንደሚለው፥ በእጃችሁ ያለውን ትልቅ የእግዚአብሄር ሀሳብና ፕሮግራም ከማቃለል እግዚአብሄር ይጠብቃችሁ። ህይወታችሁ ላይ ያለውን የከበረ ነገር ውድ መሆን እንድታዩ፥ እግዚአብሄር አይናችሁን ይክፈትላችሁ። የያእቆብ ታሪክ በዚሁ እንዳለ፥ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ደግሞ ፍጹም አምላክ ሲሆን ፍጹም ሰው ሆኖ ወዲህች ምድር የመጣ አንድ ሰው አለ። ምንም የረሀብ ስሜት ቢቆጣጠረውም፥ ይሄ ስሜት ከእግዚአብሄር ሀሳብ ውጪ ያላስወጣው፥ ፍጹም አምላክ ደግሞም ፍጹም ሰው የሆነው  ኢየሱስ። 40 ቀናቶች ሙሉ ከጾመ በኋላ ቢራብም፥ የረሀብ ስሜቱን ለማስታገስ የተሰጠውን ጥሩ የሚመስል ሀሳብ ተቀብሎ፥ ድንጋዩን ዳቦ አላረገውም። የእግዚአብሄር ልጅ ከሆንክ ይሄንን ድንጋይ ዳቦ እንዲሆን በል በተባለው መሰረት፥ የእግዚአብሄር ልጅ መሆኑን ለማረጋገጥና ለማሳየት፥ አንድም ተጨማሪ ነገር አላረገም። ሰዎች፥ በውስጣችን ያለውን እውነተኛ ማንነት ከተረዱት መልካም ነው። አለበለዚያ ግን፥ እውነተኛ ማንነታችንን ለማሳየት፥ ምንም አይነት ተጨማሪ ነገሮችን እያረግን እንዲረዱን በማድረግ፥ ጊዜ ማቃጠል የለብንም። ልባችን፥ ማንነታችንን ሁሉ በሚያውቀው አምላክ ማረፍ አለበት። ኢየሱስ ድንጋዩን ዳቦ አርጎ በመብላት ረሀቡን ለማስታገስም ሆነ፥ ይሄንን ተአምራት አርጎ የእግዚአብሄርን ልጅ መሆኑን ለማሳየት፥ ስሜት አልገፋፋውም።  ስሜት ከእግዚአብሄር ሀሳብና ፕሮግራም አላስወጣውም። በስሜት ላይ ነገሰ እንጂ ስሜት አልነገሰበትም።  እንግዲህ የያእቆብን ታሪክ እንደምታውቁት፥ ከኤሳው ብኩርናውን ከተቀበለ በኋላ፥ በተንኮል ገብቶ ኤሳው ነኝ በማለት፥ ከአባቱ ከይስሀቅ ለኤሳው የሚገባውን በረከት ሁሉ በማታለል ተቀብሏል። ለማታለል የሄደበትም መንገድ ሰርቶለት፥ ማግኘት የሚፈልገውን ነገር በሙሉ አግኝቷል። ያእቆብ “ብኩርና” ውስጥ ያለውን በረከት በሙሉ ከአባቱ ተቀብሏል። አሁን ይሄ ኪዳን ኤሳውን አልፎ በያእቆብ ህይወት ቀጥሏል። ያእቆብ በተንኮል በመግባት፥ አንድ በኩር ልጅ ከአባቱ የሚቀበለውን በረከት በሙሉ ተቀብሏል። አላማውን በሙሉ አሳክቷል። ኪዳኑ በህይወቱ ሰርቷል። የእግዚአብሄር ፕሮግራም በህይወቱ ቀጥሏል። እግዚአብሄርም በዘመኑ ሁሉ ከእርሱ ጋር ሆኗል። እግዚአብሄር ጠብቆታል። በተለያየ ጊዜያትም በድምጽና በራእይ አናግሮታል። ምንም የእግዚአብሄር ኪዳን በህይወቱ ቢሰራም ግን፥ መዝራትና ማጨድ የእግዚአብሄር ህግ በመሆኑ፥ ያእቆብ ወንድሙንም ሆነ አባቱን በማታለል የሄደባቸው የማታለል መንገዶች፥ ህይወቱ ላይ እጅግ በጣም ብዙ ዋጋ አስከፍለውታል። የያእቆብን ህይወት ጠቅለል አርገን ስናየው፥ ህይወት ትግል የሆነበት ሰው ነበር። ያእቆብ ታጋይ ነው። ትግል የጀመረው ከእናቱ ማህጸን ሲሆን፥ ይሄ ትግሉ ዘመኑን ሙሉ ቀጥሏል። ከወንድሙ ጋር ይታገላል። ከአጎቱ ከላባ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ይታገላል። ኸረ ያእቆብ ከእግዚአብሄርም ጋር ታግሏል። ወንድሙን ኤሳውን በመሸሽ ወደ አጎቱ ወደ ላባ ቤት ሲሄድ ታዲያ፥ ከላባ ጋር ያሳለፋቸው አመታቶች፥ ዘርቶ የመጣውን የማታለል ዘር ያጨደበት ቦታ ሆኖበታል። ላባ ያእቆብን አስር ጊዜ ደሞዙን እየቀያየረ አታሎታል። 20 አመታቶችን በሚስቶቹ ምክኒያት ገዝቶታል። ያእቆብ አንዴ በበጎቹ፥ አንዴ ደግሞ በፍየሎቹ፥ ከላባ ጋር ባለመስማማት፥ ብዙ ከተማረረ በኋላ፥ ከወንድሙ ከኤሳው እንደኮበለለ፥ እንዲሁ ደግሞ ከአጎቱም ከላባ ኮብልሎ ወደ ሀገሩ ተመልሷል። ከዘመናት በፊት አታሎ የተለየውን ወንድሙን ኤሳውን እንደገና ለመገናኘት፥ በጣም በብዙ ጭንቀት ውስጥ

Article

ዘላለም

Home Blog Book About Contact X Order Book ዘላለም Audio ዛሬ ስራ ቦታዬ በስራ ብዛት የተጨናነቀ ነበር። የስራዬ ባህሪ ከተለያዩ ሰዎች ጋር የሚያገናኘኝ በመሆኑ፣ ከሰዎች ጋር ለማውራትና ለመጫወት እድል ይሰጠኛል። በስራዬ መካከል በምወስዳቸው የእረፍት ሰአቶች ግን የምፈልገው አንድ ነገር ብቻ ነው። ጸጥታ።  ታዲያ ዛሬም ልክ እንደ ወትሮዬ፥ አንድ ጸጥ ያለ የማረፊያ ክፍል ፈልጌ፣ ለጥቂት ደቂቃዎች ለማረፍ ቁጭ አልኩ። እፎይ ተመስገን እግዚአብሄር አምላኬ ብዬ አይኖቼን ጭፍን እንዳደረኩ፣ ልቤ ወዳላሰብኩት ሀሳብ ውስጥ ከተተኝ። ድንገት፥ በዚህች ምድር ላይ የምኖርባትን የመጨረሻዋን ቀን ማሰብ ጀመርኩ። የመጨረሻ ቀኔ ግን ምን ይመስል ይሆን? ምን አይነት ሁኔታ ላይ እሆን? የመጨረሻ ቀኔ እንደሆነ ሳውቅና በዚህች ምድር ላይ የኖርኩትን ህይወት ሳስበው ምን አይነት ስሜት ይሰማኝ ይሆን? ይሄን ይሄን ባደረኩ ኖሮ የሚል ቁጭት? ጸጸት? ወይንስ ደግሞ እፎይ መኖር ያለብኝን ህይወት በትክክል ኖሬዋለሁ። ማድረግ ያለብኝን ነገሮች ሁሉ በትክክል አድርጌያቸዋለሁ። አሁን ሄጄ አምላኬን ለማየት ናፍቄያለሁ የሚል የድልና የእርካታ ስሜት? ሀዋሪያው ጳውሎስ እንዳለው፥ በዚህች ህይወት ብቻ ክርስቶስን ተስፋ የምናደርገው ከሆነ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን። ከዚህች አጭር የምድር ህይወት ያለፈ፥ ዘላለም የምንኖርበት ህይወት አለን። ይሄ ዘላለም ደግሞ 100 አመታቶች ብቻ አይደለም። 900 እና አንድ ሺህ አመታቶችም አይደለም። ዘላለም፥ ሚሊየን እና ቢሊየን አመታቶች ብቻም አይደለም። ለአንዳንዶች፥ ኡፍፍፍፍ እግዚአብሄር ይመስገን የሚያስብል፥ ለአንዳንዶች ደግሞ፥ ይሄም ያልፋል የሚለው ቃል ከጥቅም ውጪ የሚሆንበት አለም ነው።  አሁን ላይ ዝም ብለን ስንኖር፣ ይሄ በምድር ላይ ያለው ህይወታችን ማብቂያ ወይንም ማለቂያ ያለው አይመስለንም። ብዙ ጊዜ ማሰብ የምንፈልገው፣ ወጣትነታችንን፣ መስራት የምንችልባቸውን ጊዜያቶች፥ የህይወት ምኞቶቻችንን እና አስደሳች የሆኑትን የህይወት ጊዜያቶቻችንን ብቻ ነው። ብታምኑም ባታምኑም ግን እንደምንሞት ጊዜ ወስደን አለማሰባችን ህይወታችንን እንዴት እንደጎዳው! ሳናስበው እዚህ ምድር ላይ ዘላለም እንደምንኖር አይነት ስሜት እየሰጠ አዘናግቶናል። የተሰጠውን የምድር ቆይታ ስኬታማ በሆነ መንገድ የጨረሰው ዳዊት፥ እግዚአብሄርን ከጠየቀው ጥያቄ ውስጥ አንዱን ላንብብላችሁ። “ፍጻሜዬን አስታውቀኝ። የዘመኔ ቁጥር ምን ያህል እንደሆኑ፣ እኔ ምን ያህል ወደ ሁዋላ እንደምቀር አውቅ ዘንድ” (መዝ 39:4) አሁን ላይ ስንበላ፣ ስንጠጣ፣ ስንሰራ፣ ስንወጣና ስንገባ፥ ዘላለም ሀሳቡን ቀይሮ ላይመጣ የሄደ ይመስል ትዝም አይለንም። ልባችን በቀን ለቀን የህይወት ጉዳዮቻችን ተይዞና ተወጥሮ፣ ሀሳቦቻችን በሙሉ ምድር ላይ ተጀምረው ምድር ላይ ብቻ የሚያልቁ ሆነዋል። የምንማረው፣ የምንሰራው፣ የምናገባው፣ ቤት የምንገዛው፣ ገንዘብ የምናጠራቅመው፣ በዚህች ምድር ላይ ያለችዋን ቀሪዋን ጊዜያችንን ደስተኛ ሆነን ለመኖር ነው። እነዚህን ነገሮች ማድረግም ሆነ መመኘት ምንም ክፋት የለባቸውም። ክፋቱ ምንድነው? የአይምሮአችንን ቦታ በሙሉ ወሰዱና አይምሮአችንን አጠበቡት። ምድራዊ ብቻ አርገው አስቀሩን። ከዚህ ያለፈ ህይወት እንዳለ አስረሱን። አዘናጉን። ከዋናው ሀገራችን ሀሳብና ልባችንን ወሰዱት። ትልቁ የዘላለም ቤት ምኞታችንን በጊዜያዊ ነገሮች ተክተው ለወጡብን። አረሳሱን። ብዙዎቻችን ዛሬ ላይ ቀጣይነት ስላለው የዘላለም ህይወታችን የሚናገሩ ትምህርቶችን ወይንም ስብከቶችን ከመስማት ይልቅ፣ ከዚህ ምድር ጋር የተገናኘ የበረከት ወይንም የብልፅግና ወሬ ብናወራ ነው ደስ የሚለን። ዛሬ ግን እግዚአብሄር የሚፈልገው፣ ልባችንን በመንገዳችን ላይ እንድናደርግ፣ ዘላለማዊውን ህይወት በማሰብ፣ የተሰጠንን ድጋሚ እድልና ማስተካከያ የሌለው ህይወት በማስተዋልና በጥንቃቄ እንድንኖር ነው።  በየቀኑ ሀሳባችን ውስጥ ሊኖርና ሁሌ ልናስበው ከሚገቡ ነገሮች አንዱና ዋነኛው የዘላለማችን ጉዳይ ነው። ሰው ህይወቱ ዘላለማዊ ነው። ታዲያ መጨረሻ ከሌለው ዘላለም ላይ ለክቶና ወስኖ ለእኛ ለሰው ልጆች እግዚአብሄር የሰጠን ይህቺ የምድር ቆይታችን፥ መጀመሪያዋን እንጂ የቱ ጋር እንደምታልቅ ማናችንም አናውቃትም። በጣም ማወቅ ያለብን ደግሞ፣ በዚህች በአጭሯ የምድር ቆይታችን ላይ የምንኖረው የህይወት አይነት፥ ማለቂያና ማብቂያ የሌለውን ዘላለም እንዴት እንደምናሳልፈው ይወስናል። በደምብ ካሰባችሁት፣ ከዚህ በላይ ምን የሚያስፈራ ነገር አለ? ሰው ገንዘብ ቢያጣ ሰርቶ ይተካዋል፣ ሰው ጤና እንኳን ቢያጣ ወይ ታክሞ ይድናል፣ ወይ ህመሙን ታግሶ ይኖራል፣ ወይ ደግሞ ወደ አምላኩ ይሄዳል። ህይወቱ ከአምላኩ ጋር ትክክል ይሁን እንጂ ሞት ወደ ዘላለም ደስታው የመሻገሪያ መንገዱ ነው። ሰው ግን ህይወቱ ላይ እግዚአብሄር ከሌለ ወይንም ደግሞ እግዚአብሄር ከእርሱ የሚጠብቅበትን ህይወት ካልኖረ እዛ ሄዶ አያስተካክለው። ወይንም ጥሩ ጥሩ ምክኒያቶች ብሎ የሚሰበስባቸው ምክኒያቶቹ በእግዚአብሄር ፊት አቅም አግኝተው ምክኒያት አይሆኑለት። መጽሀፍ ቅዱስ እንደሚል፣ የጠራንን በማወቅ፣ ለህይወትና እግዚአብሄርን ለመምሰል የሚያስፈልገውን ሁሉ ስለሰጠን፣ ለኖርነው የህይወት አይነት የምናቀርበው ምንም አይነት ምክኒያት ሊኖረን አይችልም።  ዘላለም ውስጥ እኮ ስንገባ፣ በምድር ላይ ያካበትነው የትኛውም ሀብት ትርጉም አይኖረውም። አሁን የምንለብሳቸው ጥሩ ጥሩ ብራንድ ያላቸው ልብሶች ምንም ትርጉም የላቸውም። ዘላለም ውስጥ ስንገባ፥ ዛሬ የምናወጣቸው ዜሮ ማይል የሆኑ ዘመናዊ መኪናዎቻችን ምንም ትርጉም የላቸውም። ዛሬ የምንኖርባቸው የተንጣለሉ ግራውንድ ፕላሶች ትርጉም የላቸውም። ዘላለም ውስጥ ስንገባ በሰዎች ዘንድ ያገኘናቸው ክብርና ዝናዎች ወይንም ሰለብሪቱዎች ምንም ትርጉም የላቸውም። የምድር ሀያላንና ክቡራን፣ ሚሊየነሮችና ቢሊየነሮች እኮ ምንም ትርጉም የላቸውም። ትርጉም ያለው አንድ ነገር ብቻ ነው። እንደ እግዚአብሄር ሀሳብና ፈቃድ የኖርነው ህይወት ብቻ። በዚህ ምድር ላይ ቁጭ ብለን የምናካብተው ዘላለማዊነት ያለው ሀብት፥ እንደ እግዚአብሄር ሀሳብና ፈቃድ የምንኖረው ህይወት ብቻ ነው። ሌላው ቀርቶ፥ መጽሀፍ ቅዱስ ላይ ከተጻፈውና ከራሱ ከክርስቶስ አንደበት እንደሰማነው ከሆነ፣ ትንቢት መናገራችን፣ አጋንንት ማውጣታችን፣ ድንቅና ተአምራቶችን ስናደርግ እድሜያችንን ሙሉ መኖራችን እራሱ ትርጉም ላይኖረው ይችላል። በዚያን ቀን አለ ክርስቶስ በማቴዎች ምእራፍ 7 ከቁጥር 21 ጀምሮ ሲናገር፥ በዚያን ቀን፥ ብዙዎች እንዲህ ይሉኛል አለ። ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፣ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፣ በስምህስ ብዙ ተእምራት አላደረግንምን ይሉኛል። የዚያን ጊዜም ከቶ አላወቅሁዋችሁም እናንተ አመጸኞች ከኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባችሁዋለሁ አለ። ከላይ ግን አንድ ነገር አለ። በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፣ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግስተ ሰማያት የሚገባ አይደለም አለ። በነገራችን ላይ ክርስቶስ ያላቸው እነዚህ ትንቢትን የሚናገሩ፣ አጋንንትን የሚያወጡ፣ ብዙ ድንቅና ተአምራትን የሚያረጉት ሰዎች አህዛቦች አይደሉም። በክርስቶስ መጀመሪያ አምነው የዳኑ ሰዎች ናቸው። ክርስቶስ ግን ከቶ አላውቃችሁም አይደለም እላቸዋለሁ ያለው። ከቶ  አላወኩዋችሁም እላቸዋለሁ አለ። ለካ ክርስቶስ የሚያውቀን በአገልግሎታችን ብዛትና አስደናቂነት አይደለም። የሚያውቀን ፈቃዱን በማድረግ በምንኖረው ህይወት ውስጥ ነው። በእርሱ ዘንድ ያለን እውቅና ይሄ ብቻ ነው። ምናልባት የአገልግሎቶቻችን ብዛት እውቅናን የሚሰጠን በሰዎች ዘንድ ብቻ ሊሆን ይችላል። ምድር ተሰብስቦ ቢያውቀን ግን በስሙ ያገለገልነው ክርስቶስ ካላወቀን ምን ትርጉም አለው? እግዚአብሄር ተአምራቶችን የሚያደርግ ሰው አይደለም የሚፈልገው፣ እግዚአብሄር የሚፈልገው ፈቃዱንና የልቡን ሀሳብ የሚኖርለትን ሰው ነው። ተእምራቶችን ማድረጋችን መጥፎ ነው እያልን ግን አይደለም። ተእምራቶቹ የእግዚአብሄርን ፈቃድ በመኖርና በማድረግ ውስጥ መሆን አለባቸው እያልን ነው።  ብዙ ጊዜ የክርስቶስን ንግግሮች በደምብ አስተውላችሁ አይታችሁት ከሆነ እየደጋገመ የሚለው አንድ ነገር አለ። የአባቴን ፈቃድ አደርጋለሁ ይላል። እንዲያውም አንድ ጊዜ በዮሀንስ ምእራፍ 6 ቁጥር 38 ላይ ከሰማይ የመጣሁት የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ እንጂ የራሴን ፈቃድ ለማድረግ አይደለም በማለት ይናገራል። ክርስቶስ በምድር ላይ ሲኖር፣ የሰውን ስጋ እንደመልበሱ፣ ልክ እንደ ሁላችንም፣ የራሱ ፈቃድ የነበረው ቢሆንም፣ ፈቃዱን ግን አልተጠቀመበትም። ሙሉ ፈቃዱን ለአብ በማስገዛት የተላከበትን የአባቱን ፈቃድ በሙሉ መስዋእትነት ኖሮና ፈጽሞ ነው ያለፈው። እኛም እንዲሁ እዚህች ምድር ላይ ለመኖር እንደመጣን ማሰብ የለብንም። ተልከን እንደመጣን ነው ማሰብ ያለብን። የላከንን ፈቃድ አድርገን ለማለፍ ነው የመጣነው። የምንኖረው የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለማድረግ ብቻ ነው። አላማ አለን። ግብ አለን። በዚህ ምድር ላይ የተሰጠን ቆይታ፣ መጀመሪያ እንዳለው ሁሉ መጨረሻም አለው። የህይወት ስኬት ብለን የምንለው ልክ እንደ ዳዊት በተሰጠን ዘመን፥ የእግዚአብሄርን ሀሳብ ኖሮና አገልግሎ ማለፍ መሆን ይኖርበታል። በዚህች ምድር ላይ ስንኖር፥ አጥብቀን መፈለግ ያለብን የእግዚአብሄርን ፈቃድ ነው። ማወቅ ያለብን ግን መንፈሳዊነት አይደለም በእግዚአብሄር ፊት የከበረ ዋጋ ያለው። የእግዚአብሄርን ሀሳብና ፈቃድ

Article

ከትዳር በፊት ማወቅ ያሉብኝ ነገሮች

Home Blog Book About Contact X Order Book እድገት Audio መቼም የሕይወት ዘመን ተማሪ እንደመሆኔ መጠን፥ በየደረስኩበት መንገድ የምማራቸውን ነገሮች ለሰዎች ማካፈሌ ፍጹም የሆነ የእግዚአብሔር ሀሳብ እንደሆነ አውቃለሁ። እስከዛሬ በጽሁፍ ወደ እናንተ ካደረስካቸው መልእክቶች ውስጥ የእኔን ሕይወት ያለወጠ፣ እኔን ያላስተማረ እና አይምሮዬን ያላደሰ፣ የሕይወቴ አካል አድርጌው ለመኖር የማልሞክረው ጽሁፍ የለም ብዬ በድፍረት መናገር እችላለሁ። የማካፍለው የደረስኩበትን ብቻ ነው። የምሰጠው የተቀበልኩትን ብቻ ነው። ታዲያ ሰሞኑን አስብና አሰላስል የነበረውን እንዲሁም ነፍሴ የተመከረችበትን እውነት ለትንሽ ሰው እንካን ጥቂት የሚጠቅም ነገር ከተገኘበት ብዬ ልክ እንደ ወትሮው ዛሬም በጽሁፌ ይዤላችሁ እመጣ ዘንድ መልካም ሆኖ ታየኝ። አስብ የነበረው ስለ ማደግ ወይንም ስለ እድገት ነው። በየቀኑ በዙሪያችን እንደምንመለከተው ሕይወት ያለው ነገር በሙሉ ያድጋል። አንድ ልጅ ይወለድ እንጂ ከበላና ከጠጣ ማደጉ አይቀርም። ታዲያ አንድ ልጅ ከተወለደ እና የሚያስፈልገውን ምግብ ካገኘ እንደሚያድገው ሁሉ፥ ዳግም የመወለዳችን ዋናው ምልክት በሕይወታችን የሚታየው እድገት ነው። የምናድገው ስለተወለድን ነው፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ዳግም ስለተወለድን ነው። የተወለደ ነገር ሁሉ ሕይወት ያለው ነገር እንደሚያድግ ሁሉ፥ ልክ እንዲሁ ዳግም የተወለድነው ለማደግ ነው። እያደግን ካልሆነ ምክኒያቱ ከሁለት አንዱ ነው። ወይ ከነጭራሹ አልተወለድንም ወይንም ደግሞ ለማደግ የሚያስፈልገንን አስፈላጊ ምግብ እየተመገብን አይደለም ማለት ነው። የማይመገብ ሰው ደግሞ ቀስ እያለ ወደ ሞት እንደሚሄድ ሁሉ፥ አለመመገብ በጊዜ ውስጥ መንፈሳዊ ሞትን ሊያመጣ ይችላል። በኢየሱስ ክርስቶስ አምነን ድነናል ወይንም ዳግም ተወልደናል ካልን፥ በሕይወት ለመቆየት ምግብ የመብላታችን ነገር አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። ይህም ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ እድገታችንን በቀጥታ ያያያዘው የእግዚአብሔርን ቃል ከመመገብ ጋር ስለሆነ ነው። መወለድ እና ማደግ ሁለት የማይለያዩ ነገሮች ናቸው። የተወለደ እና ህይወት ያለው ነገር በሙሉ እንደሚያድግ ሁሉ፥ ዳግም በክርስቶስ አምኖ የተወለደ ሰውም ልክ እንደዚያው በመንፈሳዊ ሕይወቱ ማደግ አለበት። የእግዚአብሔርም ቃል መዳናችንን እና ማደጋችንን ለያይቶ አያየውም። እንዲያውም 1ኛ ጴጥሮስ ምእራፍ 2፡1-3 ላይ ሲናገር እንዲህ ይላል። “ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።” ይላል። ጌታን ተቀብዬ ድኛለሁ ከዚያ እንደፈለኩ እኖራለሁ የሚባል ነገር የለም። የዳንነው ለማደግ ነው። በእግዚአብሔር ቤት በቆየንበት ጊዜ ልክ እግዚአብሔር እድገትን ከእኛ እንደሚጠብቅ የሚያስተምረንን አንድ ክፍል ከእግዚአብሔር ቃል ላንብብላችሁ።  “ከጊዜው የተነሳ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ቃላት መጀመሪያ ያለውን የሕፃንነትን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ እንደ ገና ያስፈልጋችኋልና፤ የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም። ወተት የሚጋት ሁሉ ሕፃን ስለ ሆነ የጽድቅን ቃል አያውቅምና፤ ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙንና ክፉውን ለመለየት በስራቸው የለመደ ልቡና ላላቸው ለፍጹማን ሰዎች ነው።” (እብራውያን 5፡12-14)  ታዲያ ማደጋችን ከመዳናችን ጋር በቀጥታ የሚገናኝ እና አማራጭ የሌለው ነገር ከሆነ፥ ለማደግ የሚረዱንን 3 ዋና ዋና ነገሮች ከታችን እንደሚከተለው እንመለከታቸዋለን። 1ኛ የእግዚአብሔር ቃል፦ ከላይ እንዳነበብነው የእግዚአብሔር ቃል ሀሳብ፥ መጽሐፍ ቅዱስ እድገታችንን በቀጥታ የሚያያይዘው የእግዚአብሔርን ቃል ከመመገብ ጋር ነው። ለማደግ የምንፈልግ ከሆነ ለእግዚአብሔር ቃል ትልቅ ቦታ መስጠት ይኖርብናል። በየቀኑ የሚመቸንን ቋሚ ጊዜ ፈልገን የእግዚአብሔርን ቃል በማንበብ እና በማጥናት እንዴት አርገን ከህይወታችን ጋር አገናኝተን ተግባራዊ ማድረግ እንዳለብን ማሰላሰል አለብን። ቤተክርስቲያን ስንሄድ የእግዚአብሔር ቃል ሲነገር ቁጭ ብለን ማዳመጥ፣ ሶሻል ሚዲያዎቻችን ላይ ደግሞ እንዲያው ዝም ብሎ የማይጠቅመንን ነገር ከምናይበት፥ ጥሩ ጥሩ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎች የሚያስተምሩትን ትምህርቶች መስማት፣ እነዚህ ሁሉ እኛን በማሳደግ ፍጹምና ለበጎ ስራ የተዘጋጀን እንሆን ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበትን መጽሐፍ በማወቅ እያደግን የምንማርባቸው፣ የምንገሰጽባቸው፣ ልባችንን የምናቀናባቸው እንዲሁም የጽድቅን ምክር የምንመከርባቸው መንገዶች ናቸው። አንድ ህጻን እስኪ ልደግ ብሎ አይበላም። እየበላ ሲሄድ ግን እራሱ በማያውቀው ሁኔታ በየቀኑ ቁመቱ ሲጨምር፣ እና ሰውነቱ ሲያድግ እንመለከታለን። ኦ ይሄ ልጅ ዛሬ ነው በጣም ያደገው አንልም። ያ ህጻን አብሮን እራሱ አንድ ቤት እየኖረ መቼ ቁመቱ እና ሰውነቱ ጨምሮ እንዳደገ ሳናውቀው እድገቱን እናየዋለን። ዛሬ ነው ያደገው ብለን ያደገበትን ቀን በትክክል አናየውም፥ ሲመገብ ግን እናየዋለን። በህይወት መቆየቱ እና እድገቱ፥ የመብላቱ ውጤት እንደሆነም እናውቃለን። ለእግዚአብሔርን ቃል ቦታ እየሰጠን በየቀኑ ስንመገብ፥ መመገባችን አንተው እንጂ እድገታችን ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ነገር አይደለም።  የእግዚአብሔርን ቃል ለማንበብ እና ለማሰላሰል ጊዜ መስጠት፥ ፊልም እንደ ማየት ወይንም ሌሎች የምንወዳቸውን ነገሮች እንደማድረግ ለስጋችን አስደሳች ላይሆን ይችላል። ግን ሌሎች ነገሮችን ለመዝጋት እና ለመጨከን መወሰን አለብን። የውሳኔ ሰው መሆን በጣም አስፈላጊ ነው። ለማንበብ ፍላጎት የሚባል ነገር አጥተን የምንቸገር ከሆንን ደግሞ ግልጽ ሆነን እግዚአብሔር ይሄንን ረሀብ እንዲሰጠን መጸለያችን ትልቅ ለውጥ ያመጣል። እኔ የራሴን ህይወት ስመሰክርላችሁ፥ ከድሮም እግዚአብሔር ሰጥቶኝ እና ረድቶኝ መጸለይና መዘመር እወዳለሁ። ረጅም ሰአት ብጸልይና ብዘምርም የእግዚአብሔርን ቃል የማንበብ ግን ምንም ፍላጎት አልነበረኝም። ታዲያ ቃሉን ማንበቤ እጅግ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ሲገባኝ፥ ግልጽ ሆኜ እግዚአብሔር ቃሉን የማንበብ ፍላጎት እንዲሰጠኝ ለመንኩት። ታማኝ ስለሆነ ከምንለምነውና ከምናስበው እጅግ አብልጦ የሚሰጠው አምላክ፥ በልቤ የቃሉን ረሀብ ላከ። አሁን ላይ የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ማንበብ እና ማሰላሰል የሚያስደስተኝ ነገር የለም። ድሮ ቸርች ቁጭ ብሎ ትምህርት መስማት ብዙም የሚያስደስተኝ ነገር አልነበረም። እግዚአብሔር ስሙ ይባረክ አሁን ላይ በቀን ሁለት ወይንም ሶስት ትምህርቶችን ስሰማ ልውል እችላለሁ። የእግዚአብሔር ቃል ልክ እንደ ምግብ ረሀቤ ሆነ። የምረካው በዚያ ብቻ ሆነ። በዚህ ምስክርነት ውስጥ የእኔን ማንበብ አለመፈለግ እና ድካም የምናገረው፥ እግዚአብሔር እንደ ፈቃዱ የምንለምነውን ሁሉ የሚሰማ፣ እንደ እኔ አይነቷን ሰው ደግሞ የቃሉ ወዳጅ ማድረግ የሚችል አምላክ መሆኑን ሕይወቴ መመስከር ስላለበት ነው።  2ኛ ጸሎት፡- መቼም የጸሎትን አስፈላጊነት እናጣዋለን ብዬ አላስብም። ከአንድ ሰው ጋር ያላችሁን ግንኙነት ለማሳደግ፥ ከዚያ ሰው ጋር ለማሳለፍ ለማወራት እና ለመጫወት የምትወስዱት ጊዜ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። አብራችሁ የምታሳልፉት ጊዜ ነው ያንን ሰው ከትላንትና በተሻለ እንድታውቁት፣ እንድትወዱት እና እንድትረዱት ሊያድርጋችሁ የሚችለው።  ከአንድ ሰው ጋር ተገናኝታችሁ ቁጭ ብላችሁ ስታወሩ፥ ያንን ሰው “ጊዜዬ ይገባሀል” እያላችሁት ነው እንጂ ሌሎች ልታደርጉ የምትችሉት ብዙ ነገር ይኖራል። ልክ ለስራችን፣ ለጓደኞቻችን እና በሕይወታችን አስፈላጊ ናቸው ብለን ለምናስባቸው ጉዳዮቻችን ጊዜ እንደምንሰጣቸው ሁሉ፥ እግዚአብሔር በጣም እንደምንፈልገው የሚረዳው፥ “እፈልግሀለሁ” የሚለውን ዝማሬ ስንዘምር አይደለም። እንደምንፈልገው ጊዜ እና ትኩረት እየሰጠን በድርጊት ስናሳየው ነው። ታዲያ በዚህ ከእግዚአብሔር ጋር ጊዜ ለማሳለፍ በምንሰጠው ጊዜ ውስጥ፥ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ህብረት በማድረግ የውስጥ ሰውነታችን እንዲጠነክር እና በመንፈስ እንድናድግ ትልቅ እድል ይሰጠናል። የእግዚአብሔርን መንፈስ በመለማመድ እናድጋለን፥ ድምጹን በመስማት እናድጋለን፥ ከእርሱ ጋር ህብረት በማድረግ እናድጋለን፥ ነፍሳችንን በፊቱ በማፍሰስ፣ እውነተኛ ልባችንን ለእርሱ በማሳየት ከእርሱ ምክርን ለመቀበል፣ ለመገሰጽ እንዲሁም ፈቃዱን ለመከተል ትክክለኛ ምሪትን በማግኘት እና ሀሳቡን በዘመናችን በመፈጸም እናድጋለን።  3ኛ ህብረት፡- ህብረት መቼም ትልቅ የሆነ የእግዚአብሔር ሀሳብ ነው። ገና ከፍጥረት መጀመሪያ እራሱ እኮ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም ብሎ ለአዳም ሄዋንን ሲፈጥርለት በዚህ ህብረት ውስጥ አዳም እርዳታን ያገኝ ዘንድ ነው። እግዚአብሔር ህብረትን የሚወድ የህብረት አምላክ ስለሆነ ነው። ህብረት እያልን ስናወራ ታዲያ ስለ ሰዎች ስብስብ ብቻ እያወራን እንዳልሆነ ማስተዋል መልካም ነው። በምድራችን ላይ ብዙ የህብረት ስብሰባዎች አሉ። አሁን እየተነጋገርን ያለነው ህብረቶች ግን መንፈሳዊ የሆኑ፣ አላማ ያላቸው፣ እድገትን የምናገኝባቸው ህብረቶች ነው። አንዳንዴ በድካም ውስጥ ስንሆን እና ወደ ጸሎት ህብረቶች፣ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ህብረቶች እንዲሁም ወደምናገለግልባቸው ህብረቶች ስንሄድ፥ ህብረቱ ውስጥ ከሚሰራው የመንፈስ ቅዱስ ሀይል እንካፈላለን። ወደ ህብረቱ በሄድንበት ድካም እና ዝለት አንመለስም። ሀይልን እንሞላለን፣ የእግዚአብሔርን ቃል እንሞላለን፣ ጸሎትን እንሞላለን፣ ከነበርንበት ድካም የምንወጣበትን ሀይል እናገኛለን። ውስጣችን ያለውን የጸጋ ስጦታ ደግሞ ለማካፈል ስፍራን እናገኛለን። ብንደክም እንበረታለን፣ ብንስት እንመከራለን፣ ከሌሎች ጋር

Article

እድገት

Home Blog Book About Contact X Order Book እድገት Audio መቼም የሕይወት ዘመን ተማሪ እንደመሆኔ መጠን፥ በየደረስኩበት መንገድ የምማራቸውን ነገሮች ለሰዎች ማካፈሌ ፍጹም የሆነ የእግዚአብሔር ሀሳብ እንደሆነ አውቃለሁ። እስከዛሬ በጽሁፍ ወደ እናንተ ካደረስካቸው መልእክቶች ውስጥ የእኔን ሕይወት ያለወጠ፣ እኔን ያላስተማረ እና አይምሮዬን ያላደሰ፣ የሕይወቴ አካል አድርጌው ለመኖር የማልሞክረው ጽሁፍ የለም ብዬ በድፍረት መናገር እችላለሁ። የማካፍለው የደረስኩበትን ብቻ ነው። የምሰጠው የተቀበልኩትን ብቻ ነው። ታዲያ ሰሞኑን አስብና አሰላስል የነበረውን እንዲሁም ነፍሴ የተመከረችበትን እውነት ለትንሽ ሰው እንካን ጥቂት የሚጠቅም ነገር ከተገኘበት ብዬ ልክ እንደ ወትሮው ዛሬም በጽሁፌ ይዤላችሁ እመጣ ዘንድ መልካም ሆኖ ታየኝ። አስብ የነበረው ስለ ማደግ ወይንም ስለ እድገት ነው። በየቀኑ በዙሪያችን እንደምንመለከተው ሕይወት ያለው ነገር በሙሉ ያድጋል። አንድ ልጅ ይወለድ እንጂ ከበላና ከጠጣ ማደጉ አይቀርም። ታዲያ አንድ ልጅ ከተወለደ እና የሚያስፈልገውን ምግብ ካገኘ እንደሚያድገው ሁሉ፥ ዳግም የመወለዳችን ዋናው ምልክት በሕይወታችን የሚታየው እድገት ነው። የምናድገው ስለተወለድን ነው፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ዳግም ስለተወለድን ነው። የተወለደ ነገር ሁሉ ሕይወት ያለው ነገር እንደሚያድግ ሁሉ፥ ልክ እንዲሁ ዳግም የተወለድነው ለማደግ ነው። እያደግን ካልሆነ ምክኒያቱ ከሁለት አንዱ ነው። ወይ ከነጭራሹ አልተወለድንም ወይንም ደግሞ ለማደግ የሚያስፈልገንን አስፈላጊ ምግብ እየተመገብን አይደለም ማለት ነው። የማይመገብ ሰው ደግሞ ቀስ እያለ ወደ ሞት እንደሚሄድ ሁሉ፥ አለመመገብ በጊዜ ውስጥ መንፈሳዊ ሞትን ሊያመጣ ይችላል። በኢየሱስ ክርስቶስ አምነን ድነናል ወይንም ዳግም ተወልደናል ካልን፥ በሕይወት ለመቆየት ምግብ የመብላታችን ነገር አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። ይህም ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ እድገታችንን በቀጥታ ያያያዘው የእግዚአብሔርን ቃል ከመመገብ ጋር ስለሆነ ነው። መወለድ እና ማደግ ሁለት የማይለያዩ ነገሮች ናቸው። የተወለደ እና ህይወት ያለው ነገር በሙሉ እንደሚያድግ ሁሉ፥ ዳግም በክርስቶስ አምኖ የተወለደ ሰውም ልክ እንደዚያው በመንፈሳዊ ሕይወቱ ማደግ አለበት። የእግዚአብሔርም ቃል መዳናችንን እና ማደጋችንን ለያይቶ አያየውም። እንዲያውም 1ኛ ጴጥሮስ ምእራፍ 2፡1-3 ላይ ሲናገር እንዲህ ይላል። “ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።” ይላል። ጌታን ተቀብዬ ድኛለሁ ከዚያ እንደፈለኩ እኖራለሁ የሚባል ነገር የለም። የዳንነው ለማደግ ነው። በእግዚአብሔር ቤት በቆየንበት ጊዜ ልክ እግዚአብሔር እድገትን ከእኛ እንደሚጠብቅ የሚያስተምረንን አንድ ክፍል ከእግዚአብሔር ቃል ላንብብላችሁ።  “ከጊዜው የተነሳ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ቃላት መጀመሪያ ያለውን የሕፃንነትን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ እንደ ገና ያስፈልጋችኋልና፤ የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም። ወተት የሚጋት ሁሉ ሕፃን ስለ ሆነ የጽድቅን ቃል አያውቅምና፤ ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙንና ክፉውን ለመለየት በስራቸው የለመደ ልቡና ላላቸው ለፍጹማን ሰዎች ነው።” (እብራውያን 5፡12-14)  ታዲያ ማደጋችን ከመዳናችን ጋር በቀጥታ የሚገናኝ እና አማራጭ የሌለው ነገር ከሆነ፥ ለማደግ የሚረዱንን 3 ዋና ዋና ነገሮች ከታችን እንደሚከተለው እንመለከታቸዋለን። 1ኛ የእግዚአብሔር ቃል፦ ከላይ እንዳነበብነው የእግዚአብሔር ቃል ሀሳብ፥ መጽሐፍ ቅዱስ እድገታችንን በቀጥታ የሚያያይዘው የእግዚአብሔርን ቃል ከመመገብ ጋር ነው። ለማደግ የምንፈልግ ከሆነ ለእግዚአብሔር ቃል ትልቅ ቦታ መስጠት ይኖርብናል። በየቀኑ የሚመቸንን ቋሚ ጊዜ ፈልገን የእግዚአብሔርን ቃል በማንበብ እና በማጥናት እንዴት አርገን ከህይወታችን ጋር አገናኝተን ተግባራዊ ማድረግ እንዳለብን ማሰላሰል አለብን። ቤተክርስቲያን ስንሄድ የእግዚአብሔር ቃል ሲነገር ቁጭ ብለን ማዳመጥ፣ ሶሻል ሚዲያዎቻችን ላይ ደግሞ እንዲያው ዝም ብሎ የማይጠቅመንን ነገር ከምናይበት፥ ጥሩ ጥሩ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎች የሚያስተምሩትን ትምህርቶች መስማት፣ እነዚህ ሁሉ እኛን በማሳደግ ፍጹምና ለበጎ ስራ የተዘጋጀን እንሆን ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበትን መጽሐፍ በማወቅ እያደግን የምንማርባቸው፣ የምንገሰጽባቸው፣ ልባችንን የምናቀናባቸው እንዲሁም የጽድቅን ምክር የምንመከርባቸው መንገዶች ናቸው። አንድ ህጻን እስኪ ልደግ ብሎ አይበላም። እየበላ ሲሄድ ግን እራሱ በማያውቀው ሁኔታ በየቀኑ ቁመቱ ሲጨምር፣ እና ሰውነቱ ሲያድግ እንመለከታለን። ኦ ይሄ ልጅ ዛሬ ነው በጣም ያደገው አንልም። ያ ህጻን አብሮን እራሱ አንድ ቤት እየኖረ መቼ ቁመቱ እና ሰውነቱ ጨምሮ እንዳደገ ሳናውቀው እድገቱን እናየዋለን። ዛሬ ነው ያደገው ብለን ያደገበትን ቀን በትክክል አናየውም፥ ሲመገብ ግን እናየዋለን። በህይወት መቆየቱ እና እድገቱ፥ የመብላቱ ውጤት እንደሆነም እናውቃለን። ለእግዚአብሔርን ቃል ቦታ እየሰጠን በየቀኑ ስንመገብ፥ መመገባችን አንተው እንጂ እድገታችን ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ነገር አይደለም።  የእግዚአብሔርን ቃል ለማንበብ እና ለማሰላሰል ጊዜ መስጠት፥ ፊልም እንደ ማየት ወይንም ሌሎች የምንወዳቸውን ነገሮች እንደማድረግ ለስጋችን አስደሳች ላይሆን ይችላል። ግን ሌሎች ነገሮችን ለመዝጋት እና ለመጨከን መወሰን አለብን። የውሳኔ ሰው መሆን በጣም አስፈላጊ ነው። ለማንበብ ፍላጎት የሚባል ነገር አጥተን የምንቸገር ከሆንን ደግሞ ግልጽ ሆነን እግዚአብሔር ይሄንን ረሀብ እንዲሰጠን መጸለያችን ትልቅ ለውጥ ያመጣል። እኔ የራሴን ህይወት ስመሰክርላችሁ፥ ከድሮም እግዚአብሔር ሰጥቶኝ እና ረድቶኝ መጸለይና መዘመር እወዳለሁ። ረጅም ሰአት ብጸልይና ብዘምርም የእግዚአብሔርን ቃል የማንበብ ግን ምንም ፍላጎት አልነበረኝም። ታዲያ ቃሉን ማንበቤ እጅግ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ሲገባኝ፥ ግልጽ ሆኜ እግዚአብሔር ቃሉን የማንበብ ፍላጎት እንዲሰጠኝ ለመንኩት። ታማኝ ስለሆነ ከምንለምነውና ከምናስበው እጅግ አብልጦ የሚሰጠው አምላክ፥ በልቤ የቃሉን ረሀብ ላከ። አሁን ላይ የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ማንበብ እና ማሰላሰል የሚያስደስተኝ ነገር የለም። ድሮ ቸርች ቁጭ ብሎ ትምህርት መስማት ብዙም የሚያስደስተኝ ነገር አልነበረም። እግዚአብሔር ስሙ ይባረክ አሁን ላይ በቀን ሁለት ወይንም ሶስት ትምህርቶችን ስሰማ ልውል እችላለሁ። የእግዚአብሔር ቃል ልክ እንደ ምግብ ረሀቤ ሆነ። የምረካው በዚያ ብቻ ሆነ። በዚህ ምስክርነት ውስጥ የእኔን ማንበብ አለመፈለግ እና ድካም የምናገረው፥ እግዚአብሔር እንደ ፈቃዱ የምንለምነውን ሁሉ የሚሰማ፣ እንደ እኔ አይነቷን ሰው ደግሞ የቃሉ ወዳጅ ማድረግ የሚችል አምላክ መሆኑን ሕይወቴ መመስከር ስላለበት ነው።  2ኛ ጸሎት፡- መቼም የጸሎትን አስፈላጊነት እናጣዋለን ብዬ አላስብም። ከአንድ ሰው ጋር ያላችሁን ግንኙነት ለማሳደግ፥ ከዚያ ሰው ጋር ለማሳለፍ ለማወራት እና ለመጫወት የምትወስዱት ጊዜ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። አብራችሁ የምታሳልፉት ጊዜ ነው ያንን ሰው ከትላንትና በተሻለ እንድታውቁት፣ እንድትወዱት እና እንድትረዱት ሊያድርጋችሁ የሚችለው።  ከአንድ ሰው ጋር ተገናኝታችሁ ቁጭ ብላችሁ ስታወሩ፥ ያንን ሰው “ጊዜዬ ይገባሀል” እያላችሁት ነው እንጂ ሌሎች ልታደርጉ የምትችሉት ብዙ ነገር ይኖራል። ልክ ለስራችን፣ ለጓደኞቻችን እና በሕይወታችን አስፈላጊ ናቸው ብለን ለምናስባቸው ጉዳዮቻችን ጊዜ እንደምንሰጣቸው ሁሉ፥ እግዚአብሔር በጣም እንደምንፈልገው የሚረዳው፥ “እፈልግሀለሁ” የሚለውን ዝማሬ ስንዘምር አይደለም። እንደምንፈልገው ጊዜ እና ትኩረት እየሰጠን በድርጊት ስናሳየው ነው። ታዲያ በዚህ ከእግዚአብሔር ጋር ጊዜ ለማሳለፍ በምንሰጠው ጊዜ ውስጥ፥ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ህብረት በማድረግ የውስጥ ሰውነታችን እንዲጠነክር እና በመንፈስ እንድናድግ ትልቅ እድል ይሰጠናል። የእግዚአብሔርን መንፈስ በመለማመድ እናድጋለን፥ ድምጹን በመስማት እናድጋለን፥ ከእርሱ ጋር ህብረት በማድረግ እናድጋለን፥ ነፍሳችንን በፊቱ በማፍሰስ፣ እውነተኛ ልባችንን ለእርሱ በማሳየት ከእርሱ ምክርን ለመቀበል፣ ለመገሰጽ እንዲሁም ፈቃዱን ለመከተል ትክክለኛ ምሪትን በማግኘት እና ሀሳቡን በዘመናችን በመፈጸም እናድጋለን።  3ኛ ህብረት፡- ህብረት መቼም ትልቅ የሆነ የእግዚአብሔር ሀሳብ ነው። ገና ከፍጥረት መጀመሪያ እራሱ እኮ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም ብሎ ለአዳም ሄዋንን ሲፈጥርለት በዚህ ህብረት ውስጥ አዳም እርዳታን ያገኝ ዘንድ ነው። እግዚአብሔር ህብረትን የሚወድ የህብረት አምላክ ስለሆነ ነው። ህብረት እያልን ስናወራ ታዲያ ስለ ሰዎች ስብስብ ብቻ እያወራን እንዳልሆነ ማስተዋል መልካም ነው። በምድራችን ላይ ብዙ የህብረት ስብሰባዎች አሉ። አሁን እየተነጋገርን ያለነው ህብረቶች ግን መንፈሳዊ የሆኑ፣ አላማ ያላቸው፣ እድገትን የምናገኝባቸው ህብረቶች ነው። አንዳንዴ በድካም ውስጥ ስንሆን እና ወደ ጸሎት ህብረቶች፣ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ህብረቶች እንዲሁም ወደምናገለግልባቸው ህብረቶች ስንሄድ፥ ህብረቱ ውስጥ ከሚሰራው የመንፈስ ቅዱስ ሀይል እንካፈላለን። ወደ ህብረቱ በሄድንበት ድካም እና ዝለት አንመለስም። ሀይልን እንሞላለን፣ የእግዚአብሔርን ቃል እንሞላለን፣ ጸሎትን እንሞላለን፣ ከነበርንበት ድካም የምንወጣበትን ሀይል እናገኛለን። ውስጣችን ያለውን የጸጋ ስጦታ ደግሞ ለማካፈል ስፍራን እናገኛለን። ብንደክም እንበረታለን፣ ብንስት እንመከራለን፣ ከሌሎች ጋር

Article

እውቀት

Home Blog Book About Contact X Order Book እውቀት Audio “ዘመኑ የኢንፎርሜሽን ዘመን ነው” ይላሉ ሲናገሩ። ነገር ሁሉ በእውቀትና በማስረጃ የተደገፈ ሆኗል። የመጨረሻው ዘመን ነውና እውቀት በዝቷል። “አላውቅም” የሚባል ነገር ቀርቷል። ሁሉም ሰው ያውቃል። እውቀት ትምህርት ቤት ብቻ መሆኑ ቀርቶ፥ ዛሬ ዛሬ ከያዝነው ሞባይል ስልክ ጋር እጃችን ውስጥ ገብቷል። አለም በእጃችን ናት፥ የፈለግነውን መረጃ በፈለግነው ደቂቃ ውስጥ እናገኛለን። እድሜ ለጎግል! ደስ ያለንን ኢንፎርሜሽን ለማግኘት ምንም አይነት ጊዜ አይፈጅብንም፥ በደቂቃ ውስጥ እናገኘዋለን።  ድሮ ድሮ ሲያመን ቶሎ ብለን ለመሄድ የምናስበው ዶክተር ጋር ነበር፥ አሁን አሁን ግን ጎግልዬ ምልክቱን ንገሯት እንጂ፥ በሽታችሁን ለቤተሰብ ሳይሆን ለራሳችሁ በግልጽ ታበስራቹሀለች። ትንሽ ቆይቶ መድሀኒቱንም ከፋርማሲ የማዘዝ መብት ሳይሰጣት ይቀራል ብላችሁ ነው?  “እውቀት ሀይል ነው” እያሉ ይናገራሉ። ለነገሩ አባባሉ እውነት ነው። እውቀት ብዙ ነገሮችን በተሻለ መንገድ ለማከናወን የሚጠቅመን አስፈላጊ ነገር ነው። ህይወታችንን በተለያየ አቅጣጫ እያቀለለ፥ የቀን ለቀን ተግባሮቻችንን በተሻለ መንገድ እንድናከናውን የሚረዳን ነገር ነው። እኛ እንኳን በየቀን ኑሮአችን ውስጥ በምንፈልጋቸው የተለያዩ እርዳታዎች ዙሪያ የምንፈልገው፥ እውቀት ያለውን ሰው ነው። ለምሳሌ ትንሽ ቢያመን፥ እኛን የሚረዳበት እውቀት ያለው የህክምና ባለሙያ ስለሆነ፥ ቶሎ የምናስበው ወደ ዶክተራችን ጋር ለመሄድ ነው። ቤት ለመስራት ብናስብ፥ ቤት በመስራት ዙሪያ እውቀት ያላቸውን ሰዎች መሀንዲሶችን ለማናገር እንሄዳለን። መኪናችን ቢበላሽ፥ መካኒካችን ጋር በመሄድ በመኪና ዙሪያ ባለው እውቀት ችግሩን እንዲነግረንና እንዲረዳን እንጠይቃለን።  ሁላችንም በሆነ ነገር ዙሪያ ከሌሎች ነገሮች ከፍ ያለ እውቀት አለን። ለምሳሌ፣ በየቀኑ በምንሰራው ነገር ዙሪያ ከሌሎች በሌላ የስራ ዘርፍ ውስጥ ከሚሰሩ ሰዎች የተሻለ እውቀት አለን። የወር ደሞዛችንንም ልዩ ልዩ ያረገው፥ የእውቀት ደረጃችን ነው። የዚህች ምድር አሰራር እንዲህ ነው።  እውቀታችን በጨመረ መጠን፥ ሰዎችን የምንረዳበት ወይንም የምንጠቅምበት አቅም ስለሚያድግ፥ ደሞዛችንና ተፈላጊነታችን ይጨምራል። መጽሀፍ ቅዱሳችንም እንዲሁ በተለያዩ ቦታዎች እውቀት በጣም አስፈላጊ ነገር መሆኑን፥ ነፍሳችን እውቀት የሌለባት ትሆን ዘንድ መልካም አለመሆኑንና መልካም የሆነው ነፍሳችን በእውቀት መሞላትዋ እንደሆነ ጽፎልናል። ታዲያ ነፍሳችን መሞላት አለባት እያለ መጽሀፍ ቅዱስ የሚነግረን የእውቀት አይነት ከላይ እንደዘረዘርነው ስለ ጤናችን፣ ስለ መኪናችን፣ ስለ ኮምፒውተር ሲስተሞቻችን ያሉን የእውቀት አይነቶች አይደሉም። እነዚህ እውቀቶች ጊዜያዊና በዚህች ምድር እስከኖርን ድረስ ብቻ የሚጠቅሙ፥ አይምሮአችንን ብቻ እንጂ ነፍሳችንን ሊሞሏት የማይችሉ የእውቀት አይነቶች ናቸው። ነፍሳችንን የሚሞላ ግን አንድ ዘላለማዊ የሆነ እውቀት አለ። ይሄ ዘላለማዊ የሆነና ነፍሳችንን የሚሞላ እንዲሁም መጽሀፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ ይኑራችኑ የሚለን እውቀት፥ ስለ እግዚአብሄር ሊኖረን የሚገባ እውቀት ነው። እግዚአብሄርን ማወቅ ነው:: እረፉ እኔም አምላክ እንደሆንኩ እወቁ እንደሚለው፥ ነፍሳችንን የሚሞላ ብቻ ሳይሆን ነፍሳችንን ማሳረፍ የሚችል ብቸኛ እውቀት ነው። የትኛውም ምድር ላይ ያለ የእውቀት አይነት፥ ነፍሳችንን የማሳረፍ አቅም የለውም። ነፍሳችንን የሚያሳርፋት፥ እግዚአብሄርን በማወቅ ውስጥ የምናገኘው እውቀት ብቻ ነው። መጽሀፍ ቅዱስ እውነት አርነት ያወጣችኋል ሳይሆን፥ እውነትን ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል እንደሚለው፥ እውነት አርነት የሚያወጣን ስናውቀው ብቻ ነው። ስለ እውነት የምናገኘው እውቀት ነው አርነት የሚያወጣንና የሚያሳርፈን። እውነት ደግሞ እራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እውነት እግዚአብሄር ነው። ስለዚህ ብዙ ጨለማዎቻችን እየተገፈፉ፥ ወደ ሙሉ አርነት የምንወጣው፥ እግዚአብሄርን እያወቅን በመጣን መጠን ነው። አንድ ሰው በጣም ተምሮና ብዙ እውቀት አግኝቶ ትልቅ የስልጣን ደረጃ ላይ ቢደርስ እንኳን፥ እግዚአብሄርን ካላወቀ ግን ነፍሱ ባዶ ናት። እውቀት ያለው አይምሮው ውስጥ ብቻ ነው። ነፍሱ ውስጥ ምንም አይነት እውቀት የለም። አይምሮው ደግሞ እዚህ ምድር ላይ ቀሪ ነገር ነው። ስለዚህ ብዙ አመታቶች ለፍቶ የተማረው እውቀት ሊጠቅመው የሚችለው፥ እግዚአብሄር በወሰነለት በዚህች ምድር ቆይታው ብቻ ይሆናል።  “ነፍስ እውቀት የሌለባት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም” (ምሳሌ 19:2)  ስለ እግዚአብሄር የምናገኘው እውቀት፥ ነፍሳችንን ከማሳረፉም በላይ ከብዙ የጥፋት መንገዶች እኛን ማዳን መቻሉ ደግሞ በጣም አስደናቂ ነው። መጽሀፍ ቅዱስ በሆሴእ ምእራፍ 4 ቁጥር 6 ላይ ሲናገር፥ “ህዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቷል” እንደሚለው፥ ስለ እግዚአብሄር ከጎደለው እውቀት የተነሳ፥ አንድ ሰው ወይንም ጥቂት ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ፥ ህዝብ ወደ ጥፋት እንደሄደ የእግዚአብሄር ቃል ይናገራል። ዛሬም የብዙ ጥፋቶቻችን ዋና መሰረት፥ ስለ እግዚአብሄር ያለን እውቀት ማነስ ሆኖ እናገኘዋለን። መጽሀፍ ቅዱሳችን በሮሜ መጽሀፍ ምእራፍ አንድ ላይ እንደሚናገረው፥ “እግዚአብሄርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን፥ እግዚአብሄር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አይምሮ አሳልፎ ሰጣቸው” ይልና ይሄንንም ተከትሎ፥ እነዚህ ለማይረባ አይምሮ ተላልፈው የተሰጡት ሰዎች፥ ወደ ብዙ ጥፋትና ሀጢያት ውስጥ መግባታቸውን እየዘረዘረ በመናገር ቃሉ ይቀጥላል። ሰው እግዚአብሄርን ለማወቅ ባልወደደ መጠን፥ ተላልፎ የሚሰጠው ለማይረባ አይምሮ ነው። ተላልፎ የሚሰጠው፥ ከንቱ ለሆነ አይምሮ ነው። እግዚአብሄርን ማወቃችን ግን ከማይረባ አይምሮ እየጠበቀ ከንቱነትን ከእኛ ያርቃል።  እግዚአብሄርን ስላለማወቅ ስናነሳ ከህይወታቸው ብዙ ልንማርባቸው የምንችላቸው ሁለት ሰዎች በብሉይ ኪዳን ውስጥ ተጽፈው እናገኛለን። ሁለቱ የኤሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ። የኤሊ ልጆች፥ የአባታቸውን የክህነት አገልግሎት እያዩ ያደጉ፥ እነርሱም ልክ እንደ አባታቸው የክህነትን አገልግሎት ተቀብለው፥ ካህናቶች በመሆን በቤተ መቅደስ ውስጥ ለማገልገል የተሾሙ የእግዚአብሄር አገልጋዮች ነበሩ። መቼም ስለ ክህነት አገልግሎት ስናስብ፥ አንድ ሰው ካህን ከሆነ ከሌሎች እግዚአብሄርን ከሚከተሉ ሰዎች ስለ እግዚአብሄር የተሻለ እውቀት ሊኖረው እንደሚገባ እናስባለን። በተለይ ደግሞ በብሉይ ኪዳን ይሄ አገልግሎት በጣም ከባድና ብዙ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው አገልግሎት መሆኑን እናውቃለን። በክህነት አገልግሎት የሚያገለግሉት የኤሊ ልጆች፥ በቤተ መቅደስ ውስጥ ብዙ እግዚአብሄርን ደስ የማያሰኙ ነገሮችን የሚያደርጉ፣ የክህነቱን ስርአት ትክክል ባልሆነ መንገድ የሚያደርጉ፣ የእግዚአብሄርን ቁርባን የሚንቁ፣ በመገናኛው ድንኳን ደጅ ከሚያገለግሉት ሴቶች ጋር የሚተኙና እግዚአብሄርን የሚያስቆጡ፥ ሀጢያታቸውም በእግዚአብሄር ፊት ታላቅ የሆነችባቸው ልጆች ነበሩ። ታዲያ ስለ ኤሊ ልጆች ሀጢያት የሚናገረው የእግዚአብሄር ቃል ወደዚህ ድርጊት የወሰዳቸውን ዋና ምክኒያት እንዲህ በማለት ሳይናገር አላለፈም። “የኤሊ ልጆች ምናምንቴዎች ነበሩ፥ እግዚአብሄርንም አያውቁም ነበር” በማለት እዚያው በ1ኛ ሳሙኤል ምእራፍ 2፡12 ላይ ይነግረናል። የኤሊ ልጆች እግዚአብሄርን አለማወቃቸው ወደ ከንቱነት ወደ ምናምንቴነት ህይወታቸውን ከመውሰዱም በላይ፥ ከላይ በሮሜ መጽሀፍ ላይ ለማይረባ አይምሮ የተሰጡ ሰዎች ብሎ ካላቸው ሰዎች ጋር ተመሳሳይ የሆነ የህይወት አካሄድ ሲኖራቸው እንመለከታለን።  ሰው እግዚአብሄርን ባላወቀው መጠን፥ ህይወቱ የሚሄደው ወደ ከንቱነት ነው። እነዚህ በክህነት ያገለግሉ የነበሩት የኤሊ ልጆች፥ አገልግሎታቸው እግዚአብሄርን ከማወቅ ውጪ ነበር። እግዚአብሄርን በማወቅ አልነበረም ያገለግሉ የነበሩት። እግዚአብሄር ደግሞ ልናገለግለው ከመነሳታችን በፊት፥ መጀመሪያ የሚፈልገው እርሱን እንድናውቀው ነው። ለዚያ ነው በሆሴዕ መጽሀፍ ላይ “እግዚአብሄርን ማወቅ ጠልተሀልና እኔም ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሀለሁ” በማለት፥ እግዚአብሄር እርሱን ከማወቅ ውጪ የሆነውን ክህነት ወይንም አገልግሎት እንደሚጠላ የተናገረው። ሰውን እንኳን እኮ እናገልግለው ብለን ስንነሳ፥ ያ ሰው ማን መሆኑን ባህሪውን፣ የሚወደውን፣ የሚጠላውን፥ የሚፈልገውን፣ የማይፈልገውን ነገር ጠንቅቀን ካላወቅን፥ ያንን ሰው እናገልግለው ብለን ልናበሳጨውም እንችላለን። ለእኛ በጣም ጥሩና የሚያስደስተን አገልጋይ ማለት፥ እኛ ማን መሆናችንን ባህሪያችንንና ፍላጎታችንን ጠንቅቆ ያወቀና የተረዳ ሰው ነው። ትልቅ የሆነውን አምላክ ልናገለግል ስንነሳ፥ መጀመሪያ የሚፈልገው እንድናውቀው ነው። ማንነቱን እንድናውቅ፣ የሚወዳቸውን፣ የሚጠላቸውን ነገሮች እንድናውቅ፣ የሚያስደስተውን ነገሮች ደግሞም የሚያሳዝነውን ነገሮች ባህሪያቶቹን ሁሉ እንድናውቅ ነው። በዚህ እውቀት ውስጥ የሆነ አገልግሎት፥ እርሱ እንደሚፈልገው ስለሚሆን ደስ ያሰኘዋል። በተለይ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ለማገልገል እድል የተሰጠን ሁላችንም እንደመሆናችን፥ አገልግሎቶቻችን መጀመር ያለባቸው እግዚአብሄርን ከማወቅ ነው።  የእግዚአብሄር መሻት፥ የሰው ልጆች በሙሉ እሱን እንዲያውቁት፥ ምድር ሁሉ እሱን በማወቅ እንድትሞላ ነው። መቼም እግዚአብሄር የሚባል ሁሉን የፈጠረ አምላክ እንዳለ ብዙዎቻችን ብናውቅም፥ እግዚአብሄርን በቅርበት ማወቅ፣ ከእርሱ ጋር ቅርበት ያለው ወዳጅነት መኖር፣ በህይወት መንገዶቻችን ውስጥ እሱን ማወቅ ደግሞ ሌላ ራሱን የቻለ ነገር ነው። ለምሳሌ እናንተን ሰዎች ሁሉ በተመሳሳይ ደረጃና መጠን አይደለም የሚያውቋችሁ። ሰዎች ከእናንተ ጋር ባሳለፉት ጊዜ መጠን፥ ስለ እናንተ ያላቸው የእውቀት ደረጃ የተለያየ ነው። ከሰዎች ጋር

Article

ኢዮብ

Home Blog Book About Contact X Order Book ኢዮብ Audio ብዙ ነገሮችን እንዳስብና እንዳሰላስል ከሚያደርጉኝ መፅሀፎች ውስጥ አንዱ የኢዮብ መፅሀፍ ነው። ብዙ ጊዜ የኢዮብን መፅሀፍ ስናስብ ቶሎ ብሎ ትዝ የሚለን፥ ኢዮብ ያለፈባቸው በጣም ከባባድ ፈተናዎች ናቸው። መቼም የእግዚአብሄር ፀጋ የማያሳልፈው ነገር የለም እንጂ ማናችንም ብንሆን፥ ኢዮብ ያለፈባቸውን ፈተናዎች እንኳን ልናልፍባቸው፥ ለማሰብ እንኳን የሚከብዱን ናቸው። በአንድም ሆነ በሌላ ግን፥ ዛሬ ላይ በህይወታችን የሚያልፉት ችግሮች ልዩ ልዩ ይሁኑ እንጂ፥ ኢዮብን የተሰሙት ስሜቶች ሲሰሙን፥ የተናገራቸውን ቃሎች ስንናገር፥ ኢዮብ እግዚአብሄርን የጠየቀውን አይነት ጥያቄዎች ስንጠይቅ ራሳችንን እናገኘዋለን። መፅሀፉ እንደሚነግረን ከሆነ፥ ኢዮብ ፍፁምና ቅን፣ እግዚአብሄርን የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ሰው ነበረ። እግዚአብሄርን ከመፍራቱ ብዛት ምናልባት ልጆቼ እግዚአብሄርን በድለውት ይሆን? በማለት በልጆቹ ቁጥር ልክ ለእግዚአብሄር መስዋእትን የሚያቀርብና ልጆቹን የሚቀድስ፥ ለእግዚአብሄር ከፍተኛ የሆነ ፍርሀትና አክብሮት ያለው ሰው ነበር። ኢዮብ በእግዚአብሄር ፍጹም የተወደደና እግዚአብሄር ቅጥር ሰርቶ ይጠብቀው የነበረ ሰው ነው ። በነገራችን ላይ፥ እግዚአብሄር ቅጥር ሰርቶ እንደሚጠብቀን የተማርኩት ከኢዮብ መፅሀፍ ነው። የትኛውም ክፉ ነገር ይሄንን ቅጥር ማለፍ አይችልም። ሰይጣንም ቢሆን ይሄንን ቅጥር አልፎ ኢዮብን የነካው፥ በተፈቀደለት መጠን ብቻ ነው። ያልተፈቀደለትን አልነካም። ለዚያ ነው በአንደኛ ቆሮንቶስ መጽሀፍ ላይ ሲናገር፥ “ከምትችሉት በላይ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሄር” ተብሎ የተፃፈው። ፈቃጅ አለ። በሰማይ ተቀምጦ፥ በህይወታችን ላይ የሚሆነውን ነገር ሁሉ የሚፈቅድ ፈቃጅ አለ።  የኢዮብን ታሪክ ብዙዎቻችን እንደምናውቀው ታዲያ፥ እግዚአብሄር በእሱ ላይ በመወራረድ፥ ልጆቹን ሀብቱን እና ጤናውን እንዲያጣ አደረገው። በምድር ላይ ያለን ሰዎች የተባልን ፍጥረቶች በሙሉ፥ የምናጣው ነገር ልዩ ልዩ ይሁን እንጂ፥  ዋናው ችግራችን ማጣት ብቻ ነው። አንዳንዱ ሰው ገንዘብ ያጣል፥ ሌላው ጤና ያጣል፥ ሌላው ሰው ያጣል፥ ሌላው ፍቅር ያጣል፥ ሌላው ስራ ያጣል፥ ሌላው ደግሞ ሰላም እና ደስታ ያጣል። ኢዮብ ባለፈባቸው በእነዚህ ልጆቹን፥ ጤናውንና ሀብቱን የማጣት ችግሮች ዋና ጥያቄና ሙግቱ፥ ይሄ እንዲደርስብኝ ምን የሰራሁት በደል አለ? የሚል ነበር። ሙሉ መፅሀፉን ስታነቡ፥ የኢዮብ ጩሐት፥ ከእግዚአብሄር ጋር የነበረው ሙግት፣ ይሄ ነገር በእኔ ላይ እንዲደርስ የበደልኩት በደል የለም የሚል ነበር። ሊያፅናኑት የመጡት 3ቱ ወዳጆቹ ደግሞ፥ አይ ተው ግድ የለህም! እግዚአብሄር በፃድቅ ሰው ላይ እንዲህ ያለ ክፉ ነገር ሲያመጣ አይተን አናውቅም። አፍህን ሞልተህ ፃድቅ ነኝ አትበል። እግዚአብሄርን የበደልክበት የሆነ ነገርማ ይኖራል በማለት የሚሞግቱት ናቸው። መፅሀፉ እስከ 31ኛ ምእራፍ ድረስ፥ ኢዮብና ወዳጆቹ ባልተመለሰ ጥያቄ ውስጥ ያደረጉትን ንግግር የሚናገሩ ምእራፎች ናቸው። እስኪ ያልተመለሱ ጥያቄዎቻችሁን አስቡዋቸው። እኔማ አንዳንዴ የራሴን ህይወት ሳስበው፥ ምነው ልክ እንደ ፊልም ታሪኬን ፈጠን ፈጠን አርጌ መጨረሻዬን ባየሁት የምላቸውና፥ ልክ እንደ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ መጨረሻቸውን ለማየት፥ በጉጉት የምጠብቃቸው የህይወት ጉዳዮች አሉኝ። እናንተስ?  ኢዮብና ሶስቱ ጓደኞቹ 31 ምእራፍ ሙሉ እርስ በእርስ የሚያደርጉትን ንግግር፣ እግዚአብሄር ቁጭ ብሎ ያዳምጣቸው ነበር። አቤት የኢዮብ ጓደኞችማ የሚገርሙ እኮ ናቸው። በጣም የሚገርም የሚገርም ነገር እኮ ነው ስለ እግዚአብሄር ይናገሩ የነበሩት። ዛሬ ላይ እኮ እነሱ የተናገሩትን እየወሰድን ነው ጥቅስና ትምህርት የምናወጣባቸው። ቆይ እንዲያውም ከ3ቱ የኢዮብ ጓደኞች፣ ሶፋር የተባለው ጓደኛው ለኢዮብ ስለ እግዚአብሄር ከተናገረው ውስጥ ትንሹን ላንብብላችሁ። ምእራፍ 11 ቁጥር 7። “ኢዮብ፣ የእግዚአብሄርን ጥልቅ ነገር ልትመረምር ትችላለህን? ወይስ ሁሉን የሚችል አምላክን ፈጽመህ ልትመረምር ትችላለህን? ከሰማይ ይልቅ ከፍ ይላል ምን ልታደርግ ትችላለህ፧ ከሲኦልም ይልቅ ይጠልቃል ምን ልታውቅ ትችላለህ? ርዝመቱ ከምድር ይልቅ ይረዝማል። ከባህርም ይልቅ ይሰፋል።”   በጣም የሚገርመው ነገር ግን የኢዮብ ጓደኞች ምንም ትክክለኛና ስለ እግዚአብሄር አስገራሚ አስገራሚ ነገር ቢናገሩም፥ እግዚአብሄር ግን ፈጽሞ በንግግራቸው አልተደሰተም። ምክኒያቱ ደግሞ፥  ንግግራቸው በሙሉ እግዚአብሄር በኢዮብ ላይ ያለውን ሀሳቡን በመረዳት ስላልነበረ ነው። ከዚህ የተነሳ ንግግራቸው ኢዮብ ላይ ወደ መፍረድ ያደላ ነበር። ዋናው የምንናገረው ነገር ትክክለኛነት ብቻ አይደለም። ዋናው በምንናገረው ጉዳይ ላይ ያለውን የእግዚአብሄርን ሀሳብ መረዳት ነው። ዋናው የጊዜው ቃል ነው ወይ ነው? እግዚአብሄር በዚያ ሰአት፥ ለዚያ ነገር ወይንም ጉዳይ ወይንም ለእነዚያ ሰዎች ሊል የፈለገው ነገር ነው ወይ ነው ዋናው ቁምነገሩ። እግዚአብሄር በፍጹም ያለ እውቀት እንድንናገር አይፈልግም። አንዳንዴ ሰዎች በሚያልፉበት ጥሩም ሆነ መጥፎ ነገር ውስጥ፣ የእግዚአብሄርን ሀሳብ ካልተረዳን፣ ዝም እንደማለት ጥበብና ማስተዋል የለም። አንዳንዴ መልካም የሚመስሉ ነገሮችን ከመናገር ይልቅ፥ ዝም ማለት የሚሻልበት ጊዜ አለ። ዛሬ ላይ ግን ዝም ብላችሁ ዘመኑን ብታዩት፣ ሁሉ ሰው ባልገባውና ባልተረዳው የእግዚአብሄር ሀሳብ ውስጥ እየገባ አስተያየት ሰጪ የሆነበት ጊዜና ዘመን ነው። በሰዎች ጉዳይ ላይ፣ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ፣ በአለም አቀፍ በሽታዎች ላይ የመሰለንን ነገር የምንናገርበት አስፈሪ ጊዜ ነው። የኢዮብ ጓደኞች፥ በመፅሀፉ መጨረሻ ትክክለኛው የእግዚአብሄር ሀሳብ እስከሚገለጥበት ጊዜ ድረስ፣ እየተናገሩ ያሉት ነገር በሙሉ ትክክል ነበር የሚመስላቸው።  “ስለዚህ ክፉ ዘመን ነውና፥ በዚያ ዘመን አስተዋይ የሚሆን ዝም ይላል”  (ትንቢተ አሞፅ ምእራፍ 5፡13)  ኢዮብ፥ በዛ ሁሉ ያልተመለሱ ጥያቄዎችና ግራ የሚያጋባ የህይወት ፈተና ውስጥ ሲያልፍ እግዚአብሄር እንደተወራረደበትም ሆነ ሰይጣን ስለ እሱ ስለተናገረው ነገር ምንም የሚያውቀው ነገር አልነበረም። መጨረሻ ላይ እራሱ፥ አውቆ ይሆን የሞተው? እኔማ ታሪኩን እያነበብኩ መሀል መሀል ላይ ያሳዝነኝና ንገሪው ንገሪው ይለኛል። “ይኸውልህ ኢዮብ፥ ብዙ ብዙ ትርፍ ቃሎችን ስትናገር እየሰማሁክ ነው ያለሁት። እኔ ግን እውነቱን ልንገርህ? ይኸውልህ ይሄን ሚስጥር ለአንድ ሰው እንዳትናገር። ሌላው ቢቀር ለእነዚህ ሊያፅናኑህ ለመጡት ለ3ቱ ጉዋደኞችህ እራሱ እንዳትነግራቸው። እኔ አሁን በጣም ስላሳዘንከኝ ነው የምነግርህ። ይኸውልህ፥ እግዚአብሄር በጣም ባንተ ስለተማመነ እየተወራረደብህ ነው ያለው እንጂ፥ አንተ ሀጢያት ስለሰራህ ምናምን አይደለም። አንተ ግን ዋናውን እውነቱን ሳታውቅ ብዙ ብዙ ነገር ስትናገር እየሰማሁህ ነው” ልለው ብዬ እተወዋለሁ። ኢዮብም ልክ እንደ ጓደኞቹ፥ ይናገር የነበሩት ንግግሮች ከእውቀት ውጪ እንደሆኑ በመፅሀፉ በ3 የተለያዩ ቦታዎች ላይ ይነግረናል። በምእራፍ 35 ቁጥር 16 ላይ እንዲያውም፥ ኤሊሁ የተባለ አንድ በእድሜ ታናሽ፥ ነገር ግን የእግዚአብሄር መንፈስ የሞላበት ልጅ ስለ ኢዮብ ንግግር እንዲህ ይላል። “ኢዮብ አፉን በከንቱ ከፍታል። ያለ እውቀትም ቃሉን ያበዛል” በማለት ኢዮብ ይናገራቸው የነበሩት ንግግሮች ከእውቀት ውጪ እንደሆኑ ይናገራል። እንደ ኢዮብ በከባድ ነገሮች ውስጥ ስናልፍ፥ እግዚአብሄር እንዲረዳን አጥብቀን መፀለይ ካለብን ነገሮች አንዱ፥ ባልገባን ነገሮች ላይ ዝም የምንልበትን አቅም እንድናገኝ ነው። ለመናገር ጊዜ እንዳለው ሁሉ፥  ዝም ለማለትም ጊዜ አለው። አንዳንዴ ህይወቶቻችን ላይ ዝም ብሎ መፀለይን፥ ዝም ብሎ እግዚአብሄርን መጠበቅን፥ ዝም ብሎ መቆየትን የሚጠይቁ ጉዳዮች ይኖሩናል።  “ይሄ ሁሉ ነገር ይደርስብኝ ዘንድ የሰራሁት ምንም ጥፋት የለም” በሚለው የኢዮብ ጥያቄና ሙግት ውስጥ ትክክለኛ የሚመስል ነገር ቢኖረውም፣ እግዚአብሄር ለዚህ ሙገቱ የመለሰለትን አንድ አስገራሚ ነገር እስኪ በምእራፍ 40 ቁጥር 8 ላይ እናንብብ:: ኢዮብ “አንተ ፃድቅ ትሆን ዘንድ፥ በእኔ ትፈርዳለህን?” በማለት እግዚአብሄር ኢዮብን ይጠይቀዋል። አንተ ራስህን አፅድቀህ፥ እኔን ትኮንናህን? አንተ ራስህን ትክክለኛ አድርገህ፣ እኔን ተሳስተሀል እያልከኝ ነው? እግዚአብሄር ማጉረምረምን አጥብቆ የሚጠላው፣ ማጉረምረም በውስጡ፥ “እግዚአብሄር በህይወቴ ውስጥ እያረገ ያለው ነገር ትክክል አይደለም” የሚል ድምጽ ስላለው ነው። አንዳንድ ጊዜ በህይወቶቻችን ውጣ ውረዶች ውስጥ፣ ጥያቄዎች ይኖሩን ይሆናል። እግዚአብሄርን ለመጠየቅ ስንነሳ ግን ጥያቄዎቻችን፣ የእግዚአብሄርን ትክክለኛነት ከማወቅ መጀመር አለባቸው። ጥያቄዎቻችን፥ የእግዚአብሄርን ፃድቅነት ከማወቅ መጀመር አለባቸው። ጥያቄዎቻችን በእግዚአብሄር ፊት ሞገስ የሚያገኙት፣ ስለ ማንነቱ ባለን እውቀት ውስጥ ስናቀርባቸው ነው። ሁኔታዎች ይሄንን ባይሉንም እንኳን፣ መልካም አምላክ መሆኑን ከማወቅ ተነስተን ስንጠይቀው፣ እንደሚወደንና ለህይወታችን መልካም ሀሳብ እንዳለው ከመረዳት ተነስተን ስንጠይቀው፣ ጥያቄውን ያመጣንበት ልብ ከቃሉ ጋር የተስተካከለ ስለሆነ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ፈጽሞ አይዘገይም። የምናልፍባቸው ነገሮች፥ የእግዚአብሄርን ማንነት እንዲተረጉሙልን እድል መስጠት የለብንም። በተቻለን መጠን፥ የእግዚአብሄርን ማንነትና የእኛን የህይወት ውጣ ውረዶች ለያይተን ማየት አለብን። ለዛ ነው

Article

አንዲቷ  ልመና

Home Blog Book About Contact X Order Book አንዲቷ  ልመና Audio ከሌሊቶች ውስጥ በአንዱ ሌሊት ነው እግዚአብሄር ለንጉስ ሰለሞን በራእይ ተገልጦ ምን እንድሰጥህ ለምነኝ ያለው። ለእኛ ለሰዎች መለመን ብዙም የሚያስደስተን ነገር አይደለም። ምክኒያቱ ደግሞ የበዛውን ጊዜ ለመስጠት ስንነሳ፥ ከራሳችን የሚጎልብን ነገር ስላለ ነው። አብዛኛውን ጊዜ ስንሰጥ፥ ከሙላታችን ሳይሆን ከጉድለታችን ነው። እሱንም ደግሞ የምንጠየቀውን ነገር የመስጠት አቅሙ ካለን ነው። ይሄ ሁሉን የሚችለው አምላክ ግን፥ ምንም ነገር ቢለመን መስጠት የሚችለው ሁሉንቻይ ማንነቱን ተማምኖ ነው የወደድከውን ለምነኝ እያለ ወደ ሰለሞን የመጣው። ለማንም ሰው የትኛውንም ያህል ብዙ ነገር ቢሰጥ፥ ከእርሱ ላይ አንዳች የሚጎልበት ነገር የለም። ምንም ነገር ብንጠይቀውም ከአቅሙ በላይ ስለማይሆን አይደነግጥም። የማልችለውን ነገር ይጠይቁኝ ይሆን ብሎም አይፈራም። ማድረግ ባልችልስ ብሎ ደግሞ አይጨነቅም። ታዲያ፥ ሰለሞን በተሰጠው በዚህ እድል የጠየቀው ጥያቄ እግዚአብሄርን እጅግ በጣም ደስ ከማሰኘቱ የተነሳ፥ ከለመነውና ካሰበው በላይ ብቻ ሳይሆን፥ ያለመናቸውንም ብዙ ነገሮች አብሮ ሰጥቶታል። “እግዚአብሄርም አለው፥ ፍርድን ትለይ ዘንድ ለራስህ ማስተዋልን ለመንህ እንጂ፥ ለራስህ ብዙ ዘመናትን ባለጠግነትንም የጠላቶችህንም ነፍስ ሳትለምን ይህን ነገር ለምነሀልና፥ እነሆ እኔ አንደ ቃል አድጌልሀለሁ። እነሆ ማንም የሚመስልህ ከአንተ በፊት እንደሌለ፥ ከአንተም በኋላ እንዳይነሳ አድርጌ፥ ጥበበኛና አስተዋይ ልቡና ሰጥቼሀለሁ።  ደግሞም ከነገስታት የሚመስልህ ማንም እንዳይኖር፥ ያለመንከውን ባለጠግነትና ክብር ሰጥቼሀለሁ። አባትህም ዳዊት እንደ ሄደ ስርአቴንና ትእዛዜን ትጠብቅ ዘንድ በመንገዴ የሄድህ እንደሆነ፥ እድሜህን አረዝመዋለሁ።” (1ኛ ነገስት 3፥11-14) የሰለሞን ልመና እግዚአብሄርን እጅግ በጣም ደስ አሰኝቶት ነበር። ለካ እግዚአብሄር ከመመለሱ በፊት፥ ጸሎቶቻችንንና ልመናዎቻችንን ይመዝናቸዋል። ከልመናዎቻችን መካከል እንደ ፈቃዱ የሆኑና እርሱን በጣም የሚያስደስቱት፥ እንዲያውም ያለመናቸውን ሌሎችም ነገሮች ጨምሮ እንዲሰጠን የሚያስገድዱት የልመናና የጸሎት አይነቶች አሉ። እግዚአብሄር መልስ ከመስጠቱ በፊት፥ የጠየቅነውን ጥያቄ ከፈቃዱ ጋር ይመዝነዋል። ባይመዝነውማ ኖሮ፥ ሁሉን መስጠት ስለሚችል የለመነውን በሙሉ ሰጥቶን ቢሆንማ ኖሮ፥ እርግጠኛ ነኝ ማናችንም እዚህ አሁን ያለንበት ቦታ ጋር አንሆንም። ምናልባትም በህይወት የማንቆይ ብዙዎች እንኖራለን። የለመነውን ሁሉ ያልሰጠን እግዚአብሄር ይባረክ። ጥያቄዎቻችንን ሁሉ ከዘላለም ሀሳቡ አንጻር እያመዛዘነ፥ ለእኛ ቢገባንም ባይገባንም ከብዙ ፍቅሩ የተነሳ፥ በማስተዋል የሚመልስልን አምላክ ይባረክ። ዳዊትም አለ “እግዚአብሄርን አንዲት ነገር ለመንኩት፥ እርሷንም እሻለሁ። በህይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሄር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሄርን፥ ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።” (መዝሙር ዳዊት 27:4) ይሄ፥ ዳዊት ከዚህ በፊት እግዚአብሄርን የለመነው የመጀመሪያ ልመናው አይደለም። በህይወቱ የለመነው የመጨረሻ ልመናውም አይደለም።  እንደማንኛችንም ሰዎች፥ ብዙ ጊዜ ጸልዮ፥ ከእግዚአብሄርም ሌሎች ልመናዎችን ለምኖ ያውቃል። ነገር ግን ይህቺ ከብዙ ልመናዎቹ የበለጠችበት ብርቱ ልመናው ነች። ብዙ ነገሮችን አስቦ አውጥቶና አውርዶ፣ ስለ እግዚአብሄር ባገኘው እውቀትና መገለጥ ውስጥ ሆኖ፣ በህይወቱ እግዚአብሄር ማን እንደሆነ፥ እግዚአብሄር ለእርሱ ምን ማለት እንደሆነ አስቦ፣ ከነፍሱ ጋር ተማክሮ፥ ከልቡ ጋር ተጨዋውቶ፥ ብዙ ነገሮችን አይቶና ገምግሞ እግዚአብሄርን የለመነው ልመና ነው። ይሄንን የምለምነውን አንዲት ልመና ደግሞ እሻዋለሁ አለ። “ለዘላለም በእግዚአብሄር ቤት ውስጥ መኖር፣ ደስ የሚያሰኘውን እግዚአብሄርን ማየት፣ መቅደሱንም መመልከት እፈልጋለሁ አለ።” ዳዊት እግዚአብሄርን ልክ እንደለመነው፥ እግዚአብሄር ልመናውን ሰምቶለታል። በህይወቱ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሄር ቤት ኖሯል። ደስ የሚያሰኘውን እግዚአብሄርን ተመልክቷል። በእግዚአብሄር ቤት መኖር ብቻ ሳይሆን፥ በህይወቱ ዘመን ሁሉ የእግዚአብሄርን ሀሳብና ፈቃድ አገልግሎ እንዲያልፍ፥ በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ይሄ ነው የማይባል አሻራ እንዲያሳርፍ፥ የራሱን ዘመን ፈጥሮ፥ እኛ እንኳን እስከዛሬ የዳዊት አምላክ እያልን፥ ዳዊት ከእግዚአብሄር ጋር የነበረው ግንኙነት ህይወታችንን እየለወጠው ይቀጥላል።  ለዘላለም በእግዚአብሄር ቤት መኖር፣ ደስ የሚያሰኘውን እግዚአብሄርን ማየት፣ መቅደሱንም መመልከት ለዳዊት፥ ከልመናዎቹ ሁሉ የበለጠችበት ብርቱ ልመናው ነበረች። ትልቁ ልመናችሁ ምንድነው? ልባችሁ ውስጥ ያለው መሻት፥ የነፍሳችሁ ልመና ምንድነው? የውስጣችሁ ጩኸት፥ የዘውትር መሻታችሁና የአንድ ነፍሳችሁ ጸሎት ምንድነው? ደጋግማችሁ እግዚአብሄርን የምትጠይቁት አንዲቷና ከሁሉ የምትበልጠው ልማናችሁ ምንድናት? መልሱን ለእናንተ እየተውኩ፥ እኔም በተራዬ ልክ እንደ ዳዊት ብዙ ነገሮችን አውጥቼ ካወረድኩ፥ ብዙ ካሰላሰልኩ በኋላ እግዚአብሄር ባስተማረኝ ነገሮችና እስከዛሬ ድረስ በተገለጡልኝ መገለጦች ውስጥ ሆኜ፥ እግዚአብሄርን አንዲት ነገር ለመንኩት። እርስዋንም እጅግ በጣም እሻለሁ። “በዘመኔ ሁሉ የእግዚአብሄርን ፈቃድ እኖርና አገለግል ዘንድ፥ በዚህ መንገድ ውስጥ የሚያስከፍለውን ዋጋ ሁሉ መክፈል እችል ዘንድ” ብዬ ለመንኩ። እናንተስ? የእግዚአብሄርን ፈቃድ መኖር ቀላል ህይወት ነው። አልጋ በአልጋ ነው ብንል ራሳችንን ውሸታሞች እናረጋለን። እንዲያውም ኢየሱስ፥ “እኔን መከተል የሚፈልግ ቢኖር፥ መስቀሌን ተሸክሞ ይከተለኝ” በማለት እርሱን መከተል፥ ከመስቀል ወይንም ዋጋ ከመክፈል ውጪ እንዳልሆነ ግልጹን ተናግሯል። የእርሱን ፈቃድ እኖራለሁ ብለን ከመነሳታችን በፊት፥ በዚህ መንገድ ውስጥ የሚያስከፍለውን ዋጋ ለመክፈል ካልወሰንን፥ መንገዱ መሀል ላይ ግራ መጋባታችን የማይቀር ነው። የነገሩ አስደሳችነት ግን ይሄ ነው። በዚህ ህይወት ውስጥ የምንከፍለው ዋጋ በሙሉ፥ በመቶ እጥፍ በሚመጣው ህይወት ውስጥ የምንቀበለው ትልቁ ሽልማታችን ነው። የእግዚአብሄር ቃል ሲናገር፥ “አለሙም ምኞቱም ያልፋሉ፥ የእግዚአብሄር ፈቃድ ግን ለዘላለም ይኖራል” እንደሚለው፥ ሁሉ ነገር ሲያልፍ፥ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው የእግዚአብሄር ፈቃድ ብቻ ነው። እኛ እራሳችን፥ ጊዜያችንን ስንጨርስ፥ ከዚህች ምድር አላፊዎች ነን። ዛሬ ላይ በዚህ ህይወት የምንኖረው የእግዚአብሄር ፈቃድ ግን፥ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖር ነው። ዛሬ ላይ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለመኖር የምንከፍላቸው ዋጋዎች በሙሉ፥ ለዘላለም የሚኖሩ ናቸው። መጽሀፍ ቅዱሳችን ላይ የተጻፉልን አባቶቻችን፥ ከዚህች ምድር ካለፉ ስንትና ስንት ሺህ አመታቶች ቢቆጠሩም፥ በተሰጣቸው ዘመን፥ ዋጋ በመክፈል የኖሩት የእግዚአብሄር ፈቃድ ግን፥ ለዘላለም ጸንቶ ሲወራና ሲነገር ይኖራል። ልክ አባቶቻችን የኖሩት የእግዚአብሄር ፈቃድ ተጽፎ ዛሬ እንደምናነበው፥ እኛም ዛሬ የምንኖረው ህይወት፥ እኛም ዛሬ ላይ የምንኖረው የእግዚአብሄር ፈቃድ የሚጻፍና ለዘላለም የሚኖር ነው። እያንዳንዱ ዋጋ የሚጻፍ ነው። እያንዳንዱ እንደ እግዚአብሄር ሀሳብ የምንከፍለው ዋጋ በሙሉ መንፈሳዊ አለም ላይ የሚጻፍ ነው። ይሄ የምንነጋገረውን ነገር በደምብ የሚያስረግጥልንን አንድ ምሳሌ እስኪ ወስደን እንመልከት። የዘፍጥረትን መጽሀፍ የጻፈው ሙሴ ነው። የፍጥረትን መጀመሪያ፥ እንዲሁም በዘፍጥረት መጽሀፍ ላይ የተጻፉትን ሰዎች ታሪክ በሙሉ የጻፈው ሙሴ ነው። እነዚህ ለእኛ ምሳሌ ይሆናሉ ተብለው፥ በዘፍጥረት መጽሀፍ ላይ የተጻፉልን ሰዎች በነበሩበት ዘመን፥ ሙሴ ገና አልተወለደም ነበር። ሙሴ የተወለደው፥ እነርሱ ካለፉ ከብዙ መቶ አመታቶች በኋላ ነው። በዘፍጥረት መጽሀፍ ላይ እንደምናነበው፥ እነ አቤል በእግዚአብሄር ፊት የተወደደ መስዋእት ሲያቀርቡ፣ እነ ሄኖክና እነ ኖህ አካሄዳቸውን ከእግዚአብሄር ጋር ሲያደርጉ፣ እነ አብርሀም እግዚአብሄርን በመታዘዝ 75 አመታቶች ሙሉ የኖሩበትን ሀገር በእምነት ታዘው ጥለው ሲወጡ፣ እነ ዮሴፍ “በእግዚአብሄር ፊት ይሄንን ሀጢያት አላደርግም” ብለው ሲሸሹ፥ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለመኖር ዋጋ ሲከፍሉ፥ ሙሴ በቦታው አልነበረም። ሙሴ አልተወለደም ነበር። የእነዚህን ሁሉ ሰዎች ታሪክና የኖሩትን ህይወት እንዲጽፍ፥ ያልነበረበትን ህይወት መገለጥ ለሙሴ የሰጠው እግዚአብሄር ነው። እነዚህ ሰዎች ኖረው ካለፉ በኋላ፥ በህይወታቸው ውስጥ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለመኖር የከፈሉትን ዋጋ፥ ከተጻፈበት መንፈሳዊ አለም ውስጥ አውጥቶ ለትውልድ ጽፎ ያስቀምጥ ዘንድ፥ ለሙሴ የሰጠው እግዚአብሄር ነው። እነዚህን ትውልድ ሲታነጽ የሚኖርባቸውን ትልልክ የታሪክ መገለጦች ለሙሴ የሰጠው እግዚአብሄር እራሱ ነው። ሙሴ እራሱ እየጻፈ ይደነቃል። wow ይላል። ለካ አባቶቼ ለእግዚአብሄር ኖረዋል። ለካ ከእኔም በፊት ይሄ ሁሉ ታሪክ አለ በማለት፥  ለራሱ ህይወት እየተማረ፥ የተሰጠውን መገለጥ በወረቀትና በብእር ለእኛ እንዲገባን አድርጎ ጽፎልን እንዲያልፍ ያደረገው እግዚአብሄር ይባረክ።  እነ ኖህ፣ እነ ሄኖክ፣ እነ አብርሀም ይስሀቅ ያቆብና እነ ዮሴፍ እነዚህ ትልልቅ ታሪክ ያላቸውና ከእግዚአብሄር ጋር ለመጓዝ ዋጋ የከፈሉት የእግዚአብሄር ሰዎች፣ ልክ እንደ እኔና እንደ እናንተ ሰዎች ነበሩ። መላእክቶች ወይንም ልዩ ፍጥረታት አልነበሩም፥ ሰዎች ነበሩ። መጽሀፍ ቅዱስ የእነዚህን ሰዎች ህይወት በስፋት የጻፈው፥ የህይወታቸው አሻራ መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲያርፍ ያረገው፥ ዋጋ በመክፈል ለመኖር የወሰኑት የእግዚአብሄር ፈቃድ ነው። የእግዚአብሄርን ፈቃድ መኖር። ዘላለም የማይጠፋ ህይወት መኖር። ለዘላለም የሚኖር ታሪክ መኖር። እነዚህ ታሪካቸው በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ የተጻፈልን

Article

ችላ ያልነው ጠላታችን

Home Blog Book About Contact X Order Book ችላ ያልነው ጠላታችን Audio አንዳንድ ጊዜ ስፀልይ፥ ስዘምር፥ መፅሀፍ ቅዱሴን ሳነብ በጣም መንፈሳዊ እንደሆንኩ ብቻ ሳይሆን መልአክ እንደሆንኩኝም ነው የሚሰማኝ። በግራና በቀኜ ያሉትን ክንፎቼን ፈልጌ ሳላበቃ፥ መልሼ ራሴን የማልጠብቀው ቦታ ላይ አገኘዋለሁ። እንዴ ቆይ እኔ መንፈሳዊ ሰው አይደለሁ እንዴ? እንዴት ነው እንዲህ አይነት እግዚአብሄር የማይከብርበት  ሀሳብ አይምሮዬ ውስጥ ሊመጣ የሚችለው? እንዴትስ ነው በገዛ ስጋዬ ምኞት ልሳብ የምችለው? እያልኩ አንዴ ሳወጣ አንዴ ሳወርድ አስቤ አስቤ ቆይቼ ቆይቼ፥ ከተማርኩ በኋላ፥ ምንም አይነት የመልአክ ዘር ውስጤ አለመኖሩን፥ ይልቁንም የሰው ልጅ በእርግማን ከወደቀ በኋላ፥ በስጋው ተሸክሞ ከሚዞረው የስጋ ምኞት ጋር በመጋደል ለመኖር እንደተጠራሁ ገባኝ። ዛሬ በውስጤ የሞላውን ሀሳብ ሳካፍላችሁ፣ ይሄ ነው የማልለው ደስታ ይሰማኛል። ለምን መሰላችሁ? በህይወቴ፣ በመውጣትና በመውረድ፥ በመሳትና በመመለስ፥ በእግዚአብሄር የፀጋው ብርታት ተደግፌ፥ ባለማስተዋሌ ውስጥ ባሳለፈው እውቀቱ ተደንቄ የተማርኩት፣ አሁንም እየተማርኩ ያለሁትና እያንዳንዱን የትግል ቀናቶቼን ለማሸነፍ ብርታት የሆነኝን ነገር ስለማካፍላችሁ ነው።  በዚች በተሰጠን አጭር እድሜ ውስጥ ስንኖር፥ ከተጠራንባቸው ዋና አላማዎች ውስጥ አንዱ ከሀጢያት ጋር እየታገልን በመኖር፣ በክርስቶስ የተሰጠንን የአሸናፊነት ህይወት ለመጠበቅ ነው። ሁላችንም መጀመሪያ ስጋውያን ነበርን:: ቀጥሎ ነው መንፈሳውያን የሆነው። በፊት፥ የገዛ ምኞታችን  የሚመራን፥ በስጋችን ፈቃድና ምኞት እንኖር የነበርን የገዛ ስጋችን ባሪያዎች ነበርን። አሁን ግን የሚመራን የስጋችን ምኞት አይደለም:: በውስጣችን የሚኖረው የእግዚአብሄር መንፈስ ነው።  መፅሀፍ ቅዱስ ሲናገር፣ በምድር ላይ እግዚአብሄርን አስከብረው ያለፉ፥ የዚህን ምድር ቆይታቸውን በአላማ  የኖሩ፥ ከህይወታቸው ብዙ የተማርንባቸው ሰዎች አሉ። እነ ጳውሎስን፥ እነ ሙሴን፥ እነ ዳዊትን፥ እነ አብርሀምንና ብዙዎችን በምሳሌነት መጥቀስ እንችላለን። በአንፃሩ ደግሞ ከእግዚአብሄር ጋር የጀመሩ ነገር ግን አላማቸው መንገድ ላይ የተሰናከለባቸውና ሩጫቸውን ያልጨረሱ ሰዎችን እነ ሳኦልን፥ ሳምሶንን፥ አብዛኛውን የእስራኤልን ህዝብ የምድረበዳ ጉዞ ጨምሮ ብዙዎችን በምሳሌነት ማንሳን እንችላለን። በጣም የሚገርመው ነገር፥ የተፈጠሩበትን ትልቅ አላማና እግዚአብሄር በህይወታቸው ላይ ያለውን ዘላለማዊ ሀሳብ በሚጨርሱና በማይጨርሱ ሰዎች መካከል ያለው ልዩነት ለስጋቸው ምኞት የሰጡት ምላሽ ነው። አላማቸውን በትክክል ያልጨረሱትን ሰዎች ህይወት ስታጠኑ ያሰናከላቸውና መንገድ ላይ ያስቀራቸው ለገዛ ስጋቸው ምኞት የሰጡት ምላሽ ነበር። ልማድ ሆኖብን ሰይጣን ላይ እናሳብባለን እንጂ፣ እኛ ከእግዚአብሄር ጋር በትክክል የምንሄድ ከሆንን በእግዚአብሄር መለኮታዊ ጥበቃ ስር ከመሆናችን የተነሳ ያለ እግዚአብሄር ፈቃድ ሰይጣን በህይወታችን ላይ ምንም የማድረግ መብት የለውም። ይልቁንም፣ ሰይጣን እራሱ እኛን ከእግዚአብርሄ ሀሳብ ለማጉደል እንደ መሳሪያ አድርጎ የሚጠቀመው የገዛ ስጋችንን ምኞት ነው። የእስራኤልን ህዝብ ታሪክ በጥልቀት ስታጠኑ፥ ጠላቶቻቸው ምንም ቢበዙና ሀይለኞች ቢሆኑ እንኳን፥ እንድም ጊዜ ያለ እግዚአብሄር ፈቃድ መጥተው ምንም ጉዳት አድርሰውባቸው አያውቁም። ህዝቡ እራሳቸው ግን በስጋቸው ምኞት ሲሰናከሉና በልዩ ልዩ ሀጢያት እግዚአብሄርን ሲፈታተኑት፥ መለኮታዊ ጥበቃውን ከላያቸው በማንሳት፣ ለጠላቶቻቸው አሳልፎ ይሰጣቸው ነበር። አንድ ጊዜ የሞአብ ንጉስ የሆነው ባላቅ ከአምላካቸው ጥበቃና አብሮነት የተነሳ  የእስራኤልን ህዝብ ቢፈራቸው፣ በልአምን በመጥራት ህዝቡን እንዲረግምለት ጠየቀው። በልአምም፣ እግዚአብሄር የባረከውን ህዝብ በፍፁም አልረግምም በማለት የእስራኤልን ህዝብ ሲባርክ፣ ባላቅ እስራኤልን ለመጉዳት የሞከረው ሙከራ አልሳካ ቢለው፣ አንድ ዘዴ አገኘ። የሀገሩ ሴቶች ከእስራኤል ወንዶች ጋር በሀጢያት እግዚአብሄርን እንዲበድሉ የተንኮል ሁኔታን በማመቻቸት ከአምላካቸው ጋር አጣላቸው። እግዚአብሄርም በእስራኤል ልጆች ላይ በመቆጣት፣ በፅኑ ቅጣት ቀጣቸው። በጣም መፍራት ያለብን በሀጢያት እግዚአብሄርን መበደል እንጂ ሰይጣን የሚያመጣብንን ክፉ ነገር አይደለም።    ሀጢያት ማለት የሰው ልጅ ከእግዚአብሄር ቃል ውጪ የሚያደርገውና እግዚአብሄር የሚፀየፈው ነገር ማለት ነው። ሀጢያት ምንጊዜም ከሀጢያት አይጀምርም። የሚጀምረው ከሀሳብ ነው። ሰይጣንም ይሄንን በደምብ ስለሚያውቅ ያለመታከት ለመቆጣጠር የሚፈልገው ማንነታችን ቢኖር አይምሮአችንን ነው። የሰይጣን ዋነኛ የጦር መሳሪያው ሀሳብ ነው። ሀሳብን በሰዎች አይምሮ ውስጥ አስቀምጦ ይሄዳል። ምንም አይነት የሀጢያት ሀሳብ አይምሮአችን ውስጥ መጣ ማለት ግን ሀጢያተኞች ነን ማለት አይደለም። የክፋት ሀሳብ ውስጣችን ስለመጣ ክፉዎች ነን ማለት አይደለም። ሰይጣን እንኳን እኛ ጋር፣ ኢየሱስም ጋር ሀሳብን ይዞ ሄዷል። ምንም መንፈሳዊ ሰዎች ብንሆን፥ እንዴት እንዲህ አይነት የሀጢያት ሀሳብ ልባችሁ  ውስጥ ይመጣል ብሎ እግዚአብሄር  አያዝንም። ማየት የሚፈልገው ግን አይምሮአችን ውስጥ ለሚመጡት የሀጢያት ሀሳቦች የምንሰጣቸውን ምላሾች ነው። በእነዚህ ምላሾቻችን ሊደሰትም ሊያዝንም ይችላል።  “በመንፈስ ተመላለሱ የስጋንም ምኞት ከቶ አትፈፅሙ” (ገላትያ 5፡16)  በፊት በስጋችን ፈቃድ ብቻ የምንመራ የስጋችን ባሪያዎች ነበርን። አሁን ግን ክርስቶስ ከሰጠን ስልጣኖች አንዱ፣ የገዛ ስጋችንን ውስጣችን ላለው ለእግአብሄር መንፈስ በማስገዛት በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ እንድንመላለስ ነው። ይሄ ነው የተሰጠን የአሸናፊነት ህይወት። ይሄንን የአሸናፊነት ህይወት ለመለማመድ የሚረዱንን ሶስት ዋና ዋና ተግባራዊ መንገዶች እስኪ እንመልከት። መሸሽ፡ “መሸሽ ልክ እንደ አሸናፊነት ይቆጠራል” የሚለው የሀገሬ ምሳሌያዊ አነጋገር ትዝ አለኝ። አያችሁ፣ በዚህ አለም ሂሳብ ሰው እሸነፈ ተብሎ የሚቆጠረው ፊት ለፊት ተጋጥሞ የእሱን ብርታት የበላይነት ሲያሳይ ነው። በእግዚአብሄር አለም ውስጥ ግን ሰው አሸነፈ የሚባለው የእግዚአብሄርን ሀሳብና ፈቃድ በህይወቱ ሲፈፅም ነው። ለምሳሌ የክርስቶስን የመስቀል ሞት ብታስቡት፥ ያሰቃዩትና የሰቀሉት ሰዎች በሙሉ እንደተሸነፈ ነበር የቆጠሩት። የክርስቶስ የማሸነፍ ሂሳብ ግን፥ ከመስቀል ወርዶ ራሱን ማዳንና ያሰቃዩትን ሰዎች ልካቸውን ማስገባት አልነበረም። እንደዛ ያላደረገው ስለማይችል ሳይሆን ለእርሱ አሸናፊነት ማለት ወደ ምድር የመጣበትን ዋና አላማ በመፈፀም ዓለምን ሁሉ በመስቀል ሞቱ ውስጥ ህይወትንና ትንሳኤን መስጠት ነበር። ስለዚህ ስለ ሀጢያት ስናወራ የአሸናፊነታችን የመጀመሪያው ተግባር በምኞት ፈተና ውስጥ ሊጥሉን ከሚችሉት ነገሮች በሙሉ ራሳችንን ማራቅ ነው። ለራሳችን እውነተኞች መሆን ከቻልን ወደ ሀጢያት ጎዳና የሞወስዱንን መንገዶች እናውቃቸዋለን። መንቃት ያለብን ተጠላልፈን ከወደቅን በኋላ አይደለም። አያችሁ እኛ ክርስቲያኖች እኮ በማስተዋል ለመኖር የተጠራን፥ የጥብና የማስተዋል መንፈስ የተሰጠን ህዝቦች ነን። በውስጣችን ያለው መንፈስ፣ አስተዋይ የሚያደርግ የማስተዋል መንፈስ ነው። ይሄ ማስተዋል ደግሞ፣ መጀመፊያ ላይ ቆሞ መጨረሻውን ማየት ይችላል። አንድ ሰው በሚያዳልጥ ጉድጓድ አጠገብ ቆሞ “እግዚአብሄር አምላኬ ሆይ፣ እባክህ እዚህ ጉድጐድ ውስጥ እንዳልወድቅ ጠብቀኝ” ብሎ አይፀልይም። ይልቁንም እንደሚያዳልጠው ስለሚያውቅና የራሱን ደህንነት ለመጠበቅ፣ ከጉድጐዱ ለመራቅና ለመሸሽ የተቻለውን ያደርጋል እንጂ። በእግዚአብሄር አለም ውስጥ ከሀጢያትና ወደዛ ከሚመሩን ጎዳናዎች መራቅ፣ የመጀመፊያው የአሸናፊነት መንገድ ነው። ይሄ የድላችን በር ነው። የተፈጠርንበትን ዓላማ ለማሳካት የጀመርነው ፅኑ የሆነ ውሳኔ ነው። በፍፁም አንፀፀትበትም። የህይወትና የሰላም መንገድ ነው። መጨረሻው ደግሞ ክብር ነው። ታዲያ ከምን ከምን እንሸሻለን ካልን፥ ለራሳችን እውነተኞች በመሆን ደጋግመን በሀጢያት የምንጠላለፍባቸውን መንገዶች እናስብ። የእነሱን ነገሮች መጀመፊያ አስተውለን በመመልከት፣ ከእነዚህ ነገሮች ለመራቅ እንሞክር። ጏደኞች ሊሆኑ ይችላሉ። የምናያቸው የቴሌሽን ቻናሎች ወይንም የማህበራዊ ገፆቻችን ሊሆኑ ይችላሉ። “ወዳጆች ሆይ ነፍስን ከሚዋጋ ስጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መፃተኞች እንደመሆናችሁ እለምናችህለሁ” (1ኛ ጴጥሮስ 2፡11) በቃሉ መሞላት፡  በክፉዎች ምክር አልሄድም፥ በዋዘኞች ወንበር አልቀመጥም፥ በሀጢያተኞች መንገድ ደግሞ አልቆምም፥ ብለን የሀጢያት መንገዶችን ሁሉ ከህይወታችን ካስወገድን በኋላ፣ በእግዚአብሄር ህግ መደሰት፥ ህጉን ደግሞ በቀንና በሌሊት ማሰላሰል ያስፈልገናል። እስኪ ቃሉን ስለማሰብና ስለማሰላሰል ጥቂት እንነጋገር። የጦርነቱ ዋነኛ ስፍራ እንግዲህ አይምሮአችን እንደሆነ ቀደም ብለን ተነጋግረናል። ጨዋታው አይምሮአችንን በሙሉ በመቆጣጠር፣ በፍቃዱ ስር ማስገዛት ነው። አይምሮአችን በእግዚአብሄር ቃል እውነት ሙሉ ከሆነ ግን፥ ሰይጣን የሚያመጣው ሀሳብ ቦታ ሊያገኝ አይችልም። የምናሰላስለው የእግአዚብሄርን ቃል ከሆነ፥ ፈቃዳችን በሙሉ የሚገዛው ለምናሰላስለው ቃል ነው። ብዙ ጊዜ መፅሀፍ ቅዱስን ስለማንበብ እንጂ ስለማሰላሰል ትኩረት ስንሰጠው አይታይም። ጠዋት ላይ ተነስተን አንድ ቃል አነበብን ከዚያም ወደ ጉዳያችን እንገባና ሀሳቦቻችን በተለያዩ ነገሮች ሲበታተኑ፣ ያነበብነው ቃል ምንም  ትዝ ሳይለን ይውላል። እስኪ ማታ ማታ ብቻችሁን ሁኑና፣ 5 ደቂቃ ውሰዳችሁ ቀናችሁ እንዴት እንደነበረ በማስተዋል ለማሰብ ሞክሩ። ከመደበኛ ስራችሁና እንቅስቃሴያችሁ በላይ፣ አይምሮአችሁን ቢዚ በማድረግ፣ የእግዚአብሄርን ቃል እንዳታስቡና እንዳታሰላስሉ ያደረጋችሁ ነገር ብዙ ነው። እነ ሶሻል ሚዲያ፥ ዩ ቱብ፥ በጣም አስፈላጊ ያልሆኑ

Article

ትምህርት ቤት

Home Blog Book About Contact X Order Book ትምህርት ቤት Audio አንድ የቅርብ ጓደኛዬ፥ በህክምና ፊልድ ውስጥ የመሆንና በዚህ የስራ ዘርፍ የማገልገል ከፍተኛ የሆነ ፍላጎት ስለነበራት፥ በነርሲንግ ፕሮግራም ውስጥ ገብታ ለሁለት አመታቶች በትጋት ትምህርትዋን ትከታተል ነበር። የቅርብ ወዳጄ በመሆንዋ፥ በተገናኘንባቸው ጊዜያቶች ሁሉ የትምህርትዋን ሁኔታ ታጫውተኝ ነበር። እዚህ የትምህርት ፕሮግራም ውስጥ ከመግባቷ በፊት፥ ስለ ህክምናም ሆነ ስለ ተያያዥ ነገሮች ምንም አይነት እውቀት አልነበራትም። ይሄ የጀመረችው የህክምና ትምህርት ታዲያ ለሁለት የሚከፈል ነው። ግማሹን ጊዜ ቁጭ ብለው ከአስተማሪያቸው እንዲማሩ ከተደረጉ በኋላ፥ የቀረውን ጊዜ ደግሞ የተማሩትን በተግባር ማዋል እንዲማሩና የበለጠ ልምድ እንዲኖራቸው በየሆስቲታሎች ውስጥ በመሄድ የተማሩትን እንዲለማመዱ ይደረጋሉ። ይሄን የትምህርት አካሄድ ሳየው፥ ከእግዚአብሄር ጋር ያለንን የመንፈሳዊ ህይወት ያሳስበኛል። በየቤተክስቲያኖቻችን ከምንማራቸው ትምህርቶች እንዲሁም መፅሀፍ ቅዱስን አንብበን ከተረዳናቸው ነገሮች በተጨማሪ፥ እግዚአብሄር በህይወታችን አካሄዶች ውስጥ እራሱን በመግለጥ እንድናውቀው ይፈልጋል።  የመዳንን እውቀት ካገኘንበትና ኢየሱስን የህይወታችን አዳኝና ጌታ አድርገን ዳግም ከተወለድንበት ጊዜ ጀምሮ፥ ልክ አንድ የተወለደ ህፃን እድገቱ በጊዜ ውስጥ እንደሚታይ ሁሉ፥ ከእኛም ህይወት እግዚአብሄር የሚጠብቀው ዋነኛ ነገር እድገትን ነው። እግዚአብሄር እሱን በማወቅና በማመን እንድናድግ ይፈልጋል። እምነታችን ለዘላለም ህይወት ብቻ ከመሆን አልፎና አድጎ በሌሎች የህይወታችን ጉዳዮችም እንድናምነው ይፈልጋል። እሱን በማወቅ እንድናድግና ባህሪያቶቹን ሁሉ እንድንማር፥ እንድንማር ብቻም ሳይሆን ደግሞ፥ የራሱን ባህሪያቶች እኛ ውስጥ ማየት ይፈልጋል። ስለ እርሱ ያለን እውቀት እድጎና ለራሳችን ከማወቅ አልፈን፥ ለሌሎች ስለ እርሱ እንድንናገርና እንድናወራ ይፈልጋል።  ታዲያ እምነታችንን ሊያሳድግና ሊያስተምረን እንዲሁም ለእርሱ ያለን እውቀት እንዲያድግ ሲፈልግ፥ የሚወስደን የህይወት መንገዶች አሉት። የምንማርበትን መንገድ መራጮቹ ደግሞ እኛ አይደለንም። መንገዱን የሚመርጥልን እግዚአብሄር እራሱ ነው። እንድንማር የወደደውን ነገር በምን መንገድ ውስጥ ብናልፍ እንደምንማረው ያውቃል። በየትኛው መንገድ ውስጥ ህይወታችንን ቢያሳልፈው ልባችንን እንደሚያገኘው ያውቃል። “እግዚአብሄርን የሚፈራ ሰው ማነው? በሚመርጠው መንገድ ያስተምረዋል” (መዝሙረ ዳዊት 25፡12) ሁላችንም ብንሆን፥ ዛሬ ላይ ከትላንትና ይልቅ ስለ እግዚአብሄር የተሻለ እውቀት አለን። ቁጭ ብለን በትምህርትና በስብከት ከምንማራቸው ትምህርቶች ጎን ለጎን፥  በህይወቶቻችን መንገዶች ደግሞ የምንማራቸው ትምህርቶች አሉ። እስኪ ህይወታችንን ዞር ብለን ያለፍንባቸውን ከባባድ ጊዜያቶች እናስባቸው። ለዛ ጊዜ በጣም ከባድና ፈታኝ ጊዜያቶች ቢሆኑም እንኳን፥ ዛሬ ላይ ግን የቆምንባቸው እውቀቶቻችን ናቸው። ዛሬ ላይ፥ እግዚአብሄርን የበለጠ እንድናምነው ያደረጉን እምነቶቻችን ናቸው። እግዚአብሄር አጠገባችን ይሁን እንጂ፥ ምንም ነገር እንደማንሆን ያወቅንባቸው ድፍረቶቻችን ናቸው።  እኛ ክርስቲያኖች ሳንነጋገር የተስማማንበት አንድ ነገር ምንድነው? በህይወታችን ውስጥ የሚመጡ ጥሩ ጥሩ ነገሮች ሁሉ ከእግዚአብሄር፥ ከባድ ከባድ መንገዶች ሁሉ ደግሞ ከሰይጣን ነው የሚል የተሳሳተ እምነት አለን። በደምብ አስተውለን ካየነው ግን፥ ከጠላት የሚቀርቡ መልካምና ያማሩ እንዲሁም ምቾት ያለባቸው የሚመስሉ የህይወት መንገዶች እንዳሉ ሁሉ፥ ከባድና ፈታኝ የሆኑ እግዚአብሄር እንድናልፍባቸው የሚፈቅዳቸው መንገዶች ህይወታችን ላይ አሉ። እኛ አካሄዳችንን ከእግዚአብሄር ጋር እናስተካክል እንጂ፥ የትኛውም ከባድ ነገር ያለ ምክኒያት ወደ ህይወታችን አይመጣም። ሰይጣንም ቢሆን እግዚአብሄር ሳይፈቅድለት እኛ ላይ ምንም የማድረግ መብት የለውም። ታዲያ እነዚህ እግዚአብሄር እንማር ዘንድ የሚመርጥልን የህይወት መንገዶች፥ አብዛኛውን ጊዜ ለስጋችን ወይንም ለተፈጥሮ ማንነታችን አስደሳችና ምቹ አይደሉም። አንዳንዶቹ እንዲያውም ለጊዜው በጣም የሚያሙና እግዚአብሄር እንደሚያየን እስክንጠራጠር ሊያደርሱን የሚችሉ ከባባድ መንገዶች ናቸው። ታዲያ እግዚአብሄር እንድንማር የወደደውን እንድንማር ዝም የሚለው፥ ስለማያየን ወይንም ስለእኛ ግድ ስለማይለው ሳይሆን በህይወታችን ላይ ላለው ዘላለማዊ ሀሳብ፥ የግድ ልንማረው የሚያስፈልገን ነገር በመሆኑና፥ እግዚአብሄር ለአላማው ጨካኝ አምላክ ስለሆነ ነው። ምንም ከባድ ነገሮች ውስጥ ሊያሳልፈን ቢወድም ግን፥ ከማለፋችን በፊት በዚህ መንገድ ውስጥ ለማለፍ ያለንን አቅም ሳይመዝን፥ በየትኛውም መንገድ ውስጥ እናልፍ ዘንድ አይፈቅድም። ምክኒያቱ ደግሞ፥ የመንገዱ አላማ እኛን ማሰቃየት ሳይሆን ማስተማር ስለሆነ ነው። እግዚአብሄር አዋቂ፥ ስራውንም ደግሞ የሚመዝን አምላክ በመሆኑ፥ ህይወታችን ላይ የሚያደርገውን ምንም አይነት ነገር ሳይመዝን አያደርገውም። “ካለፉ ይለፉበት፥ ካላለፉ ደግሞ እንደሚሆኑ ይሁኑ” ብሎ ለራሳችን በፍፁም አይተወንም። ይልቁንም፥ በድካማችን ውስጥ የራሱን ሀይልና ብርታት እያሳለፈ፥ መሄድ ሲያቅተንና ሲደክመን ደግሞ በጀርባው እየተሸከመ፥ በምናልፍበት ሁሉ ውስጥ አብሮ በእኛ ፍጥነት ከጎናችን ይጉዋዛል። በጣም ፈጣንና ሀያል ስለሆነ፥ ቀድሞንና ጥሎን አይሄድም። ህመማችን ሁሉ እሱንም ያመዋል። የነገሩ ክብደት እሱንም ልክ እንደ እኛ ይሰማዋል፥ ይገባዋል። በሚያሳልፈን መንገዶች ሁሉ ውስጥ ደግሞ ፀጋ የሚባል መሸፈኛ አለው። አንዳንድ ነገሮች ካለፋችሁበት በሁዋላ “እንዴት ግን በዚህ ነገር ውስጥ የማልፍበትን አቅም አገኘሁ?” ብላችሁ የምትደነቁባቸው ነገሮች የሉም? አንዳንዶቹ መንገዶች እንዲያውም ምንም ትላንት አልፋችሁ የወጣችሁባቸው መንገዶች ቢሆኑም እንክዋን “ትላትና በዚህ መንገድ ውስጥ የማለፍ ልምድ ስላገኘሁ፥ እንደገና አልፌ መውጣት እችላለሁ” ለማለት የማትደፍሩባቸው ከባባድ መንገዶች ናቸው። በእነዚያ ፈታኝ መንገዶች ውስጥ ያሳለፈን የፀጋው ብርታት ብቻ ነው። እግዚአብሄር ከባባድ በሚባሉ መንገዶች ውስጥ ሊያሳልፈን የሚወድበትን 3 ዋና ዋና ምክኒያቶች እስኪ እንመልከት።   1፥ የልጁን መልክ እንድንመስል፡ ዳግም ከተወለድን በሁዋላ፥ ህይወታችን የክርስቶስን መልክ ወደመምሰል ይለወጥ ዘንድ፥ እግዚአብሄር እንድናልፍባቸው የሚፈቅዳቸው መንገዶች አሉ። በነገራችን ላይ መፅሀፍ ቅዱስ “የልጁን መልክ” በማለት ስለ መልክ የሚያናገራቸው ነገሮች፥ በስጋችን ስላለው ስለ ፊታችን ወይንም ስለ ተፈጥሮ መልካችን የሚናገሩ አይደሉም። ስለ ባህሪ የሚናገሩ ናቸው። በመጀመሪያም እግዚአብሄር ሰውን በመልካችን እንፍጠር በማለት ሲናገር፥ ስለ ተፈጥሮ የፊት መልክ እየተናገረ አልነበረም። እንደዚያ ቢሆን ኖሮ ሁላችንም አንድ አይነት ፊትና መልክ ነበር የሚኖረን። እግዚአብሄር መንፈስ በመሆኑ፥ በመልካችን እንፍጠር ሲል፥ በመንፈስ ውስጥ ስለምንካፈለው ባህሪ እንጂ ስለ ስጋችን መልክ እየተናገረ አልነበረም።  “እግዚአብሄርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ። በእግዚአብሄር መልክ ፈጠረ። ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው” (ዘፍ 1፡27) እግዚአብሄር ወንድንም ሴትንም ሲፈጥራቸው፥ የራሱን ባህሪይ በውስጣቸው አድርጎ ነበር የፈጠራቸው። ሰይጣን በተንኮሉ ሄዋንን በማሳት፥ የሰው ልጆችን ከህይወት ብቻ ሳይሆን፥ ያጎደለው መጀመሪያ ከተፈጠርንበት ከእግዚአብሄር መልክም ጭምር ነበር። ታዲያ ክርስቶስ እኛን የሰው ልጆችን ከአባቱ ጋር ለማስታረቅ ወደ ምድር ሲመጣ፥ አላማው ህይወትን መስጠት ብቻ ሳይሆን፥ በሀጢያት ምክኒያት ወዳጣነው ወደ ራሱ መልክ መመለስም ነበር። የክርስቶስን መልክ ወደ መምሰል መለወጣችን ታዲያ፥ ልክ እንደ መዳናችን በአንድ ቀን የሚከሰት ነገር አይደለም። በሂደት ውስጥ የሚከናወን ስርአት ነው። እግዚአብሄር እኛን ወደራሱ መልክ ለመለወጥ የሚጠቀምባቸው የህይወት መንገዶች አሉት። ለምሳሌ፥ ለመውደድ ከሚያስቸግር ሰው ጋር ካልኖርን፥ የሚወዱንን ብቻ እየወደድን እንኖራለን እንጂ፥ እውነተኛውን የክርስቶስን ፍቅር ልንማረው አንችልም። ሰው ካልበደለን፥ ይቅር ማለትን መለማመድ አንችልም። እግዚአብሄርን ማመን በሚያስፈልጉን ነገሮች ውስጥ ህይወታችን ካላለፈ፥ እምነትን መማር አንችልም። ትእግስትን በሚጠይቁ የህይወት መንገዶች ውስጥ ካላለፍን፥ ትእግስትን መለማመድ አንችልም።  2, እግዚአብሄርን የበለጠ እንድናውቀውና የእርሱን ባህሪያቶች እንድንማር—-እግዚአብሄር ይሄ ነው ተብለን ከምንማራቸው ትምህርቶች በተጨማሪ፥ እግዚአብሄር በህይወታችን አካሄዶች እንድናውቀው ይፈልጋል። አባቶቻችንን በመምራት፥ በእያንዳንዱ የህይወታቸው ምእራፎች እራሱን ይገልጥላቸው የነበረውም ለዚሁ ነበር። “ለሙሴ መንገዱን አስታወቀ፥ ለእስራኤል ልጆችም አደራረጉን” (መዝሙረ ዳዊት 103፡7) የእስራኤል ልጆች እግዚአብሄርን ያወቁት በአደራረጉና በሰራላቸው ተአምራቶች ብቻ ነበር። ሙሴ ግን ከእግዚአብሄር ጋር በነበረው ጉዞ፥ የእግዚአብሄርን አካሄድ፥ መንገዱንና ባህሪያቶቹን የተማረና ያወቀ ሰው ነበረ። እግዚአብሄርን በአደራረጉና በሰራላቸው ተአምራቶች ብቻ የሚያውቁት ሰዎች አሉ። በአንፃሩ ደግሞ፥ መንገዱንና አካሄዱን እንዲሁም ማንነቱንና ባህሪያቶቹን የተማሩ ሰዎች ደግሞ አሉ። ለምሳሌ አንድን ሰው እግዚአብሄር ከአንድ በሽታ ቢፈውሰው፥ ሊማር የሚችለው የእግዚአብሄርን ፈዋሽነት ብቻ ነው። እግዚአብሄር ግን ያንን ሰው ለጥቂት ጊዜ በዛ ህመም ውስጥ እንዲቆይ በማድረግ እምነትን፥ ትእግስትን፥ ፅናትን፥ ከመሆንና ካለመሆን ጋር ያልተያያዘ እውነተኛ ምስጋናን ሊያስተምረው  ይችላል። እግዚአብሄርን በጣም ያወቅነው በምቾቶቻችን ውስጥ አይደለም። ከባድ ብለን በምንላቸው ጊዜያቶቻችን ውስጥ ነው። ከእግዚአብሄር ጋር የበለጠ የተጠጋጋነው፥ የሚገርሙ የፍቅር ጊዜያቶችን ከእርሱ ጋር ያሳለፍነውና ወደ ልቡ ሀሳብ የተጠጋነውም በእነዚህ ፈታኝ የህይወታችን ጊዜያቶች ነው።   3፥ ከፊት ለፊታችን ላዘጋጀልን ስራ ወይንም አገልግሎት እኛን ለማዘጋጀት—-ሁላችንም በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት ሆነን የተፈጠርነው፥ እግዚአብሄር አስቀድሞ  ያዘጋጀልንን አገልግሎት እንድናገለግል

Article

ትላንትና

Home Blog Book About Contact X Order Book ትላንትና Audio ብቻዬን ሆኜ ጊዜ ለማሳለፍ እድል በማገኝባቸው ጊዜያቶች፥  ደስ ከሚለኝ ነገሮች አንዱ፥ ወደ ኋላ ሄጄ ያለፈውን ታሪኬን ማሰብ ነው። ማሰብ ደስ ይለኛል። ዝም ብሎ ማሰብ። ገና ከመወለዴ ጀምሮ እናቴ ስለእኔ ከነገረችኝ ታሪኮች አንስቼ ልጅነቴን፥ እንዲሁም ህይወቴ ያለፈባቸውን መንገዶች በሙሉ አስባቸዋለሁ። ያደኩባቸውን ቦታዎች፥ ልጅነቴ ያለፈባቸውን መንገዶች በሙሉ ወደ ኋላ ሄጄ ሳስብ፥ በእግዚአብሄር ፍቅር እንዲሁም በእያንዳንዱ ወቅቶቼ ውስጥ በበዛው የእግዚአብሄር ጥበቃ እገረማለሁ። ባለማወቅ ወራቶቼ ውስጥ ደግሞ እየተገለጠ የመራኝን የእግዚአብሄርን እውቀት እያሰብኩ አደንቃለሁ። ህይወቴ ላይ ባለፉት ከባባድ ወቅቶች ውስጥ፣ እንዴት አርጎ እንደረዳኝ፣ እንዴት አጠገቤ እንደነበር፣ በራሴ ማለፍ የማልችላቸውን ወቅቶች ሁሉ እንዴት አርጎ እንዳሳለፈኝ፥ ዝርዝር ሁኔታውን እያሰብኩ አመሰግናለሁ። የህይወቴ መንገድ ቀያሽ እራሱ እግዚአብሄር፣ ህይወቴን በምን ውስጥ ቢያሳልፈው የበለጠ ወደ እሱ እንደምጠጋ የሚያውቅ እሱ። በምን ውስጥ ቢያሳልፈኝ እንድማር የሚፈልጋቸውን ነገሮች እንደምማር የሚያውቅ እሱ፥ ለጊዜው ከባድ የመሰሉትን መንገዶች በሙሉ ሰብስቦ፥ ዛሬ ላይ ለሆንኩት ማንነቶቼ መሰሪያ የተጠቀመባቸውን የጥበብ አምላክ እግዚአብሄርን እባርካለሁ። ትላንትናዬን ማሰብ ደስ ይለኛል። ልቤን በምስጋና እየሞላ ከፊት ለፊቴ ያሉትን ዘመናቶች የማልፍበትን አቅም የማገኝበት እምነት ጋር ያደርሰኛል። ነፍሴ ሆይ እኔ የምልሽ፥ እግዚአብሄር ከፈጠረሽ ጊዜ አንስቶ እስከዛሬ ድረስ፥ እነዚህን ሁሉ አመታቶች ከረዳሽ “ከዚህ በኋላ እኔ ልረዳሽ ስለማልችል ራስሽን ቻይ” ብሎ አምላክ ሀሳቡን የለወጠ ይመስል ስጋት የሚገባሽ ግን ለምንድነው? እሱማ እስከ ሽበት እስከ ሽምግልና ድረስ ላይተውሽ፣ ላይረሳሽና ላይጥልሽ ከራሱ ጋር ተማምሎ ከጨረሰ በኋላ እሱም አልበቃ ቢለው፥ በእጆቹ መዳፍ ላይ እንደቀረጸሽ፥  እጆቹን ባየ ቁጥር ስላንቺ እንደሚያስብ፣ ከእርሱ ጋር የጀመርሽው የፍቅር ኪዳን፥ ለዘለአለም አንቺን የመሸከም አቅም እንዳለው አታውቂም? “ “ነፍሴ ሆይ እግዚአብሄርን አመስግኚ፣ በህይወቴ እግዚአብሄርን አመሰግናለሁ፥ በምኖርበት ዘመን ሁሉ ለአምላኬ እዘምራለሁ።” (መዝሙረ ዳዊት 146:1) ይሄ ወደ ኋላ ሄዶ ህይወቴን የማሰብ ልምዴን እንድቀጥልበት ከሚያበረታታኝ ነገሮች አንዱ፥ በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ ከተጻፈው የእስራኤል ህዝቦች ታሪክ የተማርኩት አንድ ትልቅ ትምህርት ነው። የእስራኤል ህዝቦች፥ በእግዚአብሄር የተወደዱ፣ በእግዚአብሄር የተመረጡ፣ ኪዳን ያላቸው ህዝቦች ናቸው። ከእግዚአብሄር ጋር በጣም ብዙ ታሪክ ያላቸው ህዝቦች ናቸው። መቼም የእስራኤልን ህዝቦች ታሪክ በደምብ አምብበነው ከሆነ፥ እግዚአብሄር በዘመናት ውስጥ ለእነርሱ  ያሳየውን ፍቅር ሰማይና ምድር እንኳን ሊክዱት አይችሉም። እግዚአብሄር ለእስራኤል ህዝብ ማነው? ብለን ከጠየቅን፣ እግዚአብሄር ለእስራኤል ህዝብ፣ በእነሱና በጠላቶቻቸው መካከል በጽድቅ የፈረደላቸው የጽድቅ ፈራጃቸው ነው። ከፈርኦን ጋር ጦርነት የከፈተበት፣ እስራኤል የበኩር ልጄ ነው፥ ልጄን ልቀቅ ብሎ አባትነቱን ያሳየበት አባታቸው ነው። ምድሪቱን አንበጣ በአንበጣ፣ ተምች በተምች፣ ባህሩን ውሀውን ሁሉ ደም በደም ያደረገበት፥ በበቀልና በቁጣ የወጣበት እግዚአብሄር ለእስራኤል ህዝቦች የጽድቅ ፈራጃቸው ነው። በጠላቶቻቸው ሰፈር ጽኑ ጨለማን አርጎ፣ በእነሱ ሰፈር የደመቀ ብርሀን የሆነላቸው ብርሀናቸው ነው። እግዚአብሄር ለእስራኤል ህዝብ በአንድ ሌሊት የግብጽን በኩር በሙሉ በሞት የቀጣበት፣ የጠላቶቻቸውን መንደር በለቅሶ የሞላበት፣ ለእነሱ ደግሞ ሞገስን የሰጠበት ሞገስና ውበታቸው ነው። የኤርትራንስ ተአምራት ብናነሳ፣ ስሙ የተጠራበትን ህዝብ በደረቅ ምድር ተጠንቅቆ ካሳለፈ በኋላ አይደል እንዴ፥ በግብጽ ምድር የጨፈጨፋቸው ሳያንስ፥ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ብሎ ጠላቶቻቸውን በሙሉ በኤርትራ ባህር ውስጥ የጣላቸው! ከነ ሰረገሎቻቸው እኮ ነው በውሀ በመዋጥ ለእስራኤል የማዳን ብርታትና ሀይሉን ያሳየው። “እግዚአብሄር ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሄር ነው” የሚለውን ከዚያ በፊት የሰው ልጅ ዘምሮት የማያውቀውን አዲስ ዝማሬ ከእነርሱ ውስጥ ያወጣ፥ እግዚአብሄር እኮ የእስራኤል ዝማሬ ነው። ከፊታቸው ደግሞ እየወጣ ቀን ቀን በደመና፥ ሌሊት ሌሊት ደግሞ በእሳት አምድ ሆኖ ብቻውን የመራቸው አምላካቸው እግዚአብሄር ነው። በንስር ክንፍ መሸከሙ ሳያስን፣ ሊሽርና ሊለውጠው የማይችለውን ኪዳን የገባላቸው ጽኑ ተስፋቸው ነው። እግዚአብሄር ለእስራኤል፣ ዮርዳኖስን የከፈለ፣ ኢያሪኮን የሚያክል የከተማ ግብም በድምጻቸው ውስጥ አልፎ ያፈረሰ ሀይላቸው ነው። ህግና ስርአትን የተማሩበት፥ እግዚአብሄር አምላክ መሆኑን ያወቁበት ስርአታቸው ነው።  እግዚአብሄር ለእስራኤል ህዝብ ያላሳየው መልካምነት ባይኖርም፥ አብዛኛው ህዝብ ግን የተገባለትን የተስፋ ምድር ሳያይ በምድረበዳ ላይ መቅረቱ ሁላችንንም የሚያሳዝነን ነገር ነው። መቼም ይሄ ህዝብ ከነአንን አለመውረሱ ቢያሳዝነንም፥ ሁልጊዜ ማወቅ ያለብን፥ እግዚአብሄር ከእርሱ የሚጠበቀውን ሁሉ ሳያጓድል ማድረጉን ነው። እንዲያውም የእስራኤልን ህዝብ ስናስብ ቶሎ ብለን ማሰብ ያለብን፥ የእግዚአብሄርን ታማኝነት፥ የእግዚአብሄርን ቃሉን ጠባቂነት ነው። እግዚአብሄር ለእስራኤል ቤት ከተናገረው መልካም ነገር ሁሉ ተፈጸመ እንጂ አንድም አልቀረም ብሎ፥ ቃሉ እራሱ የእግዚአብሄርን ታማኝነት አረጋግጧል። ህዝቡን ልክ እንደተናገረው ወደ ተስፋይቱ ምድር አስገብቷል። የገቡት ግን፣ በእግዚአብሄር ታማኝነት ውስጥ የታሰቡት ግን፥ እንደ እግዚአብሄር ሀሳብ የሄዱት ሰዎች ብቻ ናቸው። በጣም ብዙዎች የተስፋው ምድር ጋር ሳይደርሱ በምድረበዳ ቀርተዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በእግዚአብሄር ቁጣ መንገድ ላይ አልቀዋል። ዛሬ የምናየው እግዚአብሄር የተስፋይቱን ምድር አያዩም ብሎ እስኪምል ድረስ ከልቡ ያዘነበትንና የተቆጣበትን አንድ አሳዛኝ ታሪክ ነው። የእስራኤል ህዝብ አጠቃላይ የምድረበዳ ጉዞ አርባ አመት ቢሆንም፥ ከግብጽ ተነስቶ ከነአን ለመድረስ አይደለም አርባ አመት የፈጀባቸው። ከኮሬብ ተነስቶ የተስፋይቱ ምድር ጫፍ ለመድረስ መንገዱ የሚፈጀው አስራ አንድ ቀናቶችን ብቻ ነው። ህዝቡ ታዲያ ይሄንን መንገድ ተጉዞ የከነአን ምድር ጫፍ የሆነችው ቃዴስ በርኔ ጋር ደርሶ እንደነበር መጽሀፍ ቅዱስ በዘዳግም ምእራፍ 1 ላይ ሙሴ ጽፎልናል። ታዲያ ግን የከነአን ምድር ወይንም የተስፋይቱ ምድር ድንበር ላይ ሲደርሱ፥ የተፈጠረ በዘሁልቁ ምእራፍ 14 ላይ የምናገኘው ብዙዎቻችን የምናውቀው አንድ በጣም አሳዛኝ ታሪክ አለ። በዚህ ታሪክ ምክኒያት፥ እግዚአብሄር በጣም በማዘኑና በመቆጣቱ፥ ሊገቡ ከነበሩበት ምድር ተመልሰው ወደ ኋላ በመዞር፥ ለአርባ አመታቶች ምድረበዳ ላይ እንደተንከራተቱ፥ እንዲሁም ለብዙ ዘመናት ሴይር የተባለን አንድ ተራራ ሲዞሩ እንደኖሩ እናነባለን። ዘሁልቁ ምእራፍ 14 ላይ፥ አርባ አመታቶች ሙሉ ምድረበዳ ላይ ለመንከራተታቸው ምክኒያት ስለሆነው ታሪክ እንዲህ ሲል ይነግረናል። ሊገቡባት የነበረውን ምድር እንዲሰልሉ፥ ከአስራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ የተመረጡ አስራ ሁለት ሰዎች ወደ ተስፋይቱ ምድር ተልከው ነበረ። እነዚህ አስራ ሁለት ሰዎች፥ የተላኩበትን ምድር ለአርባ ቀናቶች ሰልለው ወደ ህዝቡ ከተመለሱ በኋላ፥ ሁለት የተለያየ መረጃዎችን አቅርበው ነበር።  ከአስራ ሁለቱ መካከል አስሮቹ፥ “ምድሪቱ የሚኖሩባትን ሰዎች የምትበላ ናት። ከነአን ውስጥ የሚኖሩት ሰዎች ደግሞ ሃያላንና ጽኑዎች ናቸው። በሀይል ከእኛ ስለሚበረቱ ወደዚህ ህዝብ መውጣት አንችልም። ሰዎቹ ረጃጅም ናቸው። እኛ ደግሞ በአይናችን ግምት በፊታቸው እንደ አንበጣዎች ነበርን” በማለት ሲናገሩ፥ ከተላኩት ሰዎች መካከል ሁለቱ ኢያሱና ካሌብ ደግሞ “የሰለልናት ምድር እጅግ መልካም ምድር ናት። እግዚአብሄር ወተትና ማር ወደምታፈሰው ወደዚህች ምድር ያስገባናል፥ ምድሪቱንም ይሰጠናል። የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፥ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ነው። እንደ እንጀራ ይሆኑልናል” ብለው ከአስሩ ለየት ያለ መረጃ አቅርበዋል። እነዚህ ሁለት ሰዎች በከነአን ምድር ውስጥ ያሉትን ሰዎች አስፈሪነት አይተዋል:: ነገር ግን የትኛውም አስፈሪ ነገር፥ እግዚአብሄር የተናገረውን ቃል ከመፈጸም እንደማያስቆመው አምነው ስለነበር፥ ካዩት ነገር በላይ፣ ከተሰማቸው የፍርሀት ስሜት በላይ የተገባላቸውን ተስፋ በሙሉ ልባቸው አምነው ነበር። መቼም ሰዎች እንደ መሆናችን መጠን የፍርሀት ስሜት ሊሰማን አይችልም ብንል ራሳችንን ውሸታሞች እናደርጋለን። የፍርሀት ስሜት ሁላችንንም ይዋጋናል። እግዚአብሄርም ይሄ ውጊያ እንዳለብን፥ ይሄ ስሜት እንደሚሰማን በደምብ ያውቃል። ለዚህም ነው “አትፍሩ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ” እያለ በተደጋጋሚ ቃል የሚገባልን። እምነት ማለት ግን ፍርሀት አለመሰማት ማለት ሳይሆን፥ በውስጣችን ለሚሰማን የፍርሀት ስሜት የምንሰጠው ተቃራኒ ምላሽ ማለት ነው። ፍርሀት አይሰማኝ ልንል አንችልም። እግዚአብሄርም የሚያዝነው የፍርሀት ስሜት ስለተሰማን አይደለም። እግዚአብሄር የሚያዝነው፥ የተሰማንን የፍርሀት ስሜት ስናምነው፥ እርሱ ከሰጠን ጽኑ ተስፋ ይልቅ ስናሰላስለውና ትልቅ ስናረገው ነው። ኢያሱና ካሌብ ልክ እንደ አስሮቹ ከእነርሱ ጋር እንደሄዱት ሰላዮች፥ የተስፋይቱ ምድር ውስጥ ያሉትን ቁመታቸው ረጃጅምና አስፈሪ ሰዎች አይተዋቸዋል። ምድሪቱ ውስጥ ያዩት የሚያስፈሩ ሰዎች ግን እግዚአብሄር የሰጣቸውን ጽኑ ተስፋ አላስጣላቸውም። ተስፋ አላስቆረጣቸውም። ፍርሀታቸው ከእግዚአብሄር ትልቅነት እንዲበልጥ አልፈቀዱም። ስለዚህ

Scroll to Top