Article

Article

ማንነት

Home Blog Book About Contact X Order Book ማንነት Audio እቤት ውስጥ ያደግነው፥ እኔ እና እህቴ ሆነን ነው። የእናት ሆድ ዥንጉርጉር ነው ብለው እነደሚናገሩት፥ ይሄ ተረትና ምሳሌ ትክክለኛ ተፈጻሚነትን ያገኘው እኛ ቤት ይመስላል። እኔና እህቴ ልጆች እያለን፥ ትንሽ እንኳን ሊቀራረብና ሊመሳሰል የማይችል የባህሪ ልዩነት ነበር የነበረን። አንዳንድ ቀን እንተያይና እንዴት እህትማማቾች ልንሆን እንደቻልን ሁለታችንም እንገረማለን። እሷ በተፈጥሮ ባህሪዋ ጸጥ ያለች፣ ከአዲስና ከማታውቀው ሰው ጋር ምንም አይነት ንግግር የማትፈልግ፥ አዲስ ሰዎችን ላለመተዋወቅ የተቻላትን ሁሉ ጥረት የምታደርግ፣ እቤታችን እንግዳ ሲመጣ፥ መኝታ ቤትዋ ገብታ በሯን በመቆለፍ በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር እየሰራ ያለ ሰው መስላ ከስልኳ ጋር የምትጫወት፥ ግርግርና ስብሰባ የማትወድ፥ ሰዎችን ለመልመድና ነጻ ሆና ለማውራት ብዙ ጊዜያቶች የሚፈጁባት ልጅ ናት። እኛን ቤተሰቦቿን እራሱ የለመደችን፥ ከተወለደች ከብዙ አመታቶች በኃላ ነው። አንዳንድ ቀን አባታችን ለስራ ፊልድ ቆይቶ ሲመጣ፥ “አላውቅህም” በሚል አስተያየት ራቅ ብላ ቆማ እያየችው የፈለገ ቢለምናት የማትቀርብ ልጅ ነበረች። ትንሽ ልቧ የሚከፈተው ተመልሶ ሌላ ፊልድ ሊሄድ ሁለት ቀናቶች ሲቀሩት ነበር። እኔ እህታችሁ ደግሞ መጫወትና መሳቅ የግል ማንነቶቼ ናቸው። ጓደኞቼን የማስቅ፥ ቤት ውስጥ እንኳን የሆነ ጥፋት አጥፍቼ አባቴ ሊቆጣኝ ሲመጣ፥ ሊስቅ የሚችልባቸውን ነገሮች እያረኩ ቁጣና ንዴቱን በሳቅ አስለውጬ የማስመልስ ልጅ ነበርኩ። አዳዲስ ሰዎችን እንደመተዋወቅ የሚያስደስተኝ ነገር አልነበረም። እቤታችን እንግዳ ሲመጣ እንግዳውን ለማጫወት ካለሁበት ተፈልጌ የምጠራው እኔ ነበርኩ። ሳሎን ቤታችን ከእንግዳው ጋር በመቀመጥ፥ የማዋራቸው፣ ስለ ቤታችን የማያውቁትን ነገር በዝርዝርና በማብራሪያ በተደገፈ ሁኔታ የማስረዳ፥ አልፎም  እንግዶቹን የማጫውትና የማስቃቸው እኔ ነበርኩ። ቤት ውስጥ ካኮረፍኩና ዝም ካልኩ፥ ቤቱ ዝም ስለሚል፥ መብራት እንደ ጠፋ ነበር የሚቆጠረው። ገና የዘጠኝና የአስር አመት ልጅ ሆኜ፥ እኩዮቼ የማይሄዱበት የእሮብ እሮብ የትልልቅ ሰዎች ጉባኤና መጽሀፍ ቅዱስ ጥናት ውስጥ የምሳተፍ፣ ልቤ ውስጥ የተፈጠረውን ጥያቄ እንዲያስረዱኝ ለመጠየቅ፥ የእድሜዬ ቁጥር አነስተኛነት አሳስቦኝ የማያውቅ፣ የገባኝን ደግሞ በተቻለኝ አቅም የማስረዳ ልጅ ነበርኩ። እኔ ለእህቴ፥ ከሌላ ፕላኔት የመጣሁ አስገራሚ ፍጥረት ነኝ። ታዲያ ቤተሰቦቼ በሙሉ ተመሳሳይ ባህሪ ስላላቸውና ከእነሱ ለየት ያለ ባህሪ የነበረኝ እኔ ስለነበርኩ፥ እነርሱ ትክክል የሆኑ፥ እኔ ደግሞ የተሳሳተ ጸባይ እንዳለኝ እያመንኩ የኖርኩባቸው ጊዜያቶች ጥቂት የሚባሉ አይደሉም። ከዚህም የተነሳ፥ እግዚአብሄር እንደ ቤተሰቦቼ ጸጥ ያልኩ እንዲያረገኝ እየለመንኩት የጸለይኩባቸው ጊዜያቶች ነበሩ። አሁን ላይ፥ በእድሜ መጨመርና እግዚአብሄር እየሰጠኝ ባለው ማስተዋል የተለወጡ አንዳንድ ባህሪያቶች ቢኖሩም፥ ምንም ብጸልይ እግዚአብሄር እስካሁን ከውስጤ ሊያወጣቸው ያልቻላቸውና ከተፈጥሮ ማንነቴ ጋር አብረው የተሰሩ ባህሪዎች አሉኝ። ከዚህ ሁሉ በኋላ ነው አንድ የህይወቴ ወቅት ላይ የሁላችንም ተፈጥሮ፣ የሁላችንም ባህሪና ጸባዮቻችን በአጋጣሚ የተሰጡን እንዳልሆኑ እየተማርኩ የመጣሁት። በምታመልኩባቸው ቤተክርስቲያኖች ወይንም ባላችሁባቸው ህብረቶች ውስጥ፥ የሰዎችን ሁሉ ባህሪ አስተውላችሁ ካያችሁ፥ የሁሉም ሰው ባህሪ ልዩ ልዩ ነው። ፈጠን ያሉ፥ ሳቅና ጨዋታ የሚወዱ፥ በተለያዩ ቦታዎች በመዘዋወር ማገልገል ስጦታቸው የሆነ፥ በህብረቶች ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ ያላቸው ሰዎች እንዳሉ ሁሉ፣ ቀስ ያሉ፥ ዝም ያሉ፥ ፕሮግራሞች ላይ መጥተው ሰምተው ብቻ መሄድ የሚፈልጉ፥ ብዙ Activity-ዎች ውስጥ የማናያቸው ሰዎች ደግሞ አሉ። ከDNA-ያችን ጀምሮ፥ እስከ ጣት አሻራዎቻችን ድረስ እግዚአብሄር ተጠንቅቆ በልዩነት እኛን የሰራበት፥ የራሱ የሆኑ ትልልቅ አላማዎች አሉት። አንድ ጊዜ ጳውሎስ በገላትያ መጽሀፍ ምእራፍ አንድ ላይ፥ በህይወቱ ስላለፈባቸው ነገሮች፣ ጌታን ሳያገኝ በፊት ስለነበረው ማንነቶቹና ባህሪያቶቹ፥ እንዴት ቀናተኛ እንደነበረ፣ እንዴት አጥፊና አሳዳጅ እንደነበረ ከተናገረ በኋላ፥ “ነገር ግን እግዚአብሄር ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን በእኔ ሁኔታ ሊገልጥ በወደደ ጊዜ ወዲያው ከስጋና ከደም ጋር አልተማከርኩም” በማለት ይናገራል።  እግዚአብሄር ልጁን ኢየሱስን በጳውሎስ ህይወት ለመግለጥ፣ የጳውሎስን እምነት እንጂ የጳውሎስን ባህሪና ማንነት በፍጹም አልቀየረም። “በእናቴ ማህጸን ሳለሁ የለየኝ” እንዳለው፥ እግዚአብሄር ገና ከእናቱ ማህጸን ጀምሮ ጳውሎስን ሲለየው፥ ይሄንን ማንነት፥ ይሄንን personality የሰጠው፥ በህይወቱ መስራት የሚፈልገውን ነገር ስለሚያውቅ ነው። በራሱ በጳውሎስ ማንነት፣ በቆራጥነቱ፣ በመሰጠቱ፣ ያመነበትን ነገር ከማድረግ ወደሁዋላ በማይለው ማንነቱ ውስጥ እግዚአብሄር ልጁን ኢየሱስን ገልጦታል። ጳውሎስ፥ ደፋር የሆነ፣ ለውሳኔዎቹና ላመነባቸው ነገሮች ነፍሱን እስከመስጠት የጨከነ፥ በአጠቃላይ አካባቢው ላይ ከነበሩ ሰዎች ለየት ያለ ባህሪ ያለው ሰው ነበር። የተለየ ማነነትና ተፈጥሮ የተሰጠው፣ የተለየ የእግዚአብሄር አላማ ህይወቱ ላይ ስለነበረ ነው። በጳውሎስ ማንነት ውስጥ፥ በጳውሎስ ባህሪና ተፈጥሮ ውስጥ የተገለጠው አስደናቂ የእግዚአብሄር የጸጋ አሰራር ታዲያ፥ እስከዛሬ ድረስ አለምን እየባረከ ይኖራል።  ኢየሱስ ለአገልግሎቱ የሾማቸውን ሀዋሪያቶችን ስታይዋቸው፥ ሁሉም የተለያየ አይነት ባህሪ ያላቸው ሰዎች ነበሩ። ለምሳሌ ዮሀንስን ብታዩት ፍቅርን የሚወድ የፍቅር ሰው ነበር። እርሱ የጻፋቸውን መጽሀፎች፥ አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ዮሀንስን ስታነቡ፥ አብዛኛው የጽሁፉ መልክቶች ስለ ፍቅር ወደ ማውራት የሚያደሉ ናቸው። ኢየሱስ ደረት ስር ጠጋ ማለት ይወዳል። ኢየሱስም ከሌሎቹ ለይቶ ዮሀንስን የሚያናግርበት፥ የፍቅር ቋንቋ አለው። እግዚአብሄር ከእኛ ጋር የሚነጋገረው፥ እኛን የሚያናግረው፥ እራሱ በሰጠን personality ውስጥ ነው። አይታችሁ ከሆነ፣ እግዚአብሄር ከአብርሀም ጋር የነበረው አይነት ግንኙነት አይደለም ከሙሴ ጋር የነበረው። እግዚአብሄር አብርሀምን ከወዳጆቹ ሁሉ ከለየው በኋላ፥ ወዳጅ ሆኖ ሲቆምለት እናያለን። ከወዳጄ ከአብርሀም የምሰውረው የለም እያለ፥ ሊያደርግ ያሰበውንና እርሱ እንኳን የማይመለከተውን ነገሮች ነበር ያወያየው የነበረው። እግዚአብሄር ከአብርሀም ጋር የነበረው አይነት ግንኙነት አይደለም ከሙሴ ጋር የነበረው። ሙሴን ያናግረው የነበረው ደግሞ፥ በክብሩ ደመና ውስጥ ነበር። ወደ ተራራ ላይ እየጠራ ነበር የክብሩን መገለጥ ያሳየው የነበረው። በእሳትና በደመና ነበር ይገለጥ የነበረው። መጀመሪያ እራሱ በኮሬብ ተራራ ላይ በእሳት ቁጥቋጦ ተአምራት ነው ወደ ራሱ አቅርቦ ልቡን የሳበውና በህይወቱ ሊያደርግ ያሰበውን አላማ በሙሉ የነገረው። እግዚአብሄር ከሙሴ ጋር የነበረው አይነት ግንኙነት አይደለም ከዳዊት ጋር የነበረው። ገና በእድሜው ማለዳ ላይ ነበር በብዙ ዝማሬና ቅኔ ከዳዊት ጋር ይነጋገር የነበረው። የእግዚአብሄርንና የዳዊትን ወዳጅነት ስናነብ፥ እግዚአብሄር ከሁሉ ነገሩ ይልቅ ከዳዊት ልብ ጋር ጥብቅ የሆነ ወዳጅነት እንደነበረው እናያለን። መጀመሪያ እራሱ ከወንድሞቹ መካከል ሊመርጠው ሲነሳ፥ ሰው ፊትን ቢያይም እግዚአብሄር ግን ልብን እንደሚያይ በመናገር፥ ሊመርጠው እራሱ የቻለበት ምክኒያት ልቡ እንደሆነ ይናገራል። ዳዊትም በመዝሙሮቹ ውስጥ ልቡን በንጽህና በመጠበቅና በእግዚአብሄር ፊት ለማቅረብ የተቻለውን ሲያደርግ እናያለን። በህግና በተአምራቱ፣ በፍቅርና በምህረቱ ውስጥ እግዚአብሄር ከዳዊት ጋር ያደረገው ንግግር አስደናቂና የእኛንም ልብ እስከዛሬ ድረስ የሚነካ ታላቅ ነገር ነው። እግዚአብሄር ከእያንዳንዳችን ጋር ያለው ግንኙነት አይነቱ የተለያየ ነው። በሰጠን ማንነት ውስጥ ነው የሚያናግረን። በሰጠን ተፈጥሮ ውስጥ ነው communicate የሚያረገን። እግዚአብሄር  እያንዳንዳችንን የሚያናግርበት የፍቅር ቋንቋ አለው። እነዚህ ቋንቋዎች ደግሞ የተለያዩ ናቸው:: ምክኒያቱ ደግሞ የሁላችንም የፍቅር ቋንቋ የተለያየ ስለሆነ ነው። ኢየሱስ ከሌሎቹ ሀዋሪያቶች በተለየ መልኩ ዮሀንስን ወደ ደረቱ ጋር የሚያስጠጋው፥ ዮሀንስ የፍቅር ሰው እንደሆነ፥ የዮሀንስ የፍቅር ቋንቋ መጠጋጋት እንደሆነ ስለሚያውቅ ነው። በዮሀንስ የፍቅር ማንነት ውስጥ ታዲያ እግዚአብሄር ፍቅርን ለአለም ሰብኮበታል። የዮሀንስ ወንጌል፣ አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ ዮሀንስ እያለ ፍቅርን ለአለም ጽፎበታል። ዮሀንስ ከዚህች ምድር ካለፈና ወደ ጌታ ከሄደ ስንትና ስንት ሺ አመታቶች ቢያልፉም፥ በዮሀንስ ማንነት ውስጥ በተገለጠው የእግዚአብሄር ፀጋ፥ እስከዛሬ ድረስ ፍቅርን እናነባለን፥ ፍቅርን እንማራለን፥ ፍቅርን እንሰበካለን። የጳውሎስን ጠንካራ ልብ ለማግኘት ደግሞ፥ እግዚአብሄር በደማስቆ መንገድ ላይ ከተፈጥሮ ውጪ በሆነ ታላቅ ብርሀንና ድምጽ መገለጥ ነበረበት። ኢየሱስ የጳውሎስን ልብ ሊያገኝ የሚችለው፥ በደማስቆ መንገድ ላይ በልዩና ከተፈጥሮ ውጪ በሆነ ተአምራት ሲገለጥ እንደሆነ ያውቃል። እግዚአብሄር በየት በኩል ቢመጣ ልባችንን እንደሚያገኘው  ያውቃል። በዚህ እውቀቱ ነው ልባችንን አግኝቶ ያዳነን። እግዚአብሄር ተስፋ እንኳን ስንቆርጥ፥ በምን አይነት ተስፋ ልባችንን ካለበት ዝቅታ ውስጥ ሊያወጣው እንደሚችል ያውቃል። በምን በኩል ካለንበት ተስፋ መቁረጥ  እንደሚያወጣን ያውቃል። አንዳችንን በሚያወጣን ተስፋ አይደለም ሌላችንን የሚያወጣን። የእያንዳንዳችንን ልብ ሊደግፍና ሊያነሳ የሚችለውን ተስፋ ጠንቅቆ ያውቀዋል። ምን እንደሚያስደስተን ያውቃል። ምን ልባችንን

Article

መዳኔ

Home Blog Book About Contact X Order Book መዳኔ Audio ዛሬ ከወትሮዬ ለየት ባለ መንገድ በክርስቶስ ውስጥ ስላገኘሁት የዘላለም መዳን ልቤ ሲገረምና ሲደነቅ ቆይቷል። አንዳንድ ቀን መዳኔ ልክ ስለሰራሁት መልካም ስራ የሚገባኝ ተመጣጣኝ ክፍያ ይመስል፣ በእግዚአብሄር ውስጥ እየኖርኩት ያለሁት ህይወት የማይገባኝና ከእግዚአብሄር ምህረት ብዛት የተሰጠኝ መሆኑን ልቤ ይዘነጋዋል:: በክርስቶስ ደም ተቀድሼ አንደበቴ ስለ ጽድቅ የማወራትን ድፍረት ማግኘቱን፣ የእግዚአብሄር ባሪያ ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሄር ልጅ ተብሎ የመጠራትን እድል ማግኘቴ ፈጽሞ የማይገባኝ ነገር መሆኑ ይረሳኛል። ግን እኮ አሁን እየኖርኩ ያለሁትና በክርስቶስ ውስጥ ያገኘኋቸው በረከቶች በሙሉ የሚገቡኝ አይደሉም። የሚገባኝማ ለሀጢያቴ የሚከፈለኝ ዋጋ ነበር። ለምሳሌ፥ የአሜሪካን ፕሮዚደንት የሆነው ባይደን እኔን በጣም ከመውደዱ የተነሳ፥ አዳብት አሮጎ ልጁ ቢያረገኝ እሱም ሰው ስለሆነ፣ እሱም ልክ እንደ እኔ አይነት ተፈጥሮ ያለው ስለሆነ ብዙም የሚገርም ላይሆን ይችላል። አይ ኸረ በጣም ይገርማል እንጂ። እንዴት የአንድ ሀያል የተባለች ሀገር መሪና አስተዳዳሪ ከመሬት ተነስቶ አንድ ምንም ውለታ ያልሰራችለትን ሴት፥ እንዴት ነው ልጄ ብሎ የሚጠራት? በየ ጋዜጣውና በየ ቢቢሲ ኒውሱ ላይ ነበር ታሪኬን የምታገኙት። እሺ ቆይ ሰማይና ምድርን ፈጥሮ፣ ዩኒቨርስን የሚያስተዳድር፣ ጸሀይን እያስወጣ የሚያስገባ፣ ነፋሳትን ወደ ወደደው ቦታ የሚልካቸው፣ በፊቱ በድፍረት መቆም የሚችል የሌለና ማንንም ሳይፈራ በጉልበቱ ጽናት የሚራመደው አምላክ እግዚአብሄር፥ በምን አይነት ተአምር ነው እኔን ልጄ ናት ብሎ የዘላለማዊ መንግስቱ ተካፋይና ወራሽ ያያረገኝ? እንዴትስ ነው አድነኝ ብዬ እንኳን ሳልጠይቀው አንድ ልጁን ለጽድቄ አይደለም፥ ለሀጢያቴ ለመሞት አሳልፎ የሰጠው? እንዴት የኪዳን ልጁ አደረገኝ? እንዴትስ ብሎ ነው ቆይ ለዘላለም ላይጥለኝና ላይረሳኝ በራሱ የማለው? ቆይ እኔ ምንድነኝ? እኔ ማነኝ? ይሄ ቃል አሳጥቶ ቃል አልባ ካላደረገኝ ሌላ ምን ያደርገኛል? ይሄ አሁን ከእግዚአብሄር ጋር የምኖረው ህይወት እኮ የሚገባኝ ህይወት አይደለም። በየቀኑ ልቤን በመደነቅ የሚሞላልኝና  ቃላቶች የማጣበት አስደናቂ ስጦታዬ ነው። ለዚህ አስደናቂ ህይወት ደግሞ፥ እኔ ያዋጣሁት ትንሽ እንኳን መልካም ነገር ቢኖር የመገረሜን ደረጃ በጥቂቱ እንኳን ሊቀንሰው በቻለ፣ መቶ በመቶ ከራሱ በሆነ ምህረት ውስጥ ከህይወት ወደ ተሻለ ህይወት አይደለም ያሻገረኝ። ከዘላለም ሞት ወደ ወደ ዘላለም ህይወት ነው ያሻገረኝ። ከብርሀን ወደ ተሻለ ብርሀን አይደለም ያሻገረኝ። ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሀን ነው ያሻገረኝ። ካሻገረኝ በኋላ ደግሞ በይ በቃ አንዴ አድኜሻለሁ፥ ካንቺ ጋር ያለኝን ጉዳይ ጨርሻለሁ አለማለቱ። ከሱ ጋር መነጋገርና መጫወት እንድችል 24 ሰአት ራሱን ለኔ ማስገኘቱ። ሰው እኮ በጥቂት ስራዎች ሲጠመድ፣ “ይቅርታ ቢዚ ስለሆንኩኝ አሁን ላናግራችሁ አልችልም” ብሎ ይመልሳል። አለምን የሚያስተዳድረው አምላክ እግዚአብሄር፥ እንዴት ብሎ ነው እኔን ለማናገር ልቡንና ትኩረቱን የሰጠኝ? ከሱ ጋር የምነጋገረው ደግሞ እሱ በፈለገበት ሰአት ብቻ ሳይሆን፥ እኔም በፈለኩት ሰአት ላናግረው ብፈልግ ራሱን ሁሌ ለኔ ማስገኘቱ በጣም ይደንቀኛል። እንዴት ነው እሱን ለማናገር ቀጠሮ ያላስያዘኝ? እንዴት ወረፋ ጠብቂ አላለኝም? ትንሽ ስልጣን አለን የሚሉ ሰዎችን እኮ በፈለኩት ሰአት ገብቼ አናግሬያቸው አላቅም። የማገኛቸውም በሰዎች በኩል እንጂ ቀጥታ ገብቼ ለማናገር እድሉ ኖሮኝ አያውቅም። እግዚአብሄር እንዴት ራሱን አሳንሶ ልቤና ቤቴ ውስጥ ገባ? ይሄን ነገሬን ወዶ ነው እንዳልል ምንም የለም። ምንድነው ያለው? እኔ በዚህች ጥቂት ዘመናቶቼ እንደዚህ አይነት ነገር አይቼ አላውቅም። አይታችሁ ታውቃላችሁ?  የመዳኔን ውድነት በቃላት ሳይሆን ልቤ ውስጥ በሚያፈሰው እውቀቱ ያስረዳኝና ያብራራልኝ የእግዚአብሄር መንፈስ ይባረክ። መንፈስ ቅዱስ አንተ ባትሰጠን ኖሮ ማን እግዚአብሄርንና ከእሱ በነጻ ያገኘናቸውን በረከቶች በቃላቶቹ ያብራራልን ነበር? ማን ነበር የሚያስረዳን? ለነገሩ የልቦናችንን አይኖችስ ቢሆን አንተ ስላበራሀው አይደል ለዚህች ምድር ሀያላንና ጠቢባን ያልተገለጠውን የወንጌል ሚስጥር ማመን የቻልነው። እንጂ እኮ እኛ ከሰዎች ሁሉ የተሻለ አማኝ ልቦና ስላለን ወይንም በቀላሉ ነገሮችን የምናምን ስለሆንን አይደለም። አሁን ያለን እምነት እራሱ ያንተ ስጦታ ነው። የእምነትን ስጦታ ሰተህ ነው ያዳንከን። ስለዚህ በእምነታችንም ቢሆን አንመካም። ኢየሱስ በምድር እያለ ስላንተ ብዙ ነገር ነግሮናል፣ አጽናኝ እንደሆንክ፣ ኑሩ ያለንን ህይወት ለመኖር ካንተ ልናገኝ ስለምንችለው እርዳታ ሁሉ ሳይቀር ነው ያጫወተን። አንተ የእውነት መንፈስ፣ ኢየሱስ የኖረውን ህይወት የምታኖረን፣ ቀድሰህ ቅዱስ ህዝቦች ያረከን። ሁሌ ከእኛ ጋር መኖርህ፣ በበደላችን ባይቸገርንህ ሰአት እንኳን ጥለኸን አለመሄድህ። ትግስትና መቻልህ። በብዙ ምክሮችህ ያጸናኸንና፣ ነገም መንገዳችን ላይ ሊመጡ የሚችሉትን ነገሮች ሁሉ እንዳንፈራ የምታረገን ብርቱ መታመኛችን ነህ።  የእግዚአብሄር መንፈስ ሆይ እናመሰግንሀለን። መዳናችን በዚህ ምድር ካገኘነው ከየትኛውም ውድ የሆነ ነገር ይበልጣል። ይሄ አለም እና ውስጥዋ ያሉት ነገሮች ቢሰበሰቡ፥ የዳንበትን መዳን ሊያክሉት አይችሉም። መዳናችን በጣም ውድ ነው። ምንም ነገር ሊከፍለው አይችልም። በጣም ውድና ልንከፍለው የማንችለው ነገር ስለሆነ ነው በነጻ የሆነው። አንዳንድ ጊዜ እኛ ሰዎች፥ ዋጋ የከፈልንባቸውንና ለፍተን ያገኘናቸውን ነገሮች በጣም የመንከባከብና ትኩረት የመስጠት፥ በነጻና ምንም ሳንለፋ ያገኘናቸውን ነገሮች ደግሞ ችላ የማለት ዝንባሌ አለን። ይሄ የእኛ የሰዎች ባህሪ ነው። መዳናችን ነጻ የሆነው፥ የገንዘብ ተመን ውስጥ የማይገባና በእኛ አቅም ሊከፈል የማይችል ነገር ስለሆነ ነው። ይሄ መዳናችን ታዲያ ነጻ የሆነው ለእኛ እንጂ፣ ኢየሱስን ግን ያላስከፈለው ዋጋ አልነበረም። የአምላክነቱን ክብር ወደ ጎን አስቀምጦ ሰው ሆኖበታል። የሰው ልጆች በምድር ላይ የሚከፍሉትን ዋጋ በሙሉ ከፍሎበታል። በከብቶች በረት ውስጥ ከመወለድ ጀምሮ እስከ መርገም ሞት ድረስ እያንዳንዱን የውርደት ጥግ ከፍሎበታል። መዳናችን ከአይምሮአችን በላይ የሆነ ዋጋ ተከፍሎበታል። እግዚአብሄርን በጣም የምትወደው ነገር ምንድነው ብትሉት የሰውን ልጆች ይላል። በጣም የምትጠላውስ ነገርስ ብትሉት ሀጢያትን ይላል። ታዲያ በጣም የሚወደውን የሰው ልጅ በጣም ከሚጠላው ሀጢያት ጋር ለመለያየት መስቀሉ እግዚአብሄር ያመጣው የእግዚአብሄር ጥበብ ነው። ታዲያ ይሄ የተሰጠን ከየትኛውም ነገር በላይ ውድ የሆነው ስጦታችን፣ በጣም ውድና የዋጋ ተመን የሌለው በመሆኑ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል። አንድ በጣም የምንወደውና የምናከብረው ሰው የሆነ ውድ ስጦታ ቢሰጠን፣ ስጦታው የመጣው በጣም ከምናከብረው ሰው በመሆኑና ውድ በመሆኑ በጣም በጥንቃቄ እንደምን ይዘው ሁሉ፣ በክርስቶስ በኩል የተሰጠን ይሄ ውድ ስጦታ፥ የሚጠይቀን ጥንቃቄ አለ። ጥንቃቄ የሚያስፈልገን ደግሞ ይሄንን ውድ የሆነ ስጦታ የምናጣባቸው ሁኔታዎች ስላሉ ነው። አሁን ውስጣችን ያለው የዘላለም ህይወት ነው። ውስጣችን ያለው ጽድቅና ቅድስና ነው። ውስጣችን ያለው የከበረ ነገር ነው። ውስጣችን ያለው ገንዘብና የአለም ሀብት የማይገዛው ነገር ነው። አሁን ያለነው አዲስ ህይወት ውስጥ ነው። አንደበቶቻችን ስለ ጽድቅና ቅድስና የማውራትን ድፍረት በክርስቶስ ውስጥ አግኝተዋል ስሙ ለዘላለም ይባረክ። አሁን ባሪያዎች አይደለንም። የእግዚአብሄር ልጆች ነን። ቅዱስ ህዝብ ነን። አሁን ቅድስና ለመያዝ የምንጣጣረው ነገር ሳይሆን፥ የአዲሱ ተፈጥሮአችን ማንነት ሆኗል። ተፈጥሮአችን ሆኗል። አሁን ውስጣችን ቢፈተሽ ያለው በጣም ውድ ውድ ነገር ነው። ምድራዊ ብርና ወርቅ እንዲሁም የትኛውም ውድ ነገር ሊገዛ የማይችለው ነገር ነው ውስጣችን ያለው። ይሄንን ሁልጊዜ ማሰብ መልካም ነው። ኤሳው እኮ ብኩርናውን ያቃለላት፣ ውድ መሆኗ በጊዜው ስላልገባው ነው። ለጊዜው ይሰማው ከነበረው የረሀብ ስሜት በልጣ ስላልታየችው ነው። ውድነቷን ቢሸፍንበት፥ አንዴ በምስር ወጥ ከሸጣትና ከለወጣት በኋላ ነው እጁ ላይ የነበረች ዘላለማዊ የእግዚአብሄር ኪዳን መሆኗ በትክክል የገባው። የሚያሳዝነው ደግሞ ከዚያ በሀዋላ ቢፈልጋት እንኳን እንዳላገኛትና ለንሰሀ እንኳን ቦታ እንዳላገኘ ቃሉ ይናገራል። ሰው የዘላለም ህይወቱን አጥቶ አለምን ሁሉ ቢያተርፍ ትልቅ ኪሳራ ውስጥ ነው ያለው። ውስጣችን ያለው ህይወት፣ ውስጣችን ያሉት ስጦታዎች አለም ላይ ውድ የተባሉ ነገሮች ቢሰበሰቡ ሊወዳደሩት አይችሉም። በጣም ውድ ውድ ነገር ይዞ የሚንቀሳቀስ ሰው ደግሞ የሌባ አይን ውስጥ መግባቱ አይቀርም። ሌባው ደግሞ ዲያቢሎስ ነው። ሊሰርቅ ሊያርድና ሊያጠፋ የሚመጣ ሌባ አለ። ለዚያ ነው ከእግዚአብሄር ያገኘናቸውን ውድ ስጦታዎች በጣም በጥንቃቄ መያዝ ያለብን። ውድ ውድ ዳይመንድ ወርቅና ኤልክትሮኒክሶች ይዘን፥ ሌባ ያለበት ከተማ ውስጥ በጥንቃቄ እንደምንመላለሰው ሁሉ፣ እግዚአብሄር የሰጠንን ውድ ስጦታዎች የዘላለም

Article

መታዘዝ

Home Blog Book About Contact X Order Book መታዘዝ Audio ዛሬ አስፈላጊ የሆነ ቀጠሮ ስለነበረኝ በጠዋት ነበር ለመሄድ የተነሳሁት። መሄድ የነበረብኝ ቦታ እኔ ከምኖርበት ሰፈር ትንሽ ራቅ ያለ ስለነበር፥ የቦታውን አድራሻ ወስጄ ስልኬን ወደዛ ቦታ እንድትመራኝ በትህትና ጠየኳት። እግዚአብሄር ይስጣት ለደቂቃ እንኳን ሳታንገራግር ነው እሺ ብላ የምፈልግበት ቦታ ያደረሰችኝ። እንዲሁ ግን አልደረስኩም። ወደምፈልገው ቦታ ለመድረስ አርጊ ያለችኝን ሁሉ ነው ያደረኩት። የእሷን ምሪት ተማምኜ ሂጂ ባለችኝ መንገዶች ሁሉ ሄድኩኝ:: ወደ ቀኝም ወደ ግራም ታጠፊ ስትለኝ አንቺ የተሻለ ታውቂያለሽ ብዬ በእሷ ላይ ያለኝን ፅኑ እምነት እየነገርኳት የምትለኝን ሁሉ አደረኩ። በዚህም ምክኒያት የምፈልግበት ቦታ ላይ መድረስ ባለብኝ ሰአት አደረሰችኝ። ዝም ብዬ ሳስበው ከእግዚአብሄር ጋር ያለን መንፈሳዊ ጉዞ በብዙ መንገድ ከዚህ ጋር ይመሳሰልብኛል።  መቼም ከህይወታቸው ብዙ ነገር ከተማርንባቸው ሰዎች ውስጥ አንዱ መዝሙረኛው ዳዊት ነው። በእግዚአብሄር እንደ ልቤ መባሉ፥ በዘመኑ ሁሉ የእግዚአብሄርን ሀሳብ አገልግሎ ማለፉ፥ እግዚአብሄርን መፈለጉ፥ አስተዋይነቱ እንዲሁም እግዚአብሄርን ከመውደዱ ብዙ ነገሮችን ተምረንበታል። ከዚህም አልፎ የዳዊት ህይወት እግዚአብሄርን ደስ ከማሰኘቱ የተነሳ፥ በብሉይ ኪዳን የነበሩት ሌሎች ነገስታት ከእግዚአብሄር ጋር በመስማማት ሲሄዱ “በአባቱ በዳዊት መንገድ ሄደ” በማለት የእግዚአብሄር ቃል ዳዊትን እንደ ሚዛን ተጠቅሞበት ነበር። ከእነዚህ ሁሉ መልካምና አስተማሪ ባህሪያቶቹ እግዚአብሄርን የበለጠ የማረከው የዳዊት ባህሪ የትኛው ነው ብላችሁ አስባችሁ አታውቁም? የዚህን መልስ ዳዊት ከሞተ በኋላ እግዚአብሄር ለልጁ ለሰለሞን ከአባቱ ህይወት እንዲማር ከነገረው ነገሮች ውስጥ ማግኘት እንችላለን።  “ዳዊትም አባትህ በየዋህ ልብና በቅንነት እንደ ሄደ አንተ ደግሞ በፊቴ ብትሄድ፥ ያዘዝሁህንም ሁሉ ብታደርግ፥ ሥርዓቴንም ፍርዴንም ብትጠብቅ፥ እኔ ከእስራኤል ዙፋን ከዘርህ ሰው አታጣም ብዬ ለአባትህ ለዳዊት እንደ ተናገርሁ፥ የመንግሥትህን ዙፋን በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ።” (1ኛ ነገ 9፡4)  ብዙ ጊዜ በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ የእምነት አባቶች ወደ እግዚአብሄር ሲፀልዩ አስተውላችሁ ከሆነ አንድ የሚሉት ነገር አለ “ለሚወዱህና ትእዛዝህን ለሚጠብቁ ቃልኪዳንህንና ምህረትህን የምትጠብቅ….” ይላሉ። እግዚአብሄርንም ከዳዊት ህይወት በጣም የማረኩት ሁለት ነገሮች ዋነኞቹ እግዚአብሄርን መውደዱና መታዘዙ ናቸው። ለልጁ ለሰለሞንም ዳዊትን ምሳሌ በማድረግ የሰጠው ትእዛዞች በእነዚህ ሁለት ነገሮች ውስጥ የሚጠቃለሉ ናቸው።  በእግዚአብሄር ፊት ትክክለኛ ህይወትና አገልግሎት አገልግሎ ለማለፍ ከትልቁ ከእግዚአብሄር እርዳታ ቀጥሎ ከእኛም የሚጠበቅ ነገር እንዳለ የዳዊትንና የሳኦልን ህይወት ማነፃፀር በቂ ነው። ዳዊት በዘመኑ ሁሉ እግዚአብሄርን ከማገልገሉና ስኬታማ ህይወት ኖሮ ከማለፉ ጀርባ አንድ ትልቅ ሚስጥር ስለ ህይወቱ የእግዚአብሄር ቃል ይነግረናል።  “ዳዊት በዘመኑ ሁሉ በእግዚአብሄር ፊት ቅን ነገርን አድርጎ ነበርና ካዘዘውም ነገር ሁሉ ፈቀቅ አላለም ነበረና” (1ኛ ነገ 15፡5)  እግዚአብሄር እያንዳንዳችንን የፈጠረበት ልዩ አላማ አለው። ይሄ አላማ የሚፈፀምበት ዋነኛ መንገድ ደግሞ የእኛ መታዘዝ ነው። በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ አካሄዳቸውን ከእግዚአብሄር ጋር ያደረጉና አላማቸውን በትክክል ያገለገሉ ሰዎችን ህይወት በጥልቀት ብናይ፥ የእግዚአብሄርን ድምፅ በመታዘዝ የተሰጣቸውን የህይወትና የአገልግሎት አደራ ከግብ ያደረሱ እንዲሁም በኖሩበት ዘመንና ትውልድ ላይ ይሄ ነው የማይባል ተፅእኖ የፈጠሩ ሰዎች ናቸው። በተቃራኒው ደግሞ ባለመታዘዝ መንገድ ላይ የቀሩ ሰዎች ታሪክም እንዲሁ ለትምህርታችን ተፅፎልናል።  እግዚአብሄር በህይወታችን ላይ የሚሰጠን ትእዛዞች በጠቅላላ ከዘላለማዊ ሀሳቦቹ ጋር በቀጥታ የተገናኙ ናቸው። አንዳንድ ጊዜ ትእዛዞቹ ለእኛ ተፈጥሮአዊ ማንነት ስሜት ባይሰጡንም፥ መታዘዝ እግዚአብሄር ከእኔ የተሻለ ያውቃል የሚል እምነት ውስጡ ስለያዘ እግዚአብሄርን ደስ ያሰኘዋል። መታዘዝና እምነት በጣም የተያያዙ ነገሮች ናቸው። ዶክተሮች አርጉ ያሉንን ሁሉ የምናረገው ጤናችንን ወደ ትክክለኛው ቦታ የመመለስ እውቀት አላቸው የሚል እምነት ስላለን ነው:: እግዚአብሄር የሚሰጠንን ትእዛዞች በመታዘዝ ውስጥ እግዚአብሄር ከእኔ በላይ ህይወቴ በየት አቅጣጫ መሄድ እንዳለበት ያውቃል የሚል እምነትን ውስጡ ይዟል።  አንድ ጊዜ እግዚአብሄር አብርሀም ጋር መጣና 75 አመት ሙሉ ከኖረበት ሀገር ዘመዶችና ቤተሰቦች ተለይተህ ውጣ አለው። ታሪኩን በተደጋጋሚ ስለሰማነውና ስለለመድነው እንጂ ራሳችንን በአብርሀም ቦታ አስቀምጠን ከተለያየ አቅጣጫ ብናየው ወደማያውቀው ሀገር ቤተሰቡን ይዞ መውጣት ቀላል ውሳኔ አልነበረም።  አብርሀም የተባለው ርስት አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፥ ወዴትም እንደሚሄድ ሳያውቅ ወጣ። (ዕብ 11፡8) “እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ” ብሎ እግዚአብሄር ለአብርሀም ትእዛዝን ሲሰጠው፥ በህይወቱ ላይ ካለው ዘላለማዊ ሀሳቡ ጋር በቀጥታ የተገናኘ ስለሆነ ነው። እግዚአብሄር ከአብርሀም ውስጥ ለራሱ የተለየ ህዝብ የማውጣት አላማ ነው የነበረው። አብርሀምን ሲያየው በእርሱ ውስጥ የእስራኤልን ህዝብ ነበር ያይ የነበረው። ታዲያ ይሄ እግዚአብሄር በዘላለማዊ ሀሳቡ ውስጥ ያየውን ህዝብ ከአብርሀም ውስጥ ለማውጣት፣ አብርሀም ከነበረበትና ከለመደው ምቹ ስፍራው መውጣት አስፈልጎት ነበር። ወዴት እንደሚሄድ ሳያውቅ የእግዚአብሄርን ድምፅ በእምነት ታዘዘ። አብርሀም አልታዘዝም ቢል የእግዚአብሄር ሀሳብ በህይወቱ አይፈፀምም ነበር።  ያ ደግሞ አብርሀም የተፈጠረበትን አላማ እንዲስት ያደርገዋል። በመታዘዙ ግን እግዚአብሄር እንደተናገረው ታላቅ ህዝብ አደረገውና የእስራኤልን ህዝብ እንዲሁም ትልልቅ ነገስታትን ከእርሱ ውስጥ አወጣ። ኢየሱስም በዚህ የዘር ሀረግ ውስጥ መጣ።  ከእግዚአብሄር የሚመጡ ትእዛዞች በውስጣቸው ትልልቅ ትርጉሞችንና አላማዎችን የያዙ ከመሆናቸውም በላይ በህይወታችን ፐዝል ውስጥ የሚገጣጠሙ ናቸው። ተገጣጥመው እስኪያልቁ ሙሉ ስእሉን ማየት ቢከብድም መታዘዝ እግዚአብሄርን ከማመን ጋር በቀጥታ የሚያያዘው ለዚህ ነው። በክርስቶስ ዳግም የተፈጠርነው መልካሙን ስራ ለመስራትና ሌሎችን ለማገልገል ነው። እኛን የፈጠረበትን አላማ የሚያውቀው እግዚአብሄር ስለሆነ ወደዛ አላማ የሚመራን በእኛ መታዘዝ ውስጥ ነው:: እያንዳንዱን ትንንሽም ሆነ ትልልቅ ትእዛዞች ከመታዘዛችን ጀርባ እግዚአብሄር በእኛ ውስጥ ሊያገለግል ያሰባቸው ሰዎች አሉ። እሺ ብለን እግዚአብሄር የሚመራንን አቅጣጫዎች ተከትለን በመሄዳችን ውስጥ እግዚአብሄር ያያቸው ሰዎች አሉ። ቢገባንም ባይገባንም መታዘዛችን የእኛ ህይወት ላይ ብቻ ሳይሆን የብዙዎች ህይወት ላይ ተፅእኖ ያመጣል። ዛሬ የእኛ መዳን ከዛሬ 2000 አመታቶች በፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እስከ መስቀል ሞት ለመታዘዝ በመወሰኑ ላይ የተመሰረተ ነው። እሱ ባይታዘዝ እኛ እስካሁን የዘላለም ጨለማ ውስጥ በሆንን ነበር። የእርሱ መታዘዝ ግን ነፍሳችንን ከዘላለም ሞት አዳነ፥ የህይወታችንንም አቅጣጫ በሙሉ ቀየረው። የእኛ መዳን በክርስቶስ መታዘዝ ላይ እንደተመሰረተ ሁሉ፥ ዛሬ በእኛ መታዘዝ ላይ ህይወታቸው የተመሰረተ ሰዎች አሉ። ከመታዘዛችን ጀርባ እግዚአብሄር ሊያድንና ሊያገለግል ያሰባቸው ሰዎች አሉ። የእኛን መታዘዝ የሚጠብቅ ህዝብና ትውልድ አለ።  አካሄዱን ከእግዚአብሄር ጋር ያደረገው ኖህ፥ አንድም ቀን በአደባባዮች ላይ ወጥቶ ሳይሰብክና ሳያስተምር፥ መርከብ እንዲሰራ የተሰጠውን መመሪያ ምንም አይነት ዝናብ ሳያይ ፀጥ ብሎ በእምነት በመታዘዙ ዓለምን ኮነነ ይለናል የእግዚአብሄር ቃል። በእምነት የሚገኘውንም ፅድቅ ወራሽ ሆነ። መታዘዛችን ከእኛ ያልፋል፥ ከእኛ ህይወት ያለፈ ተፅእኖን ያመጣል። ዓለምን ይኮንናል፥ ትውልድን ያድናል፥ የእግዚአብሄርን ፈቃድ በምድር ላይ ያስፈፅማል። መታዘዛችን በጣም ሰፊ ነው። እኛ ካለን ጠባብ አስተሳሰብ ያለፈ ነው!  ታዲያ መታዘዝ ከመፈጠራችን አላማ እና እግዚአብሄር በህይወታችን ውስጥ ካለው ዘላለማዊ ሀሳብ ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ነገር ከሆነ፥ በቃሉ ውስጥ የተፃፉልንን የእግዚአብሄርን መመሪያና ትእዛዞች ምን ያህል ለመታዘዝ እየሞከርን ነው? በግል ህይወታችንስ እግዚአብሄር የሰጠንን ትእዛዞች ምን ያህል ተግባራዊ እያደረግን ነው? ህይወታችን ፍፁም ባይሆንም፥ እንዳንድ ጊዜ ግን ቆም ብሎ እግዚአብሄር እንድናደርገው እየጠበቀብን ያሉትን ነገሮች ማሰብ፥ ለመታዘዝ መወሰን፣ እንዲሁም በሚያቅተን ነገሮች ሁሉ ላይ የእግዚአብሄርን እርዳታ መጠየቅ ትልቅ ማስተዋል ነው። “Our true success in this life is being able to fulfill the purpose we were created for!” Icon-facebook Youtube Instagram for the Kingdom through Christ ! Scroll to top Blog Book About Contact ©2026, Hana Elias. All Rights Reserved Blog Book About Contact

Article

መስዋእት

Home Blog Book About Contact X Order Book መስዋእት Audio በሀገራችን አንድ የምወደው አባባል አለ። ሰነፍ ከራሱ ውድቀት ይማራል፥ ጠቢብ ግን ከሰው ውድቀት ይማራል ይላሉ። ምን ማለት ነው? አንዳንድ ጊዜ የሆነን ነገር ለመማር ግዴታ እኛ በዚያ ውድቀት ውስጥ ማለፍ ላይጠበቅብን ይችላል። ግዴታ ዋጋ መክፈል ላይጠበቅብን ይችላል። በዚያ ውድቀት ውስጥ ያለፉ ሰዎችን ሕይወት አስተውለን በመመልከት ብቻ ብዙ ነገሮችን መማር እንችላለን። ለምንድነው ነገራቸው የፈረሰው? ለምንድነው የወደቁት? ለምድነው ዋጋ የከፈሉት የሚለውን ምክኒያት በማስተዋል ብቻ እኛ ከብዙ ውድቀት እና ዋጋ መክፈል ልንድን እንችላለን። የምንማረው ከሰዎች ስኬት ብቻ አይደለም፥ አስተዋዮች ከሆንን ከሰዎች ውድቀትም ብዙ እንማራለን። መጽሐፍ ቅዱስ ይሄንኑ ሀሳብ በምሳሌ መጽሐፍ ምእራፍ 24፡30 ላይ ሲያስረግጥ እንዲህ ይላል፥ “በታካች ሰው እርሻ፥ አእምሮ በጐደለውም ሰው ወይን ቦታ አለፍሁ። እነሆም፥ ሁሉ እሾህ ሞልቶበታል፥ ፊቱንም ሳማ ሸፍኖታል፥ የድንጋዩም ቅጥር ፈርሶአል። ተመለከትሁና አሰብሁ፤ አየሁትና ተግሣጽን ተቀበልሁ።” አያችሁ፥ ይሄ ሰው ታካች በሆነ ሰው እርሻ ውስጥ ሲያልፍ፥ የተመለከተው ነገር ነበር። የዚያ ታካች ሰው እርሻ በእሾክ የተሞላ ነው፥ እርሻው በአረም ተሸፍኗል፣ የድንጋዩ ቅጥር ሁሉ ፈራርሷል። ለምንድነው ይሄ የሆነው? የእርሻው ባለቤት ታካች ነው፥ ሰነፍ ሰው ነው። ታዲያ ይሄ የዚህን ታካች ሰውዬ እርሻ ቆሞ የተመለከተው ሰው ምን አለ? የሰውዬውን የፈረሰ እርሻ በማየት ብቻ ተግሳጽን ተቀበልኩ አለ፥ ተማርኩ ተገሰጽኩ አለ። ስንፍና መፍረስን እንደሚያመጣ፥ ስንፍና ዋጋን ስራን እንደሚያጠፋ ተማረ። አካባቢያችን የከሰረ ቢዝነስ አለ? ለምን? የፈረሰ ትዳር አለ? ለምንድነው የፈረሰው?  የእግዚአብሔር ቃል የተጻፈልን ለትምህርታችን እንደመሆኑ መጠን፥ ዛሬ በማለዳ ሳነብ በነበረው በኢሳይያስ መጽሐፍ ምእራፍ አንድ ላይ ከነበሩት የእስራኤል ሕዝቦች ሕይወት መፍረስ አንድ ትልቅ ነገር ተማርኩ። ምእራፉ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ በሕይወታቸው መፍረስ ምክኒያት የወቀሰበት ምእራፍ ነው። የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር እንዲያደርጉ ያዘዛቸውን መስዋእቶች፣ መባቻና በዓላቶች በሙሉ በማድረግ ላይ የነበሩበት፥ ነገር ግን ሕይወታቸው በብዙ እግዚአብሔርን በሚያሳዝን ድርጊቶች የተሞላበት ጊዜ ነበር። ሕዝቡ መስዋእቶችን ለማቅረብ እንዲሁም እግዚአብሔር እንዲያደርጉ ያዘዛቸውን ባእላቶች እና መባቻዎች በማድረግ ይተጋሉ፥ ነገር ግን ሕይወታቸው ክፋትን በማድረግ፣ ደምን በማፍሰስ እና እግዚአብሔርን በመበደል የተሞላ ነበር። ከዚህም የተነሳ፥ እግዚአብሔር መስዋእታቸውን መጥላቱንና መጸየፉን እንዲህ በማለት ከቁጥር 10 ጀምሮ ይነግራቸዋል።  “እናንተ የሰዶም አለቆች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እናንተ የገሞራ ሕዝብ ሆይ፥ የአምላካችንን ሕግ አድምጡ። የመሥዋዕታችሁ ብዛት ለእኔ ምን ይጠቅመኛል? ይላል እግዚአብሔር፤ የሚቃጠለውን የአውራ በግ መሥዋዕትንና የፍሪዳን ስብ ጠግቤያለሁ፤ የበሬና የበግ ጠቦት የአውራ ፍየልም ደም ደስ አያሰኘኝም። በእኔ ፊት ልትታዩ ብትመጡ ይህን የመቅደሴን አደባባይ መርገጣችሁን ከእጃችሁ የሚሻ ማን ነው? ምናምንቴውን ቍርባን ጨምራችሁ አታምጡ፤ ዕጣን በእኔ ዘንድ አጸያፊ ነው፤ መባቻችሁንና ሰንበታችሁን በጉባኤ መሰብሰባችሁን አልወድድም፤ በደልንም የተቀደሰውንም ጉባኤ አልታገሥም። መባቻችሁንና በዓላቶቻችሁን ነፍሴ ጠልታለች፤ ሸክም ሆነውብኛል፥ ልታገሣቸውም ደክሜያለሁ። እጃችሁንም ወደ እኔ ብትዘረጉ ዓይኔን ከእናንተ እሰውራለሁ፥ ልመናንም ብታበዙ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ ደም ተሞልተዋል።“  በማለት እግዚአብሔር ሕዝቡን ይወቅሳል። “የመስዋእታችሁ ብዛት ለእኔ ምን ይጠቅመኛል” ብሎ እግዚአብሔር እስከሚናገራቸው ድረስ፥ ሕዝቡ ብዙ መስዋእትን በእግዚአብሔር ፊት ያመጡ ነበር። መስዋእት በማቅረብ ጎበዞች ናቸው፥ ይተጋሉ። በመሰብሰብና በአላቶችን በማክበር ጎበዞች ናቸው ይተጋሉ። ነገር ግን ሕይወት ጎሏቸው ነበር፥ ኑሮ ጎሏቸው ነበር። ከዚህም የተነሳ ምንም መስዋእታቸው በእግዚአብሔር ፊት ቢበዛም፥ በመስዋእታቸው ብዛት እግዚአብሔር ደስ ሊሰኝ አልቻለም። እንዲያውም ጭራሽ እግዚአብሔር ምን ሲላቸው እንመለከታለን፥ “ቁርባንና እጣናችሁ በፊቴ አስጸያፊ ሆነ፥ መባቻችሁን ሰንበታችሁን እና በጉባኤ መሰብሰባችሁን አልወደውም፥ በደላችሁን ልታገስ አልችልም። የምታደርጉልኝን መባቻና በዓል ነፍሴ ጠላችው ጭራሽ ሸክም ሆነብኝ፥ መታገስ ደከምኩ ስለዚህ ልመናችሁን አልሰማም እጃችሁንም ወደ እኔ ብታነሱ አላያችሁም ምክኒያቱም እጆቻችሁ በደም ተሞልተዋል። ኑና እንዋቀስ  መስዋእቱን ለጊዜው ተውትና እስኪ እጃችሁን ታጠቡ፥ ሰውነታችሁንም አንጹ የስራችሁን ክፋት አስወግዱ፥ መልካም ማድረግን ተማሩ ፍርድን ፈልጉ፥ የተገፋውን አድኑ፥ ለድሀ አደጉ ፍረዱለት ስለ መበለቲቱም ተምዋገቱ። በፊቴ እውነተኛ ንሰሀ ግቡ እያለ ይናገራቸዋል።” “ኑና እንዋቀስ” አለ እግዚአብሔር ሕዝቡን “ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች። እሺ ብላችሁ ከታዘዛችሁ የምድርን በረከት በሙሉ ትበላላችሁ፥ እምቢ ካላችሁ ግን ሰይፍ ይበላችሁዋል።” እያለ እግዚአብሔር ሕዝቡን የወቀሰበት የእግዚአብሔር ቃል ክፍል ነው።  ይሄ የእግዚአብሔር ቃል ክፍል አንድ ነገር ያስታውሰኛል። እኔ በማመልክበት ቤተክርስቲያን ውስጥ ባለኝ የአገልግሎት ክፍል ሊያስተምረን ከኢትዮጲያ የመጣ አንድ የማከብረው አገልጋይ ከአመታቶች በፊት የነገረን አንድ ነገር ነበር። ይሄ አገልጋይ እንዲህ አለ። “እግዚአብሔር መስዋእትን የሚቀበለው፥ የመስዋእት አቅራቢውን ሕይወት ሲቀበል ብቻ ነው። የመስዋእት አቅራቢውን ሕይወት ከተቀበለ፥ መስዋእቱንም ይቀበላል። የመስዋእት አቅራቢውን ሕይወት ካልተቀበለ፥ መስዋእቱንም አይቀበልም” በማለት ያስተማረን ትምህርት ልቤ ውስጥ ቀርቷል። ብዙ ጊዜ ጭንቀታችን መስዋእቱን ማቅረብ ላይ ነው። እናመልካለን፣ እንጸልያለን፣ መባ እና መስዋእታችንን እንሰጣለን። ይሄ ሁሉ መልካም ነው እንዲያውም አድርጉ ተብለን በእግዚአብሔር ቃል ላይ የታዘዝነው ትእዛዝ ነው። ነገር ግን ብዙ ጊዜ አላማችን ህብረቶች ላይ መስዋእቱን አቅርበን መሄዳችን ላይ ነው እንጂ፥ እውነተኛው መስዋእት ከሰኞች እስከ ቅዳሜ ያለው ሕይወታችን እንደሆነ አናስተውልም። መጀመሪያ እግዚአብሔር የሚቀበለው የእሁዱን አምልኮ እና መስዋእት አይደለም። መጀመሪያ የሚቀበለው ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ያለውን ሕይወታችንን ነው።  ልክ እንደ ትምህርት ቤት ነው። አንድ ክላስ ስንወስድ ክላሱ ውስጥ የሚሰጡትን ሌክቸሮች ተከታትለን ካልተማርን፥ መጨረሻ ላይ ፈተናው ላይ መውደቃችን አይቀርም። ሕይወታችንን እንደ እግዚአብሔር ቃል እና እንደ እርሱ ፈቃድ ካልተከታተልነው መስዋእት ማቅረቡ ላይ መውደቃችን አይቀርም። ፈተናውን በጣም በጥሩ ውጤት እንድናልፍ የሚያደርገን፥ ፈተናው ቀን ላይ መገኘታችን አይደለም። ትምህርቱ በሚሰጥበት ቀናቶች መገኘታችን እና ትምህርቱ ውስጥ ያለውን ሀሳብ በአግባቡ መረዳታችን ነው። ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ወይንም የህብረት ፕሮግራም በሌለ ጊዜ ለእግዚአብሔር ህግና ስርአት የሚገዛ ሕይወት ከሌለን፥ የሚታዘዝ ሕይወት ከሌለን፣ ልክ እንደ እስራኤል ሕዝብ ሰው ባንገልም ግን ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን በመጥላት ከዋልን እና ካደርን የእግዚአብሔር ቃል እንደሚነግረን ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነውና እግዚአብሔር ከወቀሳቸው ከእስራኤል ሕዝብ የተለየ ሕይወት የለንም። በጥላቻ፣ በቂም፣ በክፋት፣ በአመጽ ውስጥ እየተመላለስን የቤተክርስቲያን ህብረቶች ላይ መጥተን ለእግዚአብሔር የምስጋናም ሆነ የዝማሬ መስዋእት እንሰዋ ማለታችን ጊዜ ከማቃጠል በስተቀር ለእኛም ሆነ ለአምላካችን ምንም የሚያመጣው ጥቅም የለም። እግዚአብሔር የመስዋእት እጥረት የለበትም። እንዲያውም መስዋእት ለማቅረብ እርሱን ለማምለክ እና ለእርሱ ለመዘመር እድል ሰጥቶን እንጂ ሰማይና ምድር ሳይሰሩ፣ የሰው ልጅ ሳይፈጠር፣ ምድር ሳትመሰረት፥ ምስጋና ሞልቶ የተረፈው አምላክ ነው። ብዙ ክብር የተረፈው አምላክ ነው። ጎሎት ስለማያውቅ አኛ አንሞላለትም። ስናመልከውም ስለሚገባው ነው እንጂ  እርሱን እየጠቀምነው ወይንም ውለታ እየሰራንለት አይደለም። ሁልጊዜ መረዳት ያለብን፥ ዋና መስዋእት ሕይወት እንጂ ዝማሬ አለመሆኑን፥ አምልኮ ኑሮ እንጂ መዝሙር እና የህብረት ስርአቶች ብቻ አለመሆናቸውን ነው። አምልኮ የሚለውን ቃል ስናስብ፥ ስለ መዝሙር ብቻ ከሚያስብ ጠባብ አስተሳሰብ መውጣት አለብን። አምልኮ ስንል በአጠቃላይ ለእግዚአብሔር ቃል ያለን መገዛት እና የመታዘዝ ሕይወት ነው። አምልኮ ትእዛዛቱን ማክበር እና መጠበቅ ነው፡፡ እርሱን በፍጹም ልባችን መውደድ እንዲሁም ሰዎችን ሁሉ እንደራሳችን መውደዳችን ነው። በፍቅር መመላለሳችን፣ በይቅርታ መመላለሳችን፣ በትጋት እና በንጹህ ሕይወት መሄዳችን ነው አምልኮ።  በኢያሱ መጽሐፍ ምእራፍ 22 ላይ የእግዚአብሔርን ሰው ኢያሱ የሮቤልና የጋድን ልጆች እንዲሁም የምናሴ ነገድ እኩሌታ የሆኑትን ህዝብ ወደ ገዛ ርስታቸው ሊያሰናብታቸው ሲል ያላቸው የመጨረሻ ቃል ይሄ ነበር። “ብቻ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ያዘዛችሁን ትእዛዙንና ሕጉን ታደርጉ ዘንድ፥ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትወድዱ ዘንድ፥ መንገዱንም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ ትእዛዙንም ትጠብቁ ዘንድ፥ ከእርሱም ጋር ትጠጉ ዘንድ፥ በፍጹምም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ ታመልኩ ዘንድ እጅግ ተጠንቀቁ።” አላቸው። ኢያሱ ሕዝቡን ምን አለ? እግዚአብሔርን ለማምለክ ተጠንቀቁ አላቸው። ምን በማድረግ አምልኩት አለ?፥ ያዘዛችሁን ትእዛዙንና ሕጉን በማድረግ፣ እርሱን በመውደድ፣ በመንገዱ ሁሉ በመሄድ፣ ትእዛዙን በመጠበቅ እና ከእርሱ ጋር በመጠጋት

Article

መማር

Home Blog Book About Contact X Order Book መማር Audio ሰሞኑን፥ የኢያሱን መጽሀፍ ነው እያነበብኩ ያለሁት። የእስራኤልን ህዝብ ከጠላቶቻቸው ጋር ተዋግቶ እግዚአብሄር የሰጣቸውን ምድር የመውረስ ታሪክ የሚነግረን መጽሀፍ ነው። መጽሀፉን በአንድ ቃል ግለጪው ተብዬ ብጠየቅ መውጣትና መውረስ ብዬ እገልጸዋለሁ። ለነገሩ ገና መጽሀፉስ ሲጀምር እግዚአብሄር ለኢያሱ መጥቶ ለአባቶቻቸው አሰጣችኋለሁ ብዬ የማልሁላቸውን ምድር ለዚህ ህዝብ ታወርሳለህና ጽና አይዞህ ብሎ በእሱ ህይወት ሊሰራ ያሰበውን የማውረስ አገልግሎት አይደል እንዴ የተናገረው። ኢያሱ አለው፥ “በህይወትህ እድሜ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም ከሙሴ ጋር እንደሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ:: አልጥልህም አልተውህም” ብሎ ይህን የሚገርም ተስፋ ከሰጠው በኋላ፥ ቀጠል አረገና ነገር ግን ሙሴ ያዘዘህን ህግ ሁሉ ጠብቅ አድርገውም። በምትሄድበት ሁሉ እንዲከናወንልህ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል። የዚህ ህግ መጽሀፍ ደግሞ ከአፍህ እንዳይለይ ሁልጊዜ አውራው፣ ተናገረው፣ ተጫወተው ከአፍህ አትለየው። የተጻፈበትን ሁሉ እንድትጠብቅና እንድታደርገው ደግሞ በቀንም በሌሊትም አስበው። አሰላስለው። የዚያን ጊዜ መንገድህ ይቃናልሀል፣ ይከናወንልሀልም ፧ በማለት ተስፋውን ብቻ ሳይሆን፣ ተስፋው በህይወቱ ይፈጸም ዘንድ ከእሱ የሚጠበቅበትንም ነገር ነው አንድ ላይ የነገረው። ብዙ ጊዜ እግዚአብሄር በህይወታችን ተስፋን ሲሰጠን ተስፋው ላይ ብቻ ነው የምናተኩረው:: በደምብ ጆሮ ሰተን መስማት ያለብን ግን ተስፋውን ብቻ ሳይሆን፣ ተስፋው ተፈጻሚነት እንዲያገኝ፣ እግዚአብሄር ከተስፋው ጋር የሚሰጠንን መመሪያዎችም ነው። ይሄ ከተስፋው ጋር የሚሰጠን ትእዛዝ፥ ተስፋው ጋር የመድረሻ መንገዳችን ነው። የተሰጡንን ትእዛዞች ስንፈጽም፣ ተስፋው መፈጸሙ አይቀርም። እግዚአብሄር እንደሆነ ታማኝ አምላክ ነው። ወደ ከነአን ትገባላችሁ የተባሉት የእስራኤል ህዝብ፣ የተሰጣቸውን ይህን ተስፋ ሳያዩ በምድረበዳ እየሞቱ ያለቁት፣ በሚጠበቅባቸው መንገድ ስላልሄዱ ነው። እግዚአብሄርማ ልጆቻቸውንና የልጅ ልጆቻቸውን ወደ ተስፋይቱ ምድር በማስገባት የተናገረውን ነገር ፈጽሞ ታማኝነቱን አሳይቷል። እነሱ ከተስፋው ጎደሉ እንጂ፣ ተስፋው መፈጸሙ አልቀረም። የተገባላቸውን የተስፋ ቃል ሳያዩ በምድረበዳ ከቀሩት የእስራኤል ህዝብ የምንማረው ከእግዚአብሄር የሚመጣ ተስፋ በሙሉ የዘላለም ህይወት ተስፋችንን ጨምሮ፣ የሚጠብቅብን ተስፋውን የሚመጥን የህይወት አይነት እንዳለ ነው። ተስፋው፥ ትእዛዙን የመጠበቂያ አቅማችን ነው። ሂዱበት የተባልነውን መንገድ የመሄጃ ጉልበታችን ነው። የድላችን፣ የማሸነፋችን፣ ስለ እኛ ከእግዚአብሄር አንደበት የወጣው ተስፋ ጋር የመድረሻ መንገዶቻችን ደግሞ፣ ከተስፋው ጋር የተሰጡን ትእዛዞችና መመሪያዎች ናቸው።  በአንደኛ ቆሮንቶስ ምእራፍ አስር ላይ ሀዋሪያው ጳውሎስ የእስራኤልን ህዝብ የምድረበዳ ጉዞ በማንሳት ሁሉም ከደመና በታች እንደነበሩ፣ ሁሉም መንፈሳዊውን መብል እንደበሉ፣ ሁሉም ከአለት የፈለቀውን መንፈሳዊ መጠጥ እንደጠጡ ያ አለት ደግሞ የክርስቶስ ምሳሌ አንደሆነ ይነግረንና፣ ምንም የእግዚአብሄርን መልካምነት ያዩ ከእግዚአብሄር እጅ የበሉና የጠጡ ህዝቦች ቢሆኑም፣ እግዚአብሄር ግን ከእነሱ በሚበዙት ደስ እንዳልተሰኘ፣ ተስፋ የተገባላቸው ምድር ውስጥ ሳይገቡ በምድረበዳ ወድቀው እንደቀሩ ይነግረናል። ይህ ታሪክ የተጻፈልን ለትምህርታችን እንደመሆኑ መጠን፣ ጳውሎስም ከእስራኤል ህዝብ ውድቀት ትምህርት ይሆናሉ ብሎ ያሰባቸውን ጥቂት ነገሮች በዚሁ ምእራፍ ላይ ጽፎልናል። ሁላችንም ጉዞ ላይ ነን። ከፊታችን ተስፋዎች አሉ። ግማሾቹ ተስፋዎች በዚሁ በምድር ላይ ባለን ቆይታ ተፈጻሚነትን የሚያገኙና እግዚአብሄር ለግል ህይወታችን የገባቸው ተስፋዎች ሲሆኑ፣ ሁላችንን በክርስቶስ አምነን የዳነውን ሰዎች አንድ የሚያረገን ደግሞ የምንጠብቀው ትልቅ የዘላለም ህይወት ተስፋ አለ። ተስፋውን መጠበቃችን መልካምና በዚህች ምድር ለምናልፍባቸው ከባባድ ፈተናዎች አቅም የሚሰጠን ነገር ቢሆንም፣ ተስፋው የሚጠብቅብንን ህይወት በእግዚአብሄር ጸጋ ተደግፈን ካልኖርነው ግን፥ ልክ እንደ እስራኤል ህዝብ ተስፋውን የማጣት አደጋ ህይወታችን ላይ እንዳለ መጽሀፍ ቅዱስ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ጽፎልናል። ጳውሎስ የእስራኤልን ህዝብ ውድቀት እንደ ምሳሌነት በማንሳት፣ የእስራኤል ህዝብ ጣኦትን በማምለክ እግዚአብሄርን እንዳስቆጡት፣ ጣኦትን አታምልኩ ብሎ ምክሩን ይጀምራል። ጣኦት ብለን ስናስብ ወዲያው ወደ ሀሳባችን የሚመጣው፥ ከወርቅ ወይም ከብር የተሰራ ምስል ሊሆን ይችላል። አዎ በድሮ ዘመን ጣኦት ምስል ባለው ነገር ይገለጥ ነበር። ጣኦት ማለት ግን፥ ልባችን ውስጥ ያለ ከእግዚአብሄር በላይ ቦታ የምንሰጠው፣ ከእግዚአብሄር በላይ ጊዜ የምንሰጠው፣ ከእግዚአብሄር በላይ ትኩረት የምንሰጠው፣ ከእግዚአብሄር በላይ የምንወደውና አጥተነው በህይወት መኖር እንደማንችል የሚሰማን ነገር በሙሉ ነው። ምንድነው ልባችንን የያዘው ነገር? ልባችን የት ነው ያለው? ከእግዚአብሄር በላይ ልናጣው የማንፈልገው ነገር ምንድነው? ብናጣቸው የመኖር ተስፋችንን በሙሉ የሚያጨልሙትና ከዚያ በሁዋላ ህይወት እንዳይታየን የሚያደርጉን ነገሮች ምንድናቸው? እግዚአብሄርን እንወዳለን እያልን ብንዘምርና ብንናገርም ግን፥ በጥልቀት ልባችንን ስንፈትሸው ከእግዚአብሄር በላይ የምንወዳቸው ነገሮች ምንድናቸው? ሁልጊዜ የምንወዳቸውን ነገሮች እያሰብን ከእግዚአብሄር እንደማይበልጡብን ጊዜ ወስደን ልባችንን መፈተሽና መመርመር አለብን። አንዳንድ ጊዜ እኮ፣ ልብን ለመፈተሽ ጊዜ መውሰድ በጣም ጥሩ ነገር ነው። በዚህ ፍተሻ ውስጥ፣ እናገኛቸዋለን ብለን ያላሰብናቸውን ነገሮች ልባችን ውስጥ ልናገኝ እንችላለን። ህይወት የሌለውንና ነገ ላይ የምንተወውን ጊዜያዊ መኪናዎቻችንን እንኳን ገንዘባችንን ከፍለን እናስመረምር የለም እንዴ? የምናስመረምረው ደግሞ፥ መኪናው ድንገት ያላየነው ችግር ቢኖርበት፣ አደጋ ላይ ሊጥለን ይችላል የሚል ስጋት ስላለን ነው። እግዚአብሄር ጋር ወስደን ያላስመረመርነው ልብም ልክ እንደዚሁ ነው። ድንገት አደጋ ላይ ሊጥለን ይችላል። አደጋው ደግሞ፣ ከመኪና አደጋ ይብሳል። ከዘላለም ጋር የተገናኘ አደጋ ነው። መዝሙረኛው ዳዊት በዚህ በምናወራው ጉዳይ ላይ ጥሩ ምሳሌ ሊሆነን ይችላል። ልቡን እግዚአብሄር ጋር እየወሰደ፣ መርምረኝ ፈትነኝ በማለት ያስመረምር ነበር። የልቡን ደህንነት በጥብቀት ይከታተል ነበር። ልባችንን ለማስመርመር እግዚአብሄር ጋር ስንሄድ ታዲያ፣ መጀመሪያ የቃሉን ብርሀን ልባችን ውስጥ በማብራት፥ መስተካከል ያለባቸውን ነገሮች በሙሉ ያሳየናል። ከልባችን ውስጥ መውጣት ያለባቸው አላስፈላጊ ነገሮች በሙሉ ይወጣሉ። ነገሮች ሁሉ ቦታ ቦታቸውን መያዝ ይጀምራሉ። እግዚአብሄርም የሚገባውን ቦታ በልባችን ውስጥ ይይዛል። ብቸኛው ተስፋችን ይሆናል። ከዚህ የተነሳ በምድር ላይ የምናጣቸው ነገሮች ለጊዜው ቢያሳዝኑንም፣ ተስፋችን ግን እግዚአብሄር ላይ ብቻ ስለሆነ አይጨልምብንም። ምንም አይነት ጣኦትም ልባችን ውስጥ እንዳይኖር ይረዳናል።  ሁለተኛው የእስራኤልን ህዝቦች ውድቀት እንደ ትምህርት በመውሰድ ጳውሎስ አትሴስኑ በማለት ይመክረናል። መቼም አሁን ባለንበት በዚህ ዘመን አለመሴሰን ወይንም መቀደስ የሚለውን ወሬ ማንሳት እንደ ፋራ የሚያስቆጥረን ጊዜ ላይ ደርሰናል። ሁሉም ሰው ደስ ያለውን ነገር የሚያረግበት ዘመን ላይ ነን። ሁሉም ሰው የተከተለው መንገድ ነው ማለት ግን፥ ትክክለኛ መንገድ ነው ማለት አይደለም። እግዚአብሄር ከህዝብ ቁጥር ጋር ችግር የለበትም። ኖህን ብቻውን አድኖት፥ የምድርን ህዝብ በሙሉ አጥፍቶ ያውቃል። ስለዚህ በዙሪያችን ያሉ ሰዎች፣ ለእኛ የስህተት መንገድ ምርጫ ተጠያቂነቱን ሊወስዱ አይችሉም። መኖር ያለብን የራሳችንን ኑሮ ብቻ ነው። አይኖቻችንን ማድረግ ያለብን ዙሪያችን ያሉት ሰዎች ላይ ሳይሆን፣ የሩጫችን ጀማሪና ፈጻሚ የሆነውን ክርስቶስን ላይ ብቻ ነው። ለእያንዳንዱ እንደ ስራው ሊከፍል ዋጋውን በእጁ ይዞ የሚመጣው እግዚአብሄር ሀሳቡን አለወጠም። አይታችሁ ከሆነ፣ ዋጋ እኮ ደሞዝ እኮ የሚከፈለው መጨረሻ ላይ ነው። እናንተ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለመኖር ወስኑ እንጂ፣ በግላችሁ ማንም ሰው ሳያውቅ ለምትኖሩት እግዚአብሄርን ደስ የሚያሰኝ ህይወት፣ በአደባባይ በብዙ ክብር የሚከፍላችሁ አምላክ ሊመጣ የቀረው በጣም በጣም ጥቂት ጊዜ ነው።  መጽሀፍ ቅዱስ በክርስቶስ ኢየሱስ ያገኘነው ደህንነት ከቅድስና ጋር ቀጥተኛ የሆነ ተዛምዶ እንዳለው ይነግረናል። ብዙ ጊዜ በክርስቶስ አምነን መዳናችንን እንጂ፣ መቀደሳችንን ቦታ ስንሰጠው አይታይም። መዳንና ቅድስና ግን፣ ሁለት የማይነጣጠሉ ነገሮች ናቸው። በቅድስና ጠርቶናል ተብሎ እንደተጻፈው፣ መጠራታችን እራሱ፣ ጥሪው እራሱ ቅዱስ ነው። ቅዱስ የሆነውን ጥሪ ተቀብለን፥ በረከሰ የህይወት አካሄድ ውስጥ እንድንመላለስ አልተፈቀደልንም። ስማችን እራሱ የንጉስ ካህናት፣ ለእርሱ የተለዩ ወገኖች፣ ቅዱስ ህዝቦች ነው የተባልነው። ጳውሎስ፣ የእስራኤልን ህዝብ ከተስፋቸው መጉደል በማንሳት ሊመክረን ሲነሳ፣ ሴሰኝነት ወይንም አለመቀደስ የእስራኤልን ህዝብ ትገባላችሁ ከተባሉት፥ ከተሰጣቸው ተስፋ ያጎደላቸው ምክኒያት እንደሆነ ይነግረናል። በኤፌሶን መጽሀፍ ምእራፍ 5 ቁጥር 5 ላይም እንዲሁ ጳውሎስ ሲናገር፣ “ይህን እወቁ፣ አመንዝራም ቢሆን ወይም ርኩስ ወይም የሚመኝ እርሱም ጣኦትን የሚያመልክ በክርስቶስና በእግዚአብሄር መንግስት ርስት የለውም።” በማለት ያስጠነቅቀናል። ቅድስናን ስናስብ ብዙ ጊዜ የምናያይዘው ከዝሙት ሀጢያት ጋር ብቻ ይሁን እንጂ፣ መቀደስ ሁለንተናዊ እንደሆነ ማወቅ ይኖርብናል። በንግግራችን፣ በአስተሳሰባችን፣ በድርጊቶቻችን ሁሉ ልንቀደስ ይገባል። በየትኛውም ሀጢያት ብንስት ታዲያ፣

Article

ልቤ

Home Blog Book About Contact X Order Book ልቤ Audio ዛሬ ቀኑ ፀሀያማና ደስ የሚል ነው። እኔም ከሰዎች ጋር አንድ አስፈላጊ ቀጠሮ ስላለኝ ወደዛ ለመሄድ እየተዘጋጀሁ ነው። መዘነጥ አይበላችሁ! ፏ ብያለሁ! የክት ልብሴን ለባብሼ፥ ፀጉሬን አስተካክዬ፥ ሽቶዬን ተቀባብቼ ከጨረስኩ በኋላ፥ ከመውጣቴ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ራሴን በመስታወት ማየት ስለነበረብኝ ወደ መስታወቱ ጋር ጠጋ ብዬ ራሴን ማየት ጀመርኩ። እዛው እንደቆምኩ ጥቂትም ሳይቆይ ነው ሀሳቦች በልቤ መምጣት የጀመሩት። እነዚህ የምሄድባቸው ሰዎች እኮ መልኬን ብቻ ነው ማየት የሚችሉት። እንዲህ መልኬን የሚያሳይ መስታወት እንዳለ ልቤንም የሚያሳያቸው መስታወት ይኖር ይሆን? እያልኩ መልኬንም ልቤንም በአንድ ጊዜ ማየት ስለሚችለው አምላክ ማሰብ ጀመርኩ። ነፍሴን ከመንፈሴ መለየት እስኪችል ድረስ ዘልቆ የሚገባው ቃሉ፥ ልቤ ውስጥ ያሉትን ሀሳቦች በሀሳብ ደረጃ ገና ወደ ልቤ ከመምጣታቸው በፊት ያውቃቸዋል። ምኞቶቼን ከነ ምክኒያታቸው መርምሮ እኔ እንኳን ስለ ራሴ የማላውቃቸውን ማንነቶቼን በዝርዝር ያውቃቸዋል። የእኔን ትክክለኛ ማንነት ለማወቅ የትኛውንም የቅርቤን ሰው መጠየቅ አያስፈልገውም። ገና ከእናቴ ማህፀን ሳይፈጥረኝ በፊት፥ የህይወቴን አካሄድ አይቶታል። ያልተፈጠሩትን ቀናቶቼን ደግሞ አንድም ሳይቀሩ በራሱ መፅሀፍ ላይ ፅፏቸዋል። ሰዎች እንዳያውቁብኝ ብዬ በልቤ የሚስጥር ክፍል ውስጥ ያስቀመጥኳቸውን ሚስጥራቶች በሙሉ ፊት ለፊት ያያቸዋል። የሆንኩትን ካልሆንኩት ለይቶ ትክክለኛ ማንነቴን በሚያውቀው አምላክ ፊት እንደምወጣና እንደምገባ ሳስበው ፈራሁምም ተገረምኩምም።  ታዲያ ግን ቆይ ሰዎች ስለሚያዩት ውጫዊው ማንነታችን ይሄንን ያህል ከተጨነቅን፥ 24 ሰዓት በእግዚአብሄር ፊት እየታየ ስላለው ልባችን የማንጨነቀው ለምንድነው? ጠዋት ከቤታችን ስንወጣ፥ ስለ አለባበሳችን ተጨንቀን አለባበሳችንን አሳምረን ከወጣን፥ ለምንድነው የህይወታችንን ትርጉም በያዘው አምላክ ፊት የሚታየው ልባችንን አስተካክለን የማንወጣው? በህይወታችን ላይ እኮ ትክክለኛውን ፍርድ ሰጪ ሰው አይደለም፥ እግዚአብሄር ነው። የሚመዝነን ደግሞ በአለባበሳችንም አይደለም። ባንካችን ውስጥ በሰበሰብነው የገንዘብ መጠንም አይደለም። በምንነዳው የመኪና ዘመናዊነትም አይደለም። በትምህርት ደረጃችንም አይደለም። በእኛ ምድራዊ መለኪያዎች አይደነቅም። አይምሮአችንን ፈጥሮ፥ በአይምሮአችን የግምት መጠን ውስጥ ሊገባ የማይችለው ይሄ ትልቁ እግዚአብሄር ከእነዚህ እድሜ የጠገቡ ተራሮች አንስታችሁ፥ ሰው በእውቀቱ ልክ ተመራምሮ ያልደረሰባቸው ሰማይ በሉት ምድር፥ ህዋ በሉት ጠፈር፥ የብስ በሉት ደረቅ ምድር እነዚህ ሁሉ እግዚአብሄር ከአንደበቱ ያወጣው የአንድ ቃል ውጤቶች ናቸው። እኛ በአውሮፕላን ከፍታ ላይ ወጥተን በመደነቅ ፎቶ የምናነሳቸው ደመናዎች ደግሞ፥ ለእርሱ የእግሩ ትቢያዎች ናቸው።   ይሄ ሰማይ ዙፋኑ ሆኖ ምድርን የእግሩ መረገጫ ያደረገው ትልቁ አምላክ፥ እነዚህን ሁሉ እጁ ሰርታ ከጨረሰች በኋላ ልክ እንደ እኔና እንደ እናንተ በሰማይ ትልቅነትም ሆነ በምድር ስፋት አልደነቅም አለ! መንፈሱ ወደተሰበረና በቃሉ ወደሚንቀጠቀጥ ልቡ ውስጥ ትህትናን ባገኘበት ሰው ግን ተደነቀ! በሰው ልጆች የልብ ሁኔታ ግን ተደነቀ! ምን አይነት ነገር ነው ቆይ?! ይሄ ከአይምሮአችን በላይ የሆነው አምላክ የእኛን ልብ ለማየት ጊዜ እራሱ አለው እንዴ? ልባችንን ለማየት ጊዜ አለኝ ማለቱ ሳያንስ፥ ልባችንን ቤቱ ለማድረግ መፈለጉ ምን አይነት ተአምር ነው?! ቆይ እኛ ማነን? እኛ ምንድነን?  እኛ ደግሞ እንዲያው ጥሎብን የሚያስጨንቀን በሰዎች ፊት ትክክል እና ፍፁም ሆኖ መታየት ነው። “ሰው ምን ይለኛል?” የሚለው ሀሳብ ህይወታችንን በይሉኝታ መኪና ወደ ወደደው ይነዳዋል። ከአለባበሳችን ጀምሮ፥ አነጋገራችን፥ ድርጊቶቻችንና ውሳኔዎቻችን በሙሉ “ሰው ምን ይለኛል?” በሚለው ተፅእኖ ስር ያደሩ ናቸው። ሰዎችን መፍራት ወጥመድ ሆኖብን፥ እግዚአብሄር እንድንኖር ከፈለገው የነፃነትና የአላማ ህይወት እየጎደልን ያለነው ጥቂቶች አይደለንም። አንዳንድ ጊዜ ትክክለኛ ያልሆኑ ነገሮችን ስናደርግ፥ የመጀመሪያው ጭንቀታችን ሰው እንዳያየንና እንደያውቅብን ነው። አይቻልም እንጂ ቢቻል፥ ከእግዚአብሄር ተደብቀን በሰው ፊት ብናደርገው ነበር የሚሻለው። በጣም መፈራት ያለበት ሰው የሚያየው ነገራችን አይደለም። እግዚአብሄር የሚያየው ነገራችን ነው። ያ ሰው ሊያየው የማይችለው በእግዚአብሄር ዘንድ ግን 24 ሰአት እየታየ ያለው ነገራችን ደግሞ ልባችን ነው። ይሄ ልብ የሚባለው ነገር በእኛ ውስጥ ይኑር እንጂ፥ እግዚአብሄር መላው ህይወታችንን ለመመዘን የሚጠቀምበት ዋና ነገሩ ነው። ልባችንን መዝኖ ሊያከብረንም  ሊንቀንም ይችላል። በሰዎች ዘንድ ይሄ ነው የማይባል ክብር የተሰጣቸው፥ በእግዚአብሄር ፊት ግን የተናቁ ብዙ ሰዎች አሉ። በአንፃሩ ደግሞ፥ በሰዎች ዘንድ ቦታ ያልተሰጣቸው፥ በእግዚአብሄር ፊት ግን ሞገስ ያገኙ ሰዎች አሉ።  በመልክና በውጫዊ ነገር፥ በቁመትና በዘለግታ ቢሆን ኖሮ የእስራኤል ንጉስ የሚሆነው ዳዊት ሳይሆን ወንድሙ ኤልያብ ነበር። ደግነቱ ከእግዚአብሄር የሚመጣ ቅባት አድራሻ አይስትም እንጂ፥ የኤልያብ ሁኔታ እኮ እንኳን ሌላ ሰውን፥ ከዳን እስከ ቤርሳቤ ቃሉ ጠብ የማይለውን አንጋፋውን ነብይ እንኳን አሳስቷል። እግዚአብሄር ግን ፊትን አላይም አለ! ስለ ውጫዊውና ሰው ስለሚያየው ነገራችሁ ብዙም አይገደኝም አለ። ልባችሁን ግን ሁልጊዜ እየመረመርኩ እመዝናችኋለሁ አለ። የእግዚአብሄርን ቅባት ከሰማይ ጎትቶ ያመጣው የዳዊት ልብ፥ ለንግስና ተፈልጎ ከጫካ ተጠራ። ሲመሰክርለትም እንደ ልቤ አለው! ልቡ ከልቤ ጋር ይሄዳል አለ። ኤልያብ በእግዚአብሄር ፊት የተናቀው፥ ዳዊትም በእግዚአብሄር ፊት የተወደደው ሁለቱም በልባቸው ሁኔታ ነው። እውነትም መፅሀፍ ቅዱስን ስታጠኑ፥ ዳዊት ከምንም ነገር በላይ ቀንና ሌሊት የሚያስጨንቀው ሰው ስለሱ የሚለው ነገር ሳይሆን፥ በእግዚአብሄር ፊት የሚታየው የልቡ ሁኔታ ነው። ብልህ ነው። ልብ በእግዚአብሄር ፊት ያለው ቦታ በደምብ የገባው ይመስላል። ልቤን መርምረው ይላል። ፈትነኝ ይላል። ልቡን በንፅህና መጠበቅ ሲሳነው ደግሞ፥ ንፁህ ልብን ፍጠርልኝ እያለ ይለምናል።   በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ በዘመናቸው ትልልቅ ተፅእኖዎችን ያመጡ ሰዎችን ህይወት ስታጠኑ፥ በእግዚአብሄር ፊት በትክክለኛ ልብ የሄዱ ሰዎች ናቸው። እግዚአብሄር ልባቸውን የወደደላቸው ሰዎች ናቸው። አንድ ትልቅና የምናከብረው ሰው አጠገባችን ቢኖር፥ ለዛ ሰው ክብር ስንል የምንናገረውን ሁሉ አስበንና ተጠንቅቀን እናደርጋለን።  ያ ትልቅ ሰው እያየን እንደሆነ ስለምናውቅ፥ አብሮነቱንና በፊቱ መሆናችንን ዋጋ እንሰጠዋለን። እንደፈለግን ከሆንን፥ አጠገባችን መሆኑና አለመሆኑ ትርጉም ካልሰጠን፥ በአጭሩ ያንን ሰው ንቀነዋል ማለት ነው። ህይወታችን መለወጥና መቀየር የሚጀምረው፥ 24 ሰአት በእግዚአብሄር ፊት እየታየን እንደሆነ በማስተዋል ስንኖር ነው። 24 ሰአት ስንል፥  እኛ በሀይለኛ እንቅልፍ ውስጥ ሆነን ራሳችንን በማናውቅበት ሰአት እንኳን፥ እግዚአብሄር ልባችንን እየመረመረ ነው። ዳዊት ሲፀልይ እንዲህ ይላል “ልቤን ፈተንኸው በሌሊትም ጎበኘኸኝ፥ ፈተንኸኝ፥ ምንም አላገኘህብኝም” (መዝ 17፡3) “ክብር እሰጥሀለሁ ጌታዬ” ብለን ብንዘምር ህይወታችን ክብርን ካልሰጠው ምን ትርጉም ይኖረዋል? በመዝሙሩ ዜማና ሙዚቃ እንደሆነ አይደነቅም። እግዚአብሄር እኮ በመላእክት ዜማ ቀንና ሌሊት ይመለካል! ትርጉም የሚሰጠው በቀናቶቻችን ውስጥ እኛን ማየቱን እውቅና መስጠታችን ነው። ሁሉን በሚያዩ አይኖቹ ፊት እንደምንወጣና እንደምንገባ በመረዳት የምንኖረው ኑሮ ነው። ይሄ ኑሮ ከመዝሙሩ ጋር ሲደመር የዝማሬ አምልኮአችንን ይቀበለዋል።  እግዚአብሄር ልብ ላይ ትኩረት የሚሰጥ አምላክ ከመሆኑ የተነሳ፥ እንማር ዘንድ መፅሀፍ ቅዱስ ስለ ተለያዩ የልብ አይነቶች ፅፎልናል። ትእቢተኛ ልብ አለ፥ አመፀኛ ልብ አለ፥ ሰነፍ፥ ሀጢያትን የሚመኝ፥ ክፉና፥ አሳች እንዲሁም ግብዝ የሆነ ልብ አለ። በአንፃሩ ደግሞ እግዚአብሄርን የሚፈራ፥ ትሁት የሆነ፥ ንፁህ፥ ትጉህ፥ ጥበበኛና መልካም ልብ አለ። የእኛ ልብ በእግዚአብሄር ፊት ሲታይ ምን ይመስላል? ዛሬ እስኪ ትኩረታችንን ከሌሎች ከማይጠቅሙን ነገሮች ላይ አንስተን እግዚአብሄር ዋጋ በሚሰጠው ነገሮች ላይ እናድርግ። ልባችንን ለመመርመር ጥቂት ጊዜ እንውሰድ። አንዳንድ ጊዜ እኮ በህይወታችን ላይ ያን ያህል ቦታ ለማንሰጣቸው ነገሮች የምንጨነቀቅን ያህል እንኳን፥ ስለ ልባችን ግድ አይለንም። ልባችንን ሰው ሊያይብን ስለማይችል ውጪያችንን ብቻ አሳምረን ስንሄድ፥ ኢየሱስ “የተለሰናችሁ መቃብሮች” ያላቸው ፈሪሳውያን እንደዚህ አይነት ሰዎች ነበሩ። የምድር ሰው ሁሉ ተሰብስቦ ቢቀበለንና ቢወደን፥ እግዚአብሄር ግን ከናቀን ምን ይጠቅመናል? ትርጉሙስ ምንድነው? “Our true success in this life is being able to fulfill the purpose we were created for!” Icon-facebook Youtube Instagram for the Kingdom through Christ ! Scroll to top Blog Book About Contact ©2026, Hana Elias. All Rights Reserved Blog Book About Contact

Article

How do I know the will of God in my Romantic relationship

Home Blog Book About Contact X Order Book How Do I Know the Will of God in my Romantic Relationship Audio Relationships are fun! It is nice to have someone to lean on and share romantic love with. I believe most of us have at least experienced what it feels like being in a relationship and having someone to love. As fun as they are, as a Christian, it is crucial to take the time to know how to navigate through it with the word of God. Relationships are God’s idea yet; this world has placed its own definition on it. The two definitions do not align and this has caused so much chaos in our lives.  Let us start with the purpose of a relationship from a Christian perspective. Sometimes, re-considering the purpose can untangle and sort out unnecessary complications. When you go shopping, you know what you want to buy, right? You also know why you want to buy that specific product. If you are shopping for groceries, the reason would simply be because you need to eat. You have purpose for doing every small things in your life. Purpose gives everything a meaning! If you are a Christian and in a relationship, it is important to think about the reason for pursuing a relationship. If we don’t focus and remind ourselves of the purpose, it can affect our relationship with the Lord and put us through unnecessary temptations which will distract us from our eternal purpose.  Dating for Christians should be a season of “intentionally” getting to know our potential spouse so that we will evaluate if they are the right person to spend the rest of our lives with. It is a time to observe and evaluate. It is the time to detect potential red flags. It is a time to really pray and seek the guidance of the Holy Spirit to make the right decision of taking it to the next level. It is a time to ask questions to see if our purposes align and will be fulfilled down the road. If you are not ready for marriage anytime soon, it is not ideal for you to get into a relationship because the downside would overweigh the benefits. You would not turn the oven on before you make the cooking ingredients ready, would you? How do I know if she/he is the right person for me?  If you are tuning in from my previous blog posts, I’ve mentioned the importance of building a strong and deeper relationship with the Lord, before a romantic relationship. Investing the time to know the Lord in singleness helps you to know his will when it is the right time to pursue a relationship. If you are currently pursuing a relationship, here are some important questions to ask yourself to have an idea of where your relationship is standing.  Do you have peace within it? Your relationship may go through hard seasons and miscommunications can get in the way but do you feel the peace of the Holy Spirit in it? Do you see a green light to keep going? Do you feel that tangible peace when you see your future with the person you are dating? The peace of the Holy Spirit is one of the biggest ways God leads his people through life.  “He lets me rest in down green meadows, he leads me beside peaceful streams.” (Psalms 23:2 NLT).  The enemy can bring a counterfeit and try to deceive you but he can never give you peace because he has no peace to offer. Listening to the peace in your heart can help you make the right decisions.  Are you growing in your walk with the Lord while in the relationship? Do you see spiritual fruits coming out of it? The fruits can speak volumes! If you are growing and getting closer to the Lord, you are probably in the right place. If you are slacking, being distracted and feeling distanced from the Lord, it is important to pray and reconsider some of your decisions because God will never give you something that would distance you away from him! Your relationship with anyone should not affect your relationship with the Lord. Everything that is from God protects the safety of your relationship with him. As a Christian, our first priority is the relationship we have with the Lord, right? That is where our whole life stands. If any relationship shakes that ground, we should question, pray and seek counsel because it is shaking the ground that our life is built on.  Can you see yourself in your future marriage being productive with the passion God has placed in your heart? Why would God give you someone who would hinder your growth in the passion he has given you?  Does your relationship acknowledge purity? This has become a rare topic in present time. I have had people looking at me as if I am the weirdest creature in the world talking about it. Here is the deal though, just because everyone is doing it, does not make it right! We don’t follow the trend, we follow Jesus and his words. If he says it, there is power with his commandments to help us live them out. Don’t listen to the negative words of people saying, “There is no one with that mindset these days” or “You are going to remain single with that mentality.” In these situations, you can tell them that your biggest purpose and priority in this life is not getting married, it is honoring God with everything you do! Let me remind you a truth that we often times forget, You will never lose the right person by choosing to honor the Lord with your decisions. You do not as well keep the wrong person by dishonoring the Lord. Trust the Lord with all your heart and lean not on your own understanding. In all your ways submit to him, and he will

Article

Purpose of Singleness

Home Blog Book About Contact X Order Book Purpose of Singleness Audio Have you heard people say, “She is so beautiful. How come she is not taken?” or “He is handsome and has got it all together. Why is he still single?”. I’m pretty sure we have all said it or heard other people say it. The statement isn’t wrong, yet it can slowly lead people to conclude that there must be something wrong with staying single. When we keep saying that, we make singleness seem wrong and mislead people to run from the plan God has in the season of their singleness. We make them run to wrong relationships pre-maturely.  Singleness is the most important season of your life. God uses this important time to mold you into the person he created you to be, without as many distractions around. If God keeps you single, he has a plan to work on your heart and has things to speak to you before moving you into the next season.  “Therefore, I will now persuade her, and bring her into the wilderness, and speak tenderly to her.” (Hosea 2:14)  A spiritual season of wilderness is a time when God often leads his people to focus their full attention on him without interruption. If you are single, God is calling for your attention! He is wanting to have quality time just with you. The most important thing you can do for yourself in this season is to spend as much time as possible in his presence and put your entire focus on him. This is probably the only season you will have the least distractions in your life before marriage and kids.  Focusing on the Lord and spending as much time with him in your singleness will help you:  Heal from a broken heart that previous friendships/relationships caused:  Being heart broken is no fun! We all have dealt with it at some point in our lives. It could be from a family member, friendships or relationships we have been involved in. Even though they were hard to deal with, God can still use them to teach us and mold our characters if we are willing to bring them up to him. God brings something beautiful out of the ashes. God uses our brokenness to bring us closer to him but the broken part of our heart still has to be restored again before we move into the next season. A broken piece just can’t work properly! We may move on from a hurtful friendship or relationship but if it makes us fearful to approach a relationship again, then we need to go back to the Lord and ask for a complete healing. Otherwise, we will not be able to fully experience and give the love of God to others. Remember there is no fear in love, perfect love casts out fear. Singleness is the perfect time to work on your heart and get a complete healing from the Lord. To learn how to love like Jesus and to share the love of God with others.         2. Learn how to be content. God intentionally created all of us with emotional needs. Just as much as we need food and water to live, we need emotional nourishments to function properly. Wanting to be loved, accepted and appreciated could be some examples of those needs. God placed these fundamental needs to fulfill them. Jesus tells us in Matthew 6 that God knows about our basic need of food, water and clothing. If God knows about our physical needs, he also knows and understands our emotional needs. When you experience hunger, all you desire in that moment is food, right? If the feeling of hunger consumes you, you would likely not care about the type of food you want to eat. The feeling of hunger could drive you to excuse eating junk foods you normally don’t eat. Similarly, when emotional needs are not met, they can become so consuming and could drive you to seek the wrong places and pursue the wrong people. One of the main things that God would want you to learn in the season of your singleness is to find contentment in him alone and to know your new identity in Christ. You are already loved, accepted and validated. When you know your identity in Christ, you stop running to people to get those affirmations. John 4 tells the story of the woman of Samaritan. She had five husbands and still was not content with what she had. Jesus set up a divine appointment with her and told her that he is the only one who could ever satisfy the depth of her soul. Running to people to meet our emotional needs and get the affirmation we desire will eventually leave us empty and disappointed. Singleness can be a place for you to learn and understand that contentment can only come from God.        3. Understand your purpose and calling. “For we are God’s handiwork, created in Christ Jesus to do good works, which God prepared in advance for us to do.” (Ephesians 2:10) One of the most important questions you can ask the Lord in this season is what your purpose is. Purpose is something God created you to accomplish while you are here on Earth. It is the reason why you were created. Yes, it is that big! We are created in Christ Jesus to do good works that God prepared in advance for each of us. Because we are called to be the body of Christ, it is crucial to find which body part we are created to play. The big picture in this life is to know your individual assignment and serve that before you go meet Jesus. I can’t stress this enough because God does everything according to his eternal purpose in our lives.  God gave Adam, the first man, a work before he gave him a wife. His wife was given to him as a “suitable

Article

ዝግጅት

Home Blog Book About Contact X Order Book ዝግጅት Audio ዛሬ ረፈድፈድ አርጌ ነው ከመኝታዬ የተነሳሁት። እንደተነሳሁ ልቤ ወደ ቀኑ ጉዳዮቼ ቢቸኩልም፥ ኸረ በሰላም ያሳደረኝን ተመስገን እንኳን ልበለው። እግዚአብሄር ከረዳኝ ደግሞ ከቅዱስ ቃሉ ለቀኔ የሚሆነኝን ጥቂት ነገር ላንብብ ብዬ የጀመርኩትን የማቴዎስ ወንጌል ማንበቤን ቀጠልኩ። ዛሬ ያነበብኩት የማቴዎስ ወንጌል ምእራፍ 25ትን ነበር። ምእራፉ ኢየሱስ በመጨረሻው ዘመን ስለሚሆነውን ልዩ ልዩ ፍርድ በተለያዩና በሚገርሙ ሶስት ምሳሌዎች የተናገረበትና ህይወታችንን በመመልከት ራሳችንን እንድናስተካክል ያስተማረበት አስደናቂ ምእራፍ ነው።  እነዚህ ሶስት አስገራሚ ምሳሌዎች የተለያዩ የህይወት ክፍሎቻችንን የሚያመለክቱ ናቸው። የመጀመሪያው ኢየሱስን ለመቀበል ወጥተው ዘይት ስለያዙትና ስላልያዙት አስር ቆነጃጅቶች በመናገር ሊኖረን ስለሚገባ የዝግጅት ህይወት የሚናገር ምሳሌ ነው። ሁለተኛው ደግሞ በተሰጣቸው መክሊት ነግደው ስላተረፉትና ስላላተረፈው ሰው በመናገር በተሰጠን የጸጋ ስጦታዎች የማትረፋችንን አስፈላጊነት የሚናገር ሲሆን የመጨረሻው ደግሞ ኢየሱስ ተርቤ አብልታችሁኛል ተጠምቼም አጠጥታችሁኛል እንዲሁም ተርቤ አላበላችሁኝም ተጠምቼም አላጠጣችሁኝም ስለሚላቸውና ሊኖረን ስለሚገባው የማካፈል ህይወት የሚናገር ምሳሌ ነው።  የማቴዎስን ወንጌልን ስታጠኑት፥ አብዛኛውን ጊዜ ኢየሱስ እየደጋገመና ትኩረት እያረገ በልዩ ልዩ ምሳሌዎች ለደቀ መዛሙርቱ ይናገር የነበረው፥ ስለ እግዚአብሄር መንግስት ጉዳይ ነበር። በዚህ በማቴዎስ ምእራፍ 25 ላይ ታዲያ ኢየሱስ ሶስት ልዩ ልዩ ምሳሌዎችን በማንሳት ከመጨረሻው ፍርድ ጋር ተያይዞ አንድ ክርስቲያን ህይወቱን እንዴት ማዘጋጀት እንዳለበት እና ምን ላይ ማተኮር እንዳለብት አስተምርዋል። በመጀመሪያው ምሳሌ፥ የተዘጋጀ ህይወት ይኑራችሁ በማለት ኢየሱስ የ10ሩን ቆነጃጅቶች ምሳሌ ይናገራል። የ10ሩ ቆነጃጅቶች ምሳሌ፥ ልክ እኛ ዛሬ ያለንበትን ዘመን ይመስላል። ሙሽራው ይመጣል ብለው ለረጅም ሰአት ቁጭ ብለው ቢጠብቁም፥ መጠበቃቸው እጅግ ሲረዝም 10ሩም እንቅልፍ እንቅልፍ ብሏቸው ተኝተው ነበር። ታዲያ በተኙበት እኩለ ሌሊት ላይ “ሙሽራው መጥቷልና ትቀበሉት ዘንድ ውጡ” የሚል ድንገተኛ ድምጽና ውካታ ሲሆን፥ ምንም እንቅልፍ እንቅልፍ ብሏቸው የተኙት 10ሩም ሴቶች ቢሆኑም፥ የኢየሱስ ድንገት መምጣት በ10ሩም ቆነጃጅቶች ላይ የፈጠረው ስሜት ግን አንድ አይነት አልነበረም። አምስቱ ልባሞች ሌሎቹ 5ቱ ደግሞ ሰነፎች ነበሩ በማለት ኢየሱስ በምሳሌው ይናገራል። ልባሞቹ ለካ ምንም ለሌሎቹ ጋር አብረው ይተኙ እንጂ ተጨማሪ ዘይት በመያዝ በዝግጅትና በጥንቃቄ ነበር የተኙት። የተዘጋጀ ማነነት ስለነበራቸው የኢየሱስ መምጣት ብዙም ግራ አላጋባቸውም። ሌሎቹ 5ቱ ቆነጃጅቶች ግን የኢየሱስ መምጣት ከፍተኛ የሆነ ድንጋጤና ግራ መጋባት ሲፈጥርባቸው ይታያል። “ወይኔ መብራታችን ሊጠፋብን ነው። እስኪ ዘይት የያዙትን ትንሽ እንዲሰጡን እንጠይቃቸው። ሙሽራው ደግሞ ደርሷል። ታዲያ ምን ይሻለናል። በናታችሁ ትንሽ ዘይት ስጡን መብራታችን ሊጠፋብን ነው” ቢሉም ልባሞቹ ዘይታቸውን ማካፈል የማይችሉበት ወሳኝ ሰአት እንደሆነ ተናግረዋል። እነዚህ 5ቱ ሰነፍ ቆነጃጅቶች ታዲያ ኢየሱስን በሚቀበሉበት ወሳኝ ሰአት፥ ዘይት ለመግዛት ወደሌላ ቦታ እንደሄዱና ሲመለሱ በሩ እንደተዘጋባቸው ኢየሱስም አላውቃችሁም እንዳላቸው እንመለከታለን። ይሄ ምሳሌ የሚያስተምረን፥ በየትኛውም ሰአት የተዘጋጀ ህይወት ሊኖረን እንደሚገባ ነው። በየምንችልበት አጋጣሚዎች ሁሉ ራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል። ክርስቶስን የማመን ህይወቴ ምን ይመስላል? የቅድስና ህይወቴ ምን ይመስላል? እግዚአብሄርን የመፈለግ ህይወቴ ምን ይመስላል? ህይወቴና አካባቢዬ ላይ ካሉት ሰዎች ጋር ያለኝ የፍቅርና የይቅርታ ህይወቴ ምን ይመስላል? የጸሎትና የቃል ህይወቴ የእግዚአብሄርን ቃል የመከተልና የመታዘዝ ህይወቴ ምን ይመስላል? ብለን እነዚህንና ተጨማሪ ጥያቄዎችን ራሳችንን በመጠየቅ “ራሳችንን ብንመረምር ግን ባልተፈረደብንም ነበር” እንደሚናገረው ህይወታችንን ምንጊዜም ለክርስቶስ መምጣት የተዘጋጀ መሆኑን መመርመርና እርግጠኞች መሆን ይኖርብናል። ይሄንን በማድረግ ስንኖር፥ የክርስቶስ መምጣት ድንጋጤና ፍርሀት ሳይሆን ደስታና ሀሴት ይሆንልናል።  ሁለተኛው ኢየሱስ በዚሁ በማቴዎስ ወንጌል ምእራፍ 25 ላይ የሚናገረው፥ ልዩ ልዩ መክሊት ወይንም የአገልግሎት ስጦታ ስለተሰጣቸውና ስላተረፉበት ሰዎች ነው። አንድ ሰው ባሮቹን ጠርቶ አቅማቸውን ካየ በኋላ፥ ልክ እንደ አቅማቸው መክሊቶችን ሰጥቷቸው ሄዶ ነበር። ከሄደበት ሲመለስ ታዲያ አምስት እና ሁለት መክሊት የተሰጣቸው ሰዎች፥ የተሰጣቸውን መክሊት አትርፈው መክሊቱን ከነትርፉ ለጌታቸው አስረክበዋል። ይሐውልህ ጌታዬ አምስት መክሊት ሰጥተሀኝ ነበር። ሌላ አምስት አትርፌ አስር አድርጌዋለሁ። ሌላኛውም ደግሞ መጣ፥ ለእኔም ሁለት መክሊት ሰጥተህኝ ነበር። እኔ ደግሞ፥ አራት አድርጌዋለሁ እያሉ መክሊታቸውን ሲያስረክቡ፥ አንድ መክሊት የተሰጠው ሰው መክሊቱን እንደቀበረና እንዳላተረፈበት ይናገራል። ጌታው ታዲያ በመቆጣት “መክሊቱን ውሰዱበትና 10 መክሊት ላለው ስጡ” በማለት ሲቆጣና ይሄንን ሰው በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት በማለት አስፈሪ ንግግር ሲናገር እንመለከታለን። የመጀመሪያው የ10ቱ ቆነጃጅቶች ምሳሌ ኢየሱስ ሲያስጠነቅቀን የፈለገው ሊኖረን ስለሚገባው የዝግጅት ህይወት ሲሆን፥ በዚህ በመክሊት ምሳሌ አርጎ ሊናገር የፈለገው ደግሞ ውስጣችን በተቀመጡት ስጦታዎችና የአገልግሎት ጥሪዎች በትጋት መስራትና ፍሬ ማፍራት እንዳለብን ነው። ሁላችንም ውስጥ እግዚአብሄር ወዶ ስላስቀመጣቸው የጸጋ ስጦታዎች አንድ ቀን እግዚአብሄር እንደሚጠይቀን ፈጽሞ መርሳት የለብንም። በውስጣችን የተቀመጡት ስጦታዎች፥ እግዚአብሄር በምክኒያት ያስቀመጣቸውና በእነዚህ ስጦታዎች ሊያገለግል ያሰባቸው ሰዎች እንዳሉ ማስተዋል አለብን። ይሄ መክሊቱን የቀበረው ባሪያ ፈርቼ ቀበርካት እንዳለው መክሊቶቻችንን ያስቀበሩንን ፍርሀቶች በጸሎትና በእግዚአብሄር ቃል እውነት እያሸነፍን ፍሬ ማፍራታችንን መቀጠል ይኖርብናል። ኢይሱስ በዚሁ በማቴዎስ 25 ላይ ከተናገራቸው ሶስት ምሳሌዎች የመጨረሻው ምሳሌ ደግሞ፥ ስለ መስጠት የተናገረበት አስደናቂ ምሳሌ ነው። ስለ ህይወት ዝግጅት፣ በጸጋ ስጦታ ስለማገልገል ከተናገረ በኋላ፥ በማካፈል ውስጥ ስላለው አስደናቂ ብድራት ደግሞ ሳይናገር ምሳሌውን አላጠናቀቀም። በመጨረሻው ዘመን አለ ኢየሱስ ሲናገር፥ በመጨረሻው ዘመን የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ፥ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል። አብዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ እረኛም በጎቹን ከፍየሎቹ እንደሚለይ ይለያቸውና በጎቹን በቀኝ በኩል፣ ፍየሎቹን ደግሞ በግራ በኩል ያቆማቸዋል። ንጉሱም በቀኙ ያሉትን ተርቤ አብልታችሁኛል፣ ተጠምቼም አጠጥታችሁኛል እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፣ ታርዤ አልብሳችሁኛል፣ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና ታስሬም ወደ እኔ መጥታችሁዋልና ሲላቸው፥ መቼ አግኝተንህ ነው ያበላንህና ያጠጣንህ? መቼ አግኝተንህ ነው የጠየቅንህና ያለብስንህ ደግሞስ የተቀበልንህ ቢሉት፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ እንኳን ስላደረጋችሁት ለእኔ አድርጋችሁታል በማለት እናንተ የአባቴ ብሩካን ኑ አለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግስት ውረሱ በማለት ወደ ታላቅ መንግስቱ ይጋብዛቸዋል። በግራው ያሉትን ሰዎች ደግሞ ተርቤ አላበላችሁኝም፣ ተጠምቼም አላጠጣችሁኝም፣ እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝም፣ ታርዤ አላለበሳችሁኝም፣ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝም ቢላቸው መቼ ተርበህ፣ ተጠምተህ፣ እንግዳ ሆነህ፣ ታርዘህ ወይስ ታመህና ታስረህ አገኘንህ ቢሉት፥ እውነት እላችኋለሁ፣ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም ብሎ ወደ ዘላለም ፍርድ ሲጥላቸው እንመለከታለን።  ኢየሱስ በዚህ ምሳሌው ላይ የሚናገረው፥ የማካፈል ህይወታችን የመጨረሻው ፍርድ ላይ ስለሚያሳድረው ተጽእኖ ነው። ይሄንን ምሳሌ ሳሳብ ወደ ኢየሱስ በመምጣት አንድ ጥያቄ የጠየቀው ሰው ወደ ሀሳቤ ይመታል። “መምህር ሆይ የዘላለምን ህይወት እንድወርስ ምን ላድርግ?” ብሎ ኢየሱስን ቢጠይቀው፥ ወደ ህይወት መግባት ከወደድክ ትእዛዛትን ጠብቅ” ቢለው ይሄንንማ ከልጅነቴ ጀምሬ ጠብቄያለሁ በማለት ይመልሳል። በቃ እንደዛ ከሆነ ደግሞ ሂድ ያለህን ሽጥና ለድሆች ስጥ በሰማይም መዝገብ ታገኛለህ መጥተህም ተከተለኝ ቢለው፥ ከነበረው ንብረት ብዛት የተነሳ እያዘነ ወደ ቤቱ ሄደ በማለት ኢየሱስ ይናገራል። ወዲያው ታዲያ ኢየሱስ ቀጠል አድርጎ ለባለጠጋ ወደ እግዚአብሄር መንግስት መግባት እንዴት ጭንቅ ነው በማለት ይናገራል። በነገራችን ላይ ኢየሱስ ሰርተን ገንዘብ ማግኘታችንን እና ሀብታሞች መሆናችንን አይቃወምም ኢየሱስ የሚቃወመው አለማካፈላችንን ነው። ስንት ዳቦ አጥቶ መንገድ ላይ እያለቀሰ ያለ ህጻን ወይንም አካሉ ተጎድቶ መስራት ያቃተው ሰው እያለ ሺዎች ወይንም ሚሊየን ብሮች ባንካችን ውስጥ አስቀምጠን እሱ ላይ ጨምረን ለማስቀመጥ እንሰራለን። ለሌላቸው ሰዎች መስጠት በጣም ፓወርፉል ነው በኢየሱስ ግራ ወይንም በኢየሱስ ቀኝ የማስቀመጥ ሀይል ያለው ነገር ነው። እንደ ኢየሱስ ምሳሌ ከሆነ በዘላለም መንግስት ወይንም ወደ በዘላለም ቅጣት ውስጥ የመጣል አቅም ያለው ነገር ነው። ለሌላቸው ስናካፍል፥ ለኢየሱስ እያካፈልን ነው። ሰዎችን ስናበላ፣ ስናጠጣ፣ የታመሙትን ስንጠይቅ፣ እንግዶችን ስንቀበል፣ የታሰሩትን ስንጎበኝ፣ የበረዳቸውን ስናለብስ ለኢየሱስ እያረግንለት ነው።  ስለዚህ በማቴዎስ ምእራፍ 25 ላይ ክርስቶስ ከተናገራቸው 3 ምሳሌዎች የምንማረው፥ የክርስቶስ መምጣት ድንገት ስለሆነ የተዘጋጀ ህይወት ሊኖረን እንደሚገባ፣ በተሰጠን የጸጋ ስጦታ

Article

ረሀብ

Home Blog Book About Contact X Order Book ረሀብ Audio በማመልክበት ቤተክርስቲያን ውስጥ አገልጋይ የሆነ አንድ ወንድም የእግዚአብሔርን ቃል በማስተማር ላይ እያለ አንድ ጥያቄ ጉባኤውን ጠየቀ። ለተወሰነ ጊዜ ብትታሰሩና ከመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፎች ውስጥ ይዛችሁ መግባት የምትችሉት አንድ መጽሐፍ ብቻ ነው ብትባሉ፥ የትኛውን መጽሐፍ ትመርጣላችሁ? በማለት ጉባኤውን ይጠይቃል። ይሄ ወንድም ጥያቄውን እየጠየቀ፥ በልቤ ጥቂት ካሰብኩ በኃላ  ከመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፎች ውስጥ አንድ መጽሐፍ ብቻ ነው መምረጥ የምትችይው ብባል የሐዋሪያት ስራ መጽሐፍን እንደሆነ ማሰብ ጀመርኩ። የሐዋሪያት ስራ መጽሐፍ በጣም የምወደው መጽሐፍ ነው። ከመጽሐፎች ሁሉ ውስጥ ለምን የሐዋሪያት ስራ መጽሐፍን መረጥሽ ከተባልኩ፥ መጽሐፉን የመረጥኩበት ዋና ዋና ምክኒያቶች እነዚህ ናቸው። የሐዋሪያት ስራ መጽሐፍ መንፈስ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ምድር ሲወርድ የተከሰቱትን ነገሮች የሚናገር ልዩ መጽሐፍ ነው። መንፈስ ቅዱስ ወደ ምድር ሲወርድ፥ ፈሪ የነበሩት እነ ጴጥሮስ በብዙ የመንፈስ ቅዱስ ድፍረት ሲያገለግሉ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ በልዩ ልዩ ድንቅና ታምራቶች ቃሉን በመካከላቸው እያጸና በሚታይና በሚዳሰስ መልኩ አብሯቸው ሲሰራ የምትመለከቱበት፥ ከዚህም የተነሳ የወንጌል እሳት እየነደደ ብዙዎች በክርስቶስ በማመን ሕይወታቸውን ለእግዚአብሔር ሲሰጡ የምታዩበት አስደናቂ መጽሐፍ ነው። በተጨማሪም፥ ሐዋሪያቶቹ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ታግዘው በብዙ ሲተጉ እና ዋጋ ሲከፍሉ የምትመለከቱበት፥ እነ ሳኦል ጳውሎስ ወደመሆን የተቀየሩበት የጳውሎስን የአገልግሎት ጉዞ እና አስደናቂ የሕይወት ምስክርነት እያነበባችሁ የምትደነቁበት መጽሐፍ ነው። የሐዋሪያት ስራ መጽሐፍን በአጠቃላይ ስትመለከቱ፥ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በሰዎች ድካም ውስጥ ሲያልፍ የሚሆኑትን አስደናቂ ነገሮች ትማሩበታላችሁ።  የእግዚአብሔርን ቃል ከትላንት ዛሬ በተሻለ መንገድ እየተማርኩ ስመጣ፥ በዘመናቶች መካከል እግዚአብሔር ትልልቅ የሆኑ አላማዎቹን በምድር ላይ የፈፀመው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንደሆነ እየተረዳሁ መጣሁ። የአዲስ ኪዳን መጽሐፍትን ብቻ ሳይሆን፥ የብሉይ ኪዳን መጽሐፎችንም ስትመለከቱ እግዚአብሔር በነገስታቶች፣ በመሳፍንቶችና በነቢያቶች ሕይወት ለመስራት እና በጊዜው የነበረውን ዓላማ ለመፈጸም የቀባቸው በመንፈስ ቅዱስ ቅባት ነበር። ሳምሶን የእስራኤልን ሕዝብ ተገዝተው ከነበረበት ከፍልስጥኤም ግዛት ለማዳን ተቀብቶ ነበር፥ በመሳፍንት መጽሐፍ ላይ እያነበብን የምንደነቅበት የሳምሶን ልዩ የሆነ ሀይል፥ የሳምሶን የጡንቻ ሀይል አይደለም የእስራኤልን ሕዝብ ከጠላቶቻቸው እጅ ያድን ዘንድ በሳምሶን ውስጥ የተገለጠ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ነው። ሌላ ምሳሌ እንመልከት ካልንም ኢዩ ኤልዛቤልን ለመበቀል ተቀብቶ ነበር ከእግዚአብሔር ቃል እንረዳለን፣ በእስራኤል ላይ ለመንገስ የተጠሩትን የሳኦልን እና የዳዊትን አገልግሎትም ስንመለከት፥ የእስራኤልን ሕዝብ ለመምራት እና ለመጠበቅ በንግስና ቅባት ተቀብተው ነበር። ሳኦልና ዳዊት በንግስና ቅባት የተቀቡት፥ የእግዚአብሔር መንፈስ በእነርሱ ውስጥ አልፎ ሕዝቡን ይመራ እና ይጠብቅ ዘንድ ነው። ይሄንን በራሳቸው ኃይል ማድረግ ቢችሉ ኖሮ መቀባት አያስፈልጋቸውም ነበር። የሳኦልንና የዳዊትን የንግስና አገልግሎት እኮ ልዩ ልዩ ያደረገው የሳኦል ከሁለት አመት በላይ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አለመቀጠል እና የዳዊት ደግሞ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እስከመጨረሻው መቀጠል ነበር። ሳኦል ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተጓዘው ለሁለት አመታቶች ብቻ ነበር። የዳዊትን አገልግሎት ውብ ያደረገው፥ በሕይወቱ ከፍታዎችም ሆነ ዝቅታዎች ውስጥ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አብሮ መጓዙ ነበር። የእግዚአብሔር ቃል  በኢዮብ መጽሐፍ 26፡13 ላይ ሲናገር “በመንፈሱ ሰማያት ውበትን አገኙ” በማለት ይናገራል። ሰማያቶች እንኳን እኮ የተዋቡት፥ ውበትን ያገኙት በእግዚአብሔር መንፈስ ነው። የእኛም ሕይወታችን የሚዋበው፥ እያንዳንዱ ነገራችን ውበትን የሚያገኘው በእግዚአብሔር መንፈስ ነው። የነገሮቻችን ሁሉ ውበት ያለው በመንፈስ ቅዱስ ከእኛ ጋር መሆን ነው። የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የምድር አገልግሎትም እንዲሁ ስንመለከት በምድር የነበረውን አገልግሎቶች በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንዳገለገለ የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል። እንዲያውም በሉቃስ ወንጌል ምእራፍ 4 ላይ እንደሚናገረው፥ በሰንበት ወደ ምኩራብ ገብቶ የእግዚአብሔርን ቃል ሊያነብ ሲነሳ በነቢዩ በኢሳይያስ መጽሐፍ ላይ ስለ እርሱ የተጻፈውን ቃል እንዲህ በማለት በፊታቸው ቆሞ አንብቦ ነበር። “የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፥ ለታሰሩትም መፈታትን ለእውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል” በማለት አንብቦ ነበር። በሐዋሪያት ስራ ምእራፍ 10፡38 ላይም ስለ ኢየሱስ የምድር አገልግሎት ሲናገር፥ እንዲህ ይላል። “እግዚአብሔር የናዝሬቱ ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና..” በማለት የኢየሱስ የምድር አገልግሎት በመንፈስ ቅዱስ ሙላት ውስጥ እንደነበረ ይናገራል። ታዲያ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ተቀብቶ ካገለገለ የእኛ አገልግሎት እንዴት ከመንፈስ ቅዱስ ውጪ ሊሆን ይችላል? እንዲያውም መንፈስ ቅዱስ ምን ያህል አስፈላጊ መሆኑን ኢየሱስ ሲናገር በዮሐንስ ወንጌል 16፡7 ላይ እንዲህ ብሎ ነበር። “እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።” በማለት መሄዱን የተሻለ አድርጎ የተናገረበት ዋና ምክኒያቱ የመንፈስ ቅዱስ ወደ ምድር መምጣት እና ከእኛ ጋር መሆን ነው።  ብዙ ጊዜ ስለ መንፈስ ቅዱስ ስናስብ፥ ቶሎ ወደ ሀሳባችን የሚመጣልን፥ በኃይል የተሞላ ፀሎት ወይንም በቤተክርስቲያን ውስጥ የምናያቸው ለየት ያሉ እንቅስቃሴዎች ናቸው። የእግዚአብሔር መንፈስ ግን ከፀሎት እና በልሳን ከመናገር ያለፈ በርካታ ስራዎችን በሕይወታችን ውስጥ ይሰራል።  ሐዋርያቱ በመንፈስ ቅዱስ ከተሞሉ በኋላ፥ በሕይወታቸው ውስጥ ልዩ ልዩ ለውጦች ሆነው እንደነበር ከእግዚአብሔር ቃል እንረዳለን። ኢየሱስን ሶስት ጊዜ የካደው ጴጥሮስ፥ ከሶስት ሺህ በሚበልጡ ሰዎች መሀከል ስለ ኢየሱስ የሚመሰክርበትን ድፍረት አግኝቶ ነበር። የእግዚአብሔር መንፈስ በተጠራንበት የአገልግሎት ስፍራ የምንቆምበት ድፍረታችን ነው። ይሄ በሐዋሪያቱ መካከላቸው የመጣው የእግዚአብሔር መንፈስ፥ በብዙ አይነት መንገድ የደቀ መዛሙርቱን ሕይወትና አገልግሎት እየለወጠ፥ ብዙ ድንቆችንና ተአምራቶችን ያደርግ ነበር፥ ብዙ አዳዲስ ሰዎችም ኢየሱስን በማመን በእነርሱ ላይ ይጨመሩ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ፥ ደቀ መዛሙርቱ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዲኖሩ መንፈስ ቅዱስ ሕይወታቸውን በተለያየ አቅጣጫ እየቀደሰ፥ በአገልግሎታቸው ውስጥ ይሰራ ነበር። የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እንደመሆኑ እኛን ለመቀደስ የሚረዳን ቅድስናችን ነው። ከዚህም በተጨማሪ ወደ እውነት ሁሉ የሚመራን መሪያችን ነው።  መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን ውስጥ ሁለት ትልልቅ አላማዎች አሉት። አንዱ አላማው፥ እኛ ክርስቶስን በመከተል ስንኖር በሚያስፈልገን ነገሮች ሁሉ እኛን መርዳት ሲሆን፥ ሌላኛው አላማው ደግሞ በእኛ ውስጥ ሆኖ ሌሎች ሰዎችን መርዳት ወይንም ማገልገል ነው። የመጀመሪያው የመንፈስ ቅዱስ አላማ እኛን እራሳችንን መርዳት ነው። መቼም መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን ያለውን ስራና አገልግሎት አንድና ሁለት ብለን መቁጠር ባንችልም ጥቂቶቹን እንዘርዝር ካልን፥ እኛን በማጽናናት፣ በመምከር፣ በመውቀስ፣ ወደ እውነትና ወደ እግዚአብሔር ሀሳብ በመምራት፣ በመቀደስ፣ ድካማችንን በማገዝ፣ የእግዚአብሔርን ማንነቶች ለእኛ በማስረዳት፣ የእግዚአብሔርን ቃል ፍቺ በማብራት፣ በእኛ ውስጥ ሆኖ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመጸለይ እንዲሁም በሌሎች በርካታ ነገሮች ይረዳናል፣ ያንጸናል፣ እግዚአብሔርን የሚመስል ሕይወት እንድንኖር በተለያየ አቅጣጫዎች ያግዘናል። በሮሜ 8፡26 ላይ ሲናገር፥ መንፈስ ቅዱስ ድካማችንን እንደሚያግዝ እና እኛ እንዴት መጸለይ እንዳለብን ስለማናውቅ በማይነገር መቃተት በውስጣችን እንደሚቃትት እንዲሁም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን እንደሚማልድ ይናገራል። እኛ በስጋችን ስንጸልይ የራሳችንን ፍላጎቶች ብቻ ነው የምንጸልየው፥ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ የሚጸልየው ግን የአብን ፈቃድ ነው።  እንግዲህ ከላይ እንዳልነው የመንፈስ ቅዱስ አንዱ ስራው እኛን መርዳት ሲሆን፥ ሌላኛው በሕይወታችን የሚሰራው ትልቁ ስራ ደግሞ በተፈጠርንበት አላማ ውስጥ ሌሎችን ማገልገል ነው። መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ሆኖ ሌሎችን ያገለግላል፥ ይመክራል፣ ያስተምራል፣ ያጽናናል፣ ይፈውሳል፣ መንገድ ያሳያል፣ የእግዚአብሔርን ቃል ይገልጣል፣ በወደደው መንገድ እኛን ለራሱ አላማና ስራ ይጠቀማል።   በዓለ ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ልክ ድንገት እንደሚነጥቅ አውሎ ነፋስ በመካከላቸው እንደመጣና ቤቱን እንደሞላው፥ እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች እንደታይዋቸው፥ በሁሉም ላይ መንፈስ ቅዱስ እንደሞላባቸውና መንፈስ ቅዱስ በሰጣቸው ልሳኖች መናገር እንደጀመሩ ይናገራል።  ታዲያ እዚያው የሐዋሪያት ሥራ መጽሐፍን ማንበባችሁን ስትቀጥሉ፥ ሐዋሪያቱና ደቀ መዛሙርቱ የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ከተቀበሉ በኋላ፥ ወዲያው የገቡት ወደ አገልግሎት ነበር። ወዲያውኑ ነበር ስለ ክርስቶስ መመስከር የጀመሩት። ኢየሱስም ወደ አባቱ ሳያርግ

Scroll to Top