መድሀኒት
Audio
በሀገራችን አንድ የተለመደ አባባል አለ። “በሽታውን ያልተናገረ መድሀኒት አይገኝለትም” ይላሉ። አባባሉ እውነት ነው። አንድ ሰው ሲታመም፥ እንደታመመ መጀመሪያ ቀድሞ የሚረዳው እራሱ ያ ሰው ነው። ይሄ ሰው ታዲያ በሽታውን የመናገርና መፍትሄ የማግኘት፥ ወይንም ደግሞ ዝም በማለት ህመሙን የመደበቅ መብት አለው፥ በተለይ ደግሞ በጣም ካልባሰበትና ከአቅሙ በላይ ካልሆነ። ህመሙን መደበቁ ግን፥ መድሀኒት እንዳይገኝለት አልፎም ደግሞ በሽታው እንዲብስና የበለጠ እንዲጎዳው ሊያደርግ ይችላል። ስለዚህ አንድ የታመመ ሰው፥ መድሀኒት ያገኝ ዘንድ መጀመሪያ እንደታመመና እርዳታ እንደሚያስፈልገው ማመን አለበት ምክኒያቱም፥ የሚሰጠውን መድሀኒት መውሰድና መዳን ወይንም ደግሞ ህመሙን ማስታገስ የሚችለው፥ እንደታመመ ሲያምን ብቻ ነው።
ስለዚህ ጉዳይ ሳስብ፥ ወደ ሀሳቤ የሚመጣ አንድ የመጽሀፍ ቅዱስ ክፍል አለ። ክፍሉ የእግዚአብሄር መልአክ መጥቶ ስለ ኢየሱስ መወለድ በሜዳ በጎቻቸውን ሲጠብቁ ላደሩ እረኞች የሚናገርበት ክፍል ነው። መልአኩ በድንገት ለእረኞቹ ተገልጦ እረኞቹን ያላቸው ነገር ይሄ ነው። “እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።” አላቸው። የመልአኩ አባባል የሚገርም ነው! “አሁን የምነግራችሁ የምስራች፥ ለህዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ ነው” አለ። መቼም አንድ ህጻን ሲወለድ፥ ደስታ የሚሆነው ለወለዱት ቤተሰቦቹና በቅርቡ ላሉት ወዳጅ ዘመዶቹ ብቻ ነው እንጂ፥ ለህዝቡ ሁሉ ታላቅ ደስታ ሊሆን አይችልም። እንደ መልአኩ አባባል ከሆነ ግን፥ የዚህ የተወለደው ህጻን ደስታ የቤተሰቦቹ ብቻ ሳይሆን የህዝቡ ሁሉ ነው። የህጻኑ መወለድ ለህዝቡ ሁሉ ታላቅ ደስታና የምስራች የሆነበትን ሚስጥር ታዲያ መልአኩ እንዲህ በማለት ይናገራል። የተወለደው ህጻን ለእናንተ የሚሆን መድሀኒት ነው አለ። መቼም ከላይ እንዳልነው፥ ሰው መድሀኒት የሚያስፈልገው ሲታመም ነው። ጤነኛ የሆነ ሰው መድሀኒት አያስፈልገውም።
አምላክ ሲሆን ራሱን ከሰው ልጆች አንዱ ለማድረግ ፈቅዶ ወደ ምድር የመጣው ኢየሱስ፥ የሰው ልጆችን መከራ ሊቀበልና በመስቀል ላይ ሊሞት ያስፈለገው፥ በአዳምና በሄዋን አለመታዘዝ ምክኒያት የሰው ዘር በሙሉ በሀጢያት በሽታ ስለተበከለ ነው። አንድ ሰው መድሀኒት ለመውሰድ መታመሙን አምኖ መቀበል እንደሚያስፈልገው ሁሉ፥ ኢየሱስ ስለ ሀጢያታችን የከፈለውን ዋጋ በመቀበል መዳን የምንችለው፥ መጀመሪያ ከፍጥረታችን ሀጢያተኞች መሆናችንን ስናምን ብቻ ነው። ሀጢያተኞች መሆናችንን በመረዳት፥ መድሀኒት ለመሆን ኢየሱስ ክርስቶስ የከፈለውን ዋጋ አምነን መቀበላችን፥ እግዚአብሄር የሰው ልጆችን ከሀጢያት በሽታ ለማዳን ያዘጋጀው ብቸኛ መንገድ ነው። በትንቢተ ኢሳይያስ መጽሀፍ ላይ፥ ነቢይ የሆነው ኢሳይያስ በመጽሀፉ 53ተኛ ምእራፍ ላይ ስለ ኢየሱስ ሲናገር እንዲህ ብሎ ነበር፦
“በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው። እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን። እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።”
በማለት ይናገራል። ከላይ እንዳነበብነው ቃል፥ ስለ እኛ መተላለፍ የቆሰለው፣ ስለ እኛ በደል የደቀቀው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። “እግዚአብሄር የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ” እንደሚለው፥ እግዚአብሄር የዓለምን ሁሉ ሀጢያት ሰብስቦ ያኖረው፥ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ብቻ ነው። ከኢየሱስ ክርስቶስ ሌላ ሀጢያታችንን የተሸከመልን ሰውም፣ መልአክም የለም። ከኢየሱስ ክርስቶስ ሌላ የእኛን ሀጢያት ዋጋ በመክፈል ከእግዚአብሄር ጋር ሊያስታርቀን የቻለ ሰውም መልአክም የለም። ለዚህ ነው ኢየሱስ በራሱ አንደበት ሲናገር “እኔ መንገድና እውነት ህይወትም ነኝ፥ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም” በማለት በዮሀንስ ወንጌል 14፡6 ላይ የተናገረው። ወደ አብ የመድረሻ መንገዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። ከእግዚአብሄር ጋር የመታረቂያ መንገዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። የዘላለምን ህይወት የማግኛ መንገዱ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። ሌላ መንገድ የለም። ሌላ አማራጭ መንገድ የለም። ሌሎች አማራጭ መንገዶች ቢኖሩ ኖሮ፥ ሌላ ከሀጢያት በማዳን እኛን ከእግዚአብሄር ጋር የሚያስታርቁን መንገዶች ቢኖሩ ኖሮ፥ ለምሳሌ መላእክቶች እኛን ከእግዚአብሄር ጋር ማስታረቅ ቢችሉ ኖሮ፥ የሀይማኖት አባቶች ሀጢያታችንን በመሸከም እኛን ከእግዚአብሄር ጋር ማስታረቅ ቢችሉ ኖሮ፥ ወይንም እኛ በምንሰራቸው ጥሩ ጥሩ ስራዎች መዳን ብንችል ኖሮ፥ ኢየሱስ ወደ ምድር መጥቶ ይሄንን ሁሉ ዋጋ መክፈል ለምን ያስፈልገው ነበር? ኢየሱስ ለምን የአምላክነት ክብሩን ትቶ ሰው ሆነ? ለምንስ ወደ ምድር መጥቶ ሀጢያታችንን ተሸከመ? ለምን የሀጢያታችንን ዋጋ ከፈለ? ከሀጢያት የመዳኛ መንገዱ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ስለሆነ ነው። ከእግዚአብሄር ጋር የመታረቂያ መንገዱ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ስለሆነ ነው። ከሞት በኋላ ያለውን የዘላለምን ህይወት የማግኛ መንገዱ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ስለሆነ ነው። ከዚህ ውጪ እኛ የምንድንበት ሌላ መንገድ ስለሌለ ነው። ወደ አንድ ቤት ውስጥ ለመግባት የቤቱን በር ማግኘት እንዳለብን ሁሉ፥ ወደ መንግስተ ሰማያት ለመግባት በሩ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መሆኑን፥ ኢየሱስ እራሱ በዮሀንስ ወንጌል ምእራፍ 10 ላይ በራሱ አንደበት ይናገራል።
መዳን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሀጢያታችን የከፈለውን ዋጋ በማመን ብቻ ነው። መዳን በስራ አይደለም በእምነት ብቻ ነው። ለመዳን የእኛ ስራ አያስፈልግም። እኛን ከሀጢያት ለማዳን ክርስቶስ ከሰራው ስራ ጋር አብሮ የሚደመር የእኛ ስራ የለም። ኢየሱስ ክርስቶስ የከፈለው ዋጋ እኛን ለማዳን በቂ ሆኖ በእግዚአብሄር ፊት ተቀባይነትን አግኝቷል። የሀጢያት ዋጋው በክርስቶስ ተከፍሏል። መልካም ነገሮችን የምናደርገው ለመዳን አይደለም። መልካም ነገሮችን የምናደርገው፥ በክርስቶስ አምነን ስለዳንን ነው። ለመዳን አንሰራም፥ ስለዳንን ግን እንሰራለን። በክርስቶስ አምነን ከዳንንና ወደ እግዚአብሄር መንግስት ከገባን በኋላ በምናደርጋቸው መልካም ተግባሮች ደግሞ እግዚአብሄር ይደሰታል። በሰማይ ቤትም ዋጋን ይሰጠናል። የዳነው ግን በስራ አይደለም በእምነት እንጂ። መጽሀፍ ቅዱስ በዮሀንስ ወንጌል ምእራፍ 3 ቁጥር 16 ላይ ሲናገር እንደዚህ ይላል።
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና። በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል” ይላል።
መዳን በእምነት ብቻ እንደሆነ ከተረዳን በኋላ፥ በክርስቶስ ማመን ማለት ታዲያ ምን ማለት ነው ብለን እንጠይቅ ይሆናል። የሰውን ልጅ ከእግዚአብሄር የለየው፥ በአዳምና በሄዋን አለመታዘዝ ምክኒያት ወደ ሰው ዘር ሁሉ የገባው ሀጢያት ነው። “ይሄንን ፍሬ በበላችሁ ጊዜ ሞትን ትሞታላችሁ” ብሎ አስቀድሞ እግዚአብሄር ለአዳም እንደተናገረው፥ ፍሬውን በበሉ ጊዜ ሞተዋል። ከእግዚአብሄር ህይወት ተለይተዋል። ሞት ማለት ከእግዚአብሄር መለየት ማለት ነው። ህይወት የተፈጠረው በእርሱ ስለሆነ፥ ከእርሱ የተለየ ህይወት በሙሉ የሞተ ነው። አንድ ሰው ከእግዚአብሄር ከተለየ፥ የሚኖረው እዚህ ምድር ላይ ብቻ ነው እንጂ ያለው በዘላለም ሞት ውስጥ ነው። በዚህች ምድር ያለው ቆይታ ሲያበቃ፥ የሚሄደው ወደ ዘላለም ሞት ወይንም ወደ ገሀነመ እሳት ነው።
ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው ታዲያ የዚህን ሀጢያት ዋጋ በመክፈል እና የዘላለምን ሞት ከሰው ልጆች ላይ በማስወገድ፥ በእግዚአብሄርና በሰው ልጆች መካከል ተቋርጦ የነበረውን ህብረት ለማስተካከል ነው። በሀጢያት ምክኒያት ለሞተው መንፈሳችን ህይወትን በመስጠት፥ እንደገና ህያዋን እንድንሆንና የዘላለምን ህይወት ወይንም መንግስተ ሰማያትን እንድንወርስ ነው። ይሄንን የዘላለም ህይወት የሚወርሱት ታዲያ፥ መጀመሪያ በሰው ዘር ሁሉ ላይ በመጣው ሀጢያት ምክኒያት ሀጢያተኞች መሆናቸውን የሚያምኑ እና ስለዚህ ሀጢያት ክርስቶስ የከፈለውን ዋጋ አምነው የሚቀበሉ ሰዎች ብቻ ናቸው። ኢየሱስ ለዓለም ሁሉ ቢሞትም፥ የሚድኑት ግን በእምነት የሚቀበሉት ሰዎች ብቻ ናቸው። መጽሀፍ ቅዱስ በዮሀንስ ወንጌል ምእራፍ 3 ቁጥር 36 ላይ እንዲህ ይላል።
“በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።” ይላል።
ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህች ምድር ሳይመጣ በብሉይ ኪዳን የነበረውን ስርዓት ስትመለከቱ፥ ሰዎች ሀጢያትን ሲሰሩ የእንስሳቶችን ደም በማፍሰስ ጊዜያዊ የሆነ የሀጢያት ስርየትን ያገኙ ነበር። ታዲያ ሀጢያታቸውን ይዞ በእግዚአብሄር ፊት የሚቆመው ካህን፥ እርሱም ሰው ስለሆነና ሀጢያት ስላለበት፥ መጀመሪያ የራሱ ሀጢያት እንዲሰረይ የእንስሳን ደም በማፍሰስ የሀጢያትን መስዋእትን ማቅረብ ይጠበቅበታል። መጽሀፍ ቅዱስም በዕብራውያን መጽሀፍ ምእራፍ 9 ቁጥር 22 ላይ ሲናገር፥ “እንደ ሕጉም ከጥቂቶች በቀር ነገር ሁሉ በደም ይነጻል፥ ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም” ይላል። ደም ሳይፈስ የሀጢያት ስርየት ስለሌለ ነው አባቶቻችን ስለ ሀጢያታቸው የእንስሳቶችን ደም ያፈሱ የነበሩት። ይሄ እንግዲህ ክርስቶስ ወደ ምድር ሳይመጣ በፊት እግዚአብሄር ለህዝቡ የሰጣቸው የብሉይ ኪዳን ስርዓት ነበር። አዲስ ኪዳን ላይ ወዳለው ወደ እግዚአብሄር ዘላለማዊ ሀሳብ ስንመጣ ግን፥ እየደጋገምን የእንስሳቶችን ደም እንዳናፈስ፥ ሀጢያታችን ይሰረይ ዘንድ፥ ሀጢያት የሌለበት የጻድቅ ሰው ደም አንድ ጊዜ መፍሰስ ነበረበት። የሰው ልጅ ሁሉ ደግሞ በሀጢያት ስለተበከለ፥ ጻድቅና ፍጹም ሆኖ የተገኘው የእግዚአብሄር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነበር። ይሄ ጻድቅ ደም አንድ ጊዜ ስለ ሀጢያታችን ፈሷል! የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከየትኛውም ካለንበት ሀጢያት እኛን የማንጻት አቅም አለው። የእንስሳቶች ደም ጊዜያዊ የሆነ የሀጢያት ስርየትን ያመጣ ነበር፥ የክርስቶስ ደም ደግሞ ዘላለማዊ የሆነ የሀጢያት ስርየትን ወደ ህይወታችን አምጥቷል። በአዳም አለመታዘዝ ምክኒያት በላያችን ካለው ሀጢያት፥ እንዲሁም እኛ ሰርተናል ብለን ከምናስበው ከየትኛውም አይነት ከባድ ሀጢያት የሚያነጻን፥ በመስቀል ላይ ስለ እኛ ሀጢያት የፈሰሰው የእግዚአብሄር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ብቻ ነው። ከሀጢያታችን ለመንጻት የሚያስፈልገን፥ ደሙ ስለ እኛ ሀጢያት መፍሰሱን ማመንና በእግዚአብሄር ፊት እውነተኛ ንሰሐ መግባት ብቻ ነው። መጽሀፍ ቅዱስ በ1ኛ ዮሀንስ ምእራፍ 1 ቁጥር 7 ላይ ሲናገር፥
“..የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል” በማለት ይናገራል።
አሁን ሀጢያታችንን ለማስተስረይ፥ የእንስሳቶችን ደም ማፍሰስ አያስፈልገንም ምክኒያቱም የክርስቶስ ደም አንድ ጊዜ ስለ ሀጢያታችን ፈሶልናል። አሁን ሀጢያታችንን እንዲሰረይ፥ የሰው ካህን አያስፈልገንም ምክኒያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ የዘላለም ሊቀ ካህናችን ሆኖ ሀጢያታችን ይሰረይ ዘንድ በእኛና በእግዚአብሄር መካከል ገብቷል። ሀጢያት ስንሰራ፥ ባለንበት ቦታ ሆነን ሀጢያታችንን ለእግዚአብሄር በመናዘዝና እውነተኛ ንሰሀ በመግባት፥ በክርስቶስ ደም እንዲያጥበን እግዚአብሄርን መጠየቅ እንችላለን።
“ፀጋው በእምነት አድኖናል” በማለት በኤፌሶን ምእራፍ 2 ቁጥር 8 ላይ እንደሚናገረው፥ የእግዚአብሄር ጸጋ ያዳነን፥ በእኛ እምነት ውስጥ አልፎ ነው። እምነታችን፥ ከሀጢያት አዳኝ የሆነው የእግዚአብሄር ጸጋ በህይወታችን የሚሰራበት ዋና መንገድ ነው። እምነታችን፥ ለኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ስራ የምንከፍተው በር ነው። ዘላለማችንን ከሲኦል አድኖ በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ እንድናሳልፍ እግዚአብሄር የሚጠቀምበት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው።
ይሄንን የእግዚአብሄር ቃል እውነት በበለጠ ለመረዳትና እርዳታ ለማግኘት፥ ወይንም ክርስቶስን ለማመንና እንደ ግል አዳኞት አርገው ለመቀበል እርዳታ ከፈለጉ፥ በኢሜል አድራሻ hanaelias10@gmail.com መልእክትን በመጻፍ ጥያቄዎችን መጠየቅ ወይንም የሚፈለገውን እርዳታ ማግኘት ትችላላችሁ።

"Our true success in this life is being able to fulfill the purpose we were created for!"